ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.39.0-wmf.21
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
Module
Module talk
Gadget
Gadget talk
Gadget definition
Gadget definition talk
መጽሐፈ ሄኖክ
0
9743
372142
372130
2022-07-26T15:08:47Z
Beza legesse
39478
አንድ ለውጥ 372130 ከ[[Special:Contributions/196.189.182.184|196.189.182.184]] ([[User talk:196.189.182.184|ውይይት]]) ገለበጠ
wikitext
text/x-wiki
'''መጽሐፈ ሄኖክ''' ጥንት የተጻፈ የ[[መጽሐፍ ቅዱስ]] [[ዲዩትሮካኖኒካል]] መጽሓፍ ነው። በ[[ኢኦተቤ|ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን]] እምነት ዘንድ ይህም በሰዎች ቃላት በ[[ግዕዝ]] በ[[ያሮድ]] ልጅ በ[[ሄኖክ]] ከ[[ማየ አይህ]] አስቀድሞ ተጽፎ ነበር።
በመጽሓፉ [[ሄኖክ]] ከእግዚአብሔር ብዙ ራዕዮች ሲያይ ይናገራል። [[ደቂቀ ሴት]] (ትጉሃን) በአመጻቸው ጽናት ከ[[ቃየል]] ልጆች ጋራ አብረው እንዲዋሀዱ ከደብረ ቅዱስ በወረዱበት ጊዜ ሄኖክ እንደ ገሠጻቸው ይላል። የከለሱት ልጆቻቸውም በቁመት አብልጠው ረጃጅሞች እንደተባሉ እነዚህም አባቶቻቸውንና ምድሪቱን እንደ በደሉ ይላል። በሠሩት እጅግ ክፉ ሥራ ምክንያት የጥፋት ውኃ እንደሚደርሰባቸው ፈጽሞም እንደሚያሰምጣቸው የሚል የ[[ትንቢት]]ም መጽሓፍ ነው። ይህም ትንቢት [[ኖህ]] በኖረበት ዘመን የተፈጸመ እንደነበረ የሚያምኑ ኣሉ።
በተጨማሪም ሄኖክ ወደ ሰማያት ተወስዶ የሰማይ ቦታዎችን ያሳዩታል። ከዚህ በላይ ስለ [[እግዚአብሔር መንግሥት]] ብዙ ይነበያል፤ ያኔ ጻድቃን ሺ ልጆችን ይወልዳሉና በሰላም በደስታ እንደሚኖሩ የሚል ትንቢት ነው። በዚህ መሠረት የ[[መሢህ]]፣ [[የሙታን ትንሣኤ]] እና የ[[ዕለተ ደይን]] ትንቢቶች መጀመርያ ከሄኖክ ወይም ከ[[አዳም]] ዘመን ጀምሮ ተገለጹ።
መጽሐፉ በሙላቱ የታወቀው በግዕዙ ትርጉም ብቻ ሲሆን፣ የተጻፈበት ቋንቋ፡ በተለይም በ[[ኢትዮጵያ]] መምህራን ዘንድ፡ ግዕዝ መሆኑ ይታመናል። ከዚህም ውጭ አንዳንድ ፍርስራሽ ብራና ቅጂዎች በ[[ሙት ባሕር ብራናዎች]] (በ[[ቁምራን]] ዋሾች) መካከል በ[[አረማይስጥ]] ቋንቋ በ1950ዎቹ በመገኘታቸው፣ በምዕራባውያን ሊቃውንት ዘንድ መጀመርያ የተቀነባበረበት ልሳን ግዕዝ ሳይሆን አረማይስጥ ይሆናል የሚሉ አሉ። ከዚህም በላይ አንዳንድ የ[[ግሪክኛ]] ወይም የ[[ሮማይስጥ]] ምንባቦች በከፊል ተርፈዋል።
== ምሳሌ ==
ለምስጋና የሚተጉ የከበሩ የመላእክት ስማችው ይህ ነው።
ከከበሩ ከመላእክት አንዱ [[ቅዱስ ዑርኤል]] በመብረቅ በነጐድጓድ የተሾመ ነው።
በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ [[ቅዱስ ሩፋኤል]] ነው።
ዲያብሎስን የሚበቀለው አጋንንትንም የሚበቀላችው ከከበሩ ከመላእክት አንዱ [[ቅዱስ ራጉኤል]] ነው።
ለሰው ባደረገው በጎነት ላይ ለሕዝቡ ታዛዥ ነውና ከከበሩ ከመላእክት አንዱ [[ሚካኤል]] ነው።
አእምሯቸውን ባጡ ሰዎችም ላይ የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሠረቃኤል ነው።
በባቦች ላይ በጎነትም ባሉ ጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ [[ገብርኤል (መልዐክ)|ገብርኤል]] ነው። -- [[ሄኖክ]] 6፡1-7
== የይሁዳ መልእክት ==
[[የይሁዳ መልእክት]]፡
፡1፡14-15 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።
== መጽሐፉን ለማንበብ ==
[[ስዕል:3-apoch-3-cr.pdf|thumb|left|300px| የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [http://am.wikipedia.org/w/index.php?title=%E1%88%B5%E1%8B%95%E1%88%8D:3-apoch-3-cr.pdf&page=4] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች ማንበብ ይችላላሉ|page=4]]
*[http://www.tau.ac.il/~hacohen/Henoch/Henoch%201.html መጽሐፈ ሄኖክ በግዕዝ]
*[http://www.tau.ac.il/~hacohen/Henoch/Henochp%201.html መጽሐፈ ሄኖክ በግዕዝ (ሌላ ዕትም)]
*[http://www.good-amharic-books.com/library?id=1475 መጽሐፈ ሄኖክ - ከጥንት አባቶቻችን ሲወርድ ሲዋረድ የተቀበልነው የአንድምታ ትርጓሜ] - ኢ.ኦ.ተ.ቤ.
<references/>
{{መዋቅር}}
[[መደብ:አዋልድ መጻሕፍት]]
[[መደብ:ግዕዝ]]
[[መደብ:ትንቢት]]
e3sf4vihdyur02d561d1669mnlbrpo1
አይሳክ ኒውተን
0
9896
372140
370387
2022-07-26T13:08:12Z
77.98.153.90
wikitext
text/x-wiki
[[ስዕል:Isaac Newton-1689.jpg|thumb|300px]
'''ሰር አይሳክ ኒውተን''' ከ[[ጃንዩዌሪ]] 4 ቀን [[1663 እ.ኤ.አ.]] እስከ [[ማርች]] 31 ቀን [[1727 እ.ኤ.አ.]] የኖረ [[እንግሊዛዊ]] የ[[ፊዚክስ]]፤ የ[[ሒሳብ]]፤ የ[[ስነ ክዋክብት]]፤ የ[[ስነ መለኮት]]፤ የ[[ተፈጥሮአዊ ፍልስፍና]] እና ጥንት የነበረው የ[[አልኬሚ]] ምሁር ነበረ። ምናልባትም ኒውተን በጣም ከሚታወቅባቸው ነገሮች ውስጥ ሶስቱ የኒውተን [[ሥነ-እንቅስቃሴ]] ህጎች ፤ [[የኒውተን የግስበት ቀመር]]፤ [[ካልኩለስ]] ለተባለውን የሒሳብ ክፍል መጀመር (ይህን ክብር ከጀርመናዊው ምሁር ከ[[ጎትፍሪድ ሌብኒትዝ]] ጋር ይጋሩታል)፤ ስለ [[ብርሃን]]ና ስለሚይዛቸው [[ቀለም|ቀለማት]] ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኒውተን የእንቅስቃሴ ህጎችን በመጠቀም የፕላኒቶች (ፈለገ ሰማያት) እንቅስቃሴ በነዚሁ ህጎች እንደሚመሩ በማሳየት እና የሌላ ምሁር የጃናንስ [[ኬፕለር]] የፕላኒቶች እንቅስቃሴ ህግ ጋር እንደሚጣጣም በማሳየት ፤ በፊት ይታመንበት የነበረውን መሬት የሁሉም ነገሮች ማዕከል ናት የሚባለውን ሐሳብ ትክክል እንዳልሆነ በሳይንሳዊ መንገድ አሳይቷል።
== የህይወት ታሪክ ==
ሰር አይሳክ ኒውተን በ4ኛ ቀን 1642 አመተ ምህረት ተወለደ። አባቱ ከመወለዱ በፊት በመሞቱ እናቱ ከሌላ ባል ጋር ኮበለለች። ስለዚህ ከአያቱ ጋር መደግ ጀመረ። ከ 12-10 አመት ድረስ ኒውተን በግራንተም ግራመር ት/ቤት ውስጥ ተማረ። ኒውተን ገበሬ መሆን ባለመፈለጉ ወደ ተሪኒቲ ኮሌጅ ካምበሪጅ ገባ። ዲግሪውን በ፩፮፭፱ ጨረሰ። ነገር ግን በ፩፮፮፮ በነበረው ወረርሽ ምክንያት ከኮሌጁ መሰደድ ነበረበት። በቀጣዩ አመት ተመለሰ።
በቀጣዮቹ አመታት ስለ ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች፣ ካልኩለስ እናም ስለ ነጭ ብርሃን እና ስለሚይዛቸው [[ቀለም|ቀለማት]] ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በማርች ፫፩ ቀን ፩፯፪፯ ከዚህ አመት በሞት ተለየ ኒውተን ራሳቸውን በቀላሉ ከሚገልጹ ተመራማሪዎች አንዱ ነበር።።
{{Commons|Isaac Newton}}
{{clear}}
{{መዋቅር}}
[[መደብ:የእንግሊዝ ሰዎች]]
[[መደብ:ሒሳብ ተመራማሪዎች]]
[[መደብ:ሳይንቲስቶች]]
[[መደብ:ፊዚሲስቶች]]
kx1ufyemlf3v4498bllef8umwtgj5y7
372141
372140
2022-07-26T13:09:18Z
77.98.153.90
wikitext
text/x-wiki
[ስዕል:Isaac Newton-1689.jpg|thumb|300px]
'''ሰር አይሳክ ኒውተን''' ከ[[ጃንዩዌሪ] 4 ቀን [[1663 እ.ኤ.አ.] እስከ [[ማርች]] 31 ቀን [[1727 እ.ኤ.አ.]] የኖረ [[እንግሊዛዊ]] የ[[ፊዚክስ]]፤ የ[[ሒሳብ]]፤ የ[[ስነ ክዋክብት]]፤ የ[[ስነ መለኮት]]፤ የ[[ተፈጥሮአዊ ፍልስፍና]] እና ጥንት የነበረው የ[[አልኬሚ]] ምሁር ነበረ። ምናልባትም ኒውተን በጣም ከሚታወቅባቸው ነገሮች ውስጥ ሶስቱ የኒውተን [[ሥነ-እንቅስቃሴ]] ህጎች ፤ [[የኒውተን የግስበት ቀመር]]፤ [[ካልኩለስ]] ለተባለውን የሒሳብ ክፍል መጀመር (ይህን ክብር ከጀርመናዊው ምሁር ከ[[ጎትፍሪድ ሌብኒትዝ]] ጋር ይጋሩታል)፤ ስለ [[ብርሃን]]ና ስለሚይዛቸው [[ቀለም|ቀለማት]] ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኒውተን የእንቅስቃሴ ህጎችን በመጠቀም የፕላኒቶች (ፈለገ ሰማያት) እንቅስቃሴ በነዚሁ ህጎች እንደሚመሩ በማሳየት እና የሌላ ምሁር የጃናንስ [[ኬፕለር]] የፕላኒቶች እንቅስቃሴ ህግ ጋር እንደሚጣጣም በማሳየት ፤ በፊት ይታመንበት የነበረውን መሬት የሁሉም ነገሮች ማዕከል ናት የሚባለውን ሐሳብ ትክክል እንዳልሆነ በሳይንሳዊ መንገድ አሳይቷል።
== የህይወት ታሪክ ==
ሰር አይሳክ ኒውተን በ4ኛ ቀን 1642 አመተ ምህረት ተወለደ። አባቱ ከመወለዱ በፊት በመሞቱ እናቱ ከሌላ ባል ጋር ኮበለለች። ስለዚህ ከአያቱ ጋር መደግ ጀመረ። ከ 12-10 አመት ድረስ ኒውተን በግራንተም ግራመር ት/ቤት ውስጥ ተማረ። ኒውተን ገበሬ መሆን ባለመፈለጉ ወደ ተሪኒቲ ኮሌጅ ካምበሪጅ ገባ። ዲግሪውን በ፩፮፭፱ ጨረሰ። ነገር ግን በ፩፮፮፮ በነበረው ወረርሽ ምክንያት ከኮሌጁ መሰደድ ነበረበት። በቀጣዩ አመት ተመለሰ።
በቀጣዮቹ አመታት ስለ ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች፣ ካልኩለስ እናም ስለ ነጭ ብርሃን እና ስለሚይዛቸው [[ቀለም|ቀለማት]] ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በማርች ፫፩ ቀን ፩፯፪፯ ከዚህ አመት በሞት ተለየ ኒውተን ራሳቸውን በቀላሉ ከሚገልጹ ተመራማሪዎች አንዱ ነበር።።
{{Commons|Isaac Newton}}
{{clear}}
{{መዋቅር}}
[[መደብ:የእንግሊዝ ሰዎች]]
[[መደብ:ሒሳብ ተመራማሪዎች]]
[[መደብ:ሳይንቲስቶች]]
[[መደብ:ፊዚሲስቶች]]
37lkj54erwcu4njbk5d1b3ug7tuy38y
ገብርኤል (መልዐክ)
0
25911
372145
361575
2022-07-26T18:36:11Z
ክርስቶስሰምራ
27288
wikitext
text/x-wiki
{{infobox|abovestyle=background:#7CB9E8|above=ቅዱስ ገብርኤል|image=[[ስዕል: L' Annonciation de 1644, Philippe de Champaigne..jpg|264px|center|ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል [[ማርያም|ማርያምን]] ወልድን እንደምትወልድ ሲያበሥራት (ብሥራተ ገብርኤል)]]|caption=|headerstyle=background:#7CB9E8|header1=ብሥራተ ገብርኤል |headerstyle=background:#7CB9E8|header8=<span style="color:#FFBF00">
</span>|label1=ሚካኤል ማለት|data1=ዕፁብ ድንቅ ነገር|label2=መዐረግ|data2= ሊቀመላዕክት |label5=፫ኛ በዓለ ንግሥ|data5='''[[ቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል|ታኅሣሥ ፲፱ ሦሥቱን ደቂቃት ከእሳት ያዳነበት]]''' |label4=፪ኛ በዓለ ንግሥ|data4='''[[ሐምሌ ፲፱]]''' [[ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ቅድስ እያሉጣ|ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት እያሉጣን ከእሳት ያወጣበት]]|label3=፩ኛ በዓለ ንግሥ|data3='''[[ቤተ ማርያም|ታኅሣሥ ፳፪ ብሥራተ ገብርኤል]]'''|captionstyle=|header5=}}
'''ገብርኤል''' ('''ቅዱስ ገብርኤል''') '''በ[https://en.m.wikipedia.org/wiki/God_in_Abrahamic_religions አብርሃማዊ ሀይማኖቶች]''' ([[ክርስትና]] ፤ [[አይሁድ]] ፤ [[እስልምና]]) ከሶስቱ ዋና '''የ[[እግዚአብሔር]]''' መላዕክት ([[ቅዱስ ሚካኤል]]፡ [[ገብርኤል (መልዐክ)|ቅዱስ ገብርኤል]]፡[[ቅዱስ ሩፋኤል]]) አንዱ ነው። በ[[መጽሐፍ ቅዱስ]] ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በ[[መጽሐፈ ዳንኤል]] ነው። የስሙም ትርጉም «ከእግዚአብሔር የሆነ አለቃ» ማለት ነው። በእግዚአብሔር ፊት መቆም ከሚችሉ ስባት መላዕክት ውስጥም አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል። የአምላካችን፣ የጌታችንና የመድሐኒታችን የ[[ኢየሱስ ክርስቶስ]]ን ልደት ለቅድስት [[ድንግል ማርያም]] አብስሯል።
በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት ፡
=='''ይህን ይመለከቱ'''==
==='''ሰውን ይረዳሉ'''===
ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/
==='''ስግደት ይገባቸዋል'''===
ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12-14/ መሳ.13፡2-22/ 1ኛ ዜና 21፡1-16/ ዳን.8፡15-17
እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ይህም ደግሞ እውነት ነው፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል።
== '''የቅዱስ ገብርኤል አንዱ ተአምር''' ==
እስራኤልላውያን በምርኮ ወደ ባቢሎን ምድር ወረዱ በዚያም በግዞት ኑሮዋቸውን ሲገፎ ሰነበቱ፡፡ የባቢሎንም ምድር ንጉስ የነበረው ናቡከደነጾር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድሳ ክንደ የሆነ ጣዖትን አሰርቶ ዱራ በሚባል ሜዳ ላይ አስቆመው በዚያም አንድ ትህዛዝን አዘዘ በእርሱ ግዛት ስር የሚተዳደሩትን በሙሉ እንደዚህ አላቸው የመለከት ድምጽ በሰማችሁ ጊዜ ለዚህ እኔ ላቆምኩት ምስል ስገዱ የማይሰግድ ግን በዚህ በሚነደው እቶን እሳት ስር ይጣላል አለ፡፡
እንደተባለውም የመለከቱ ድምጽ በተሰማ ጊዜ ሁሉም በግባሩ ተደፍቶ ለቆመው ምስል ሰገደ፡፡ ነገር ግን ከሕዝቡ ምካከል ሦስት ሰዎች ሳይሰግዱ ዝም ብለው ቆሙ፡፡ አስተናባሪዎቹ ግን እንዲሰግዱ ለመኑዋቸው ልጆቹ ግን እንቢ አሏዋቸው፡፡ ይህን ባለማድረጋቸው ወደ ሚነደውና ድምጽም ወደሚያስፈራ እሳት አመላከቷዋቸው ነገር ግን ጸንተው ቆሙ ልጆቹ ‹‹አምላኩን የሚያውቅ ሕዝብ ይቃወሙታል›› ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፡፡
በመሆኑም ልጆቹ ይህን በጽናት ተቃወሙት፡፡ አንሰግድም ብለውም በጽናት ቆሙ፡፡ ‹‹የምናመልክው አምላክ ከዚህ ከሚነደው እሳት ያድነናል ባያድነን እንኳን አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም›› አሉት፡፡
በመጨረሻም ሶስቱንም ከሚነደው እሳት ውስጥ ጣሏቸው፣ከራሳቸው ጸጉር አንዲት እንኳን ሳይነካ ይባስ ብሎ ሶስት አድርገው የጣሏቸው አራት ሆነው ተገኙ፤ አራተኛው ቅ'''ዱ'''ስ ገብራኤል ነው ፤የሚነደውን እሳት ውሃ አድርጎላቸው በእሳት ውስጥ እየተመላለሱ ይዘምሩም ነበር፤ንጉሱ ናቡከደነጾርም ይህን ታምር አይቶ በእግዚአብሔር አመነ (ትን. ዳን. ምዕራፍ 3)።
== '''የእምነት ከፍተኛ ደረጃ''' ==
ይህ ዓይነት ነገር ታላቅ እምነት ነው በዚህም ደግሞ ወንጌልን በኦሪት ያስተምሩናል፡፡ ይህም ማለት ‹‹ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው›› እነዚህም ልጆች ሳያዩ አመኑ ድግሞም ቁርጥ ያለ መለስ መለሱ፡፡ በቅዱሱ አምላክ መታመን ማለት የእርሱን ጥበቃ የሚሆነውን ታላቅ ድህነት እናገኛለን ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› መዝ.33፡7፡፡ ይህም በመሆኑ ታዳጊው አምላክ እነርሱን ለመታደግ ሲል መላእክትን ይልካል፡፡
በዚህም ሁኔታ ንጉሱ ናቡ ከደነጾር በቁጣ እንዲህ አለ ወደ እሳቱ ጨምሩዋቸው አለ፡፡ ወስደውም ወደ እሳቱ ጨመሩዋቸው ነገር ግን በዚህ መሀል አንድ ትልቅ ነገር ተከሰተ ከሚጣሉት ሶስቱ ልጆች ጋራ ቀድሞ የተገኘው አራተኛው የእግዚአብሔር መልአክ ነበር፡፡ እሳቱም መካከል በዝማሬ ተሞሉ፡፡ በዚያም የነበሩት ሁሉ በሆነው ነገር ተገረሙ፡፡ ንጉሱም እንዲህ አለ ‹‹እኔ የተፈቱ በእሳቱ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለው ›› አለ አራተኛውንም ሲገልጸው ‹‹የአምላክን መልክ ይመስላል›› አለ፡፡
ከሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብረኤል በገነት አበቦች መካከል የተሾመው የአምላክ ባለሙዋል ነበር መ.ሔኖክ 10፡14፡፡ ከእሳቱ ውስጥ የነበርው፡፡ ለአምላካቸው የሚታመኑትን የሚረዱና የሚያገለግሉ የአምላካችን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ቅዱሳን መላእክት ሁሌም ቢሆን እኛን ለመርዳት ይፈጥናሉ፡፡ በመሆኑም መላእክት ፈጣንና ሰውን ለመታደግ የሚተጉ ናቸው፡፡ ‹‹ቅዱሳን መላእክት አፈጣጠራቸው እም ኀበ አልቦ ኀበ ቦ (ካለመኖር ወደ መኖር) አምጥቶ ነው፡ ነገር ግን በግበራቸው በእሳትና በነፋስ ተመስለዋል፡፡ ይህውም እሳት ረቂቅ ነው መላእክትም እንደዚሁ ረቂቃን ናቸው፡ ነፋስ ፈጣን ነው እንደዚሁ መላእክት ፈጣን ናቸው ለተልእኮና እኛን ለመርዳት ፈጣን ናቸው›› (አክሲማሮስ) መዝ. ‹‹መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዮቹን እሳት ነበልባል›› ይላል በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ተፈጥሮ ሲነግረን እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ እንዲህ ይለናል፡-‹‹ሁሉ መዳንን ይወረሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን ›› ዕብራውያን 1፡14፡፡ አምላካችን ሁላችንንም ከዚህ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡
ክርስትያኖች የአምላክን መልዕክተኛ «ገብርኤል» ሲሉት በ[[እስልምና]] ደግሞ በ[[አረብኛ]] ስሙ «[[ጂብሪል]]» ይባላል።
{{መዋቅር-ሃይማኖት}}
{{መደብ:ክርስትና}}
h3bkijogrurq37efz32ackrnffrlwwz
እዝራ እጅጉ ሙላት አለሙ
0
52622
372144
2022-07-26T17:19:06Z
እዝራ እጂጉ
40196
hhh
wikitext
text/x-wiki
'
መዝገበ አእምሮ የተሰኘውን መጽሀፍ ጨምሮ 6 መጽሀፍትን ለንባብ አብቅቷል፡፡ የ44 ሰዎችንም ታሪክ በኦድዮ እና በዲቪዲ አሳትሟል፡፡ ታሪክ ሰናጁ ይሉታል ብዙዎች፡፡እዝራ እጅጉ
እዝራ እሁድ መጋቢት 30፣ 1971 ዓ.ም ተወለደ፡፡ በ1971 አመት ግንቦት ወር የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ይሰሩ የነበሩት አባቱ አቶ እጅጉ ሙላት ወደ ጅቡቲ በመዛወራቸው እትብቱ የተቀበረባትን መሬት ሳይድህባት በእናቱ ወይዘሮ በለጥሻቸው ስዩም እቅፍ ሁኖ አባቱን ተከትሎ ጅቡቲ ገባ።በጅቡቲ 4 አመታት ኖሩ፡፡
ከጅቡቲ መልስ በ1976 ዓ.ም ‘ማርች ኤይት’ ትምህርት ቤት ገብቶ ለሁለት አመታት የመዋእለ ህጻናት ትምህርቱን ተከታተለ። ቀጥሎ ወደ ‘ቦሌ ህብረተሰብ’ አቅንቶ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በቦሌ ህብረተሰብ አጠናቅቋል፡፡ከዚያም ሁለተኛ ደረጃ ቦሌ አጠቃላይ ተማረ፡፡
የስነጽሁፍ ዝንባሌ
በ1981 ዓ.ም ክረምት አባቱን ድጋሜ የምስራቁ ማግኔት ስቧቸው ወደ ድሬደዋ ሲያቀኑ እርሱም ከታናሽ እህቱ ጋር ሁኖ ተከተላቸው። የሚድያ ማግኔት ደግሞ እርሱን ሳበው፡፡ ቦሌ ህብረተሰብ እያለ የተረት መጽሐፍትን ማንበብ ድረስ ብቻ የነበረ የሥነ ጽሑፍ ቅርበቱ፤ በድሬዳዋ ቆይታው በብዙ እጥፍ አድጎ ልቦለዶችን እስከመጻፍ ደረሰ። አባቱ ቢሮ ይመጡ የነበሩ አዲስ ዘመንና የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጦችንና የካቲት መጽሔትን የማንበብ እድሉም ነበረው።
በጅቡቲ አመታትን የሰነበቱት አባቱ ለፈረንሳይኛ ቅርብ ስለነበሩ የፈረንሳይኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ነበራቸው። ብላቴናው እዝራ ገና ያኔ ይህን መጽሐፍ ሲያገላብጥ ነበር አሁን እያሰናዳ ያለውን መዝገበ አዕምሮ(ኢንሳይክሎፒዲያ) የማዘጋጀት ሃሳብ የመጣለት።
እንደልጆቹ ወጣ ብለህ ተጫወት” እስኪሉት ድረስ ከወረቀት ጋር ተዋደደ። 8ኛ ክፍል ሲደርስ ለተለያዩ መጽሔቶች አስተያየትና ስራዎቹን ‘እዝራ እጅጉ ከቦሌ’ በሚል አድራሻ መላክ ጀመረ። 42ቱ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሲባረሩ ስሜቱን ጽፏል፤ 9ነኛ ክፍል ሲሻገር ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ሳለ ንባብና ተሰጥዖውን ለማሳደግ ሚኒ ሚዲያ ለመግባት ቢያመለክትም ሳይጠራ ይቀራል። በዚህ ተናዶ የሚኒ ሚዲያው በር ላይ ያገኘው አንተነህ ዓለሙን እንዴት በጉልበት ገፍቶት እንደገባ አይዘነጋውም፡፡
በዚያው አመት ወደ ለገዳዲ ሬዲዮ ጣቢያ አቅንቶ መሳተፍ ጀመረ። ለመጀመሪያ ጊዜ ለገዳዲ ሲደርስ ተቀብለው፤ ሻይ ጋብዘው፤ ቤተ መጽሐፍቱን አስጎብኝተው ያበረታቱት መምህራንን ዛሬም ድረስ ከነስማቸው ያስታውሳል። “ጣሰው ተፈራ፣ ሃይሉ ማሞ፣ ኤርሚያስ ተገኝ፣ ህሊና ማሞ፣ ከድጃ ሰይድ” እያለ ስማቸውን ጠራ፡፡ቤተ መጽሐፍቱን በአግባቡ ተጠቅሞበታል፤ ‘ዘ ወርልድ ቡክ ኦፍ ኢንሳይክሎፒዲያ... ብሪታኒካ’ ጋር ተዋውቆበታል፣ ለገዳዲ ሬዲዮ የጥያቄና መልስ ዝግጅት ከ300 ያላነሱ ጥያቄዎችን አዘጋጅቶበታል።ገና የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሳለ፡፡
በ1989 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፍ የነበረ “አካፑልኮ ቤይ” የተሰኘ ፊልምን ወደ አማርኛ መልሶ ከያኔ የትምህርት ቤት ተጋሪው አርቲስት ስናፍቅሽ ተስፋዬ ጋር በመሆን በቦሌ ሚኒ ሚዲያ ተረከ። ከፊልሙ ትረካ መጠናቀቅ በኋላ የሚዲያዎችን ትኩረት ሳበ። ከኢቲቪ፣ ከሬዲዮ ፋና፣ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ የመጡ ጋዜጠኞች ስለሰራው ትርጉም በየተራ አነጋገሩት።
በ1990 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍን ለመማር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማታው መርሃ ግብር ተመዘገበ። ከአብሮ አደጉ ናይእግዚ ጋር በመሆን የሚዲያ ፈቃድ አውጥተው “ልጅነት” የምትል የልጆች መጽሔት ለማሳተም ቢሞክሩም በስፖንሰር ማጣት ምክንያት ሀሳባቸውን ሳያሳኩ ቀሩ። በተመሳሳይ አመት እዝራ ወደ ሪፖርተር ጋዜጣ አምርቶ ቅጥር ጠይቆ ስላልተሳካ በነፃ ማገልገል ጀመረ። ለወራት በዘለቀ የነፃ ግልጋሎቱ ደረጀ ደስታ፣ ከበደ ደበሌ ሮቢ፣ ሰለሞን አባተ፣ እሸቴ አሰፋና አብዱ አሊ ሂጅራን ጨምሮ ከሌሎች አንጋፋዎች ጋር ቢሮ ተጋርቶ ጽሑፎቻቸውን አርሟል፣ ዝንቅና ሌሎች አምዶችን አዘጋጅቷል፣ ደሞ በልጅ እግሩም ለአንጋፋዎቹ ተላልኳል።
ቀጥሎ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ አመለከተ፤፤ ከብዙ መቶዎች ተወዳድሮ ሃይለ ገብርኤል ይመርን ተከትሎ፣ ታገል ሰይፉን አስከትሎ፣ በሁለተኝነት አለፈና ጋዜጠኛ ሆነ። 1992 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ በ21 አመቱ፣ ገና የ3ኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለ፣ በ347 ብር የሙሉ ጊዜ ጋዜጠኛ ሲሆን የተሰማውን ደስታ ዛሬም ከአእምሮው የሚጠፋ አይደለም፡፡
መዝናኛ ክፍልን እየፈለገ ዜና ክፍል ሲመድቡት መጀመሪያ ላይ አልከፋውም ነበር፤ እንዲያውም ‘በሳምንት 4 ዜና ማምጣት አለብህ’ ያለ አለቃውን በተለየ ጉጉት ሁኖ “7 አይቻልም?” ብሎ ጠይቆት ነበር። የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታትን ሰባትም ስድስትም ዜናዎችን መስራት ቢችልም እየቆየ ሲሄድ ግን እንዳሰበው ቀላል ሊሆንለት አልቻለም። በዜና እጦት ራሱን እያመመው ሻሽ አስሮ ቢሮው ይገባ እንደነበር ያስታውሳል። ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ የአዲስ ልሳን ጋዜጠኝነቱን ተወ።
ከአዲስ አድማሶች ደጅ ደረሰ። “ለኔ የሚሆን ትክክለኛ ሰው” በማለት የሚገልፀው አሰፋ ጎሳዬ በጥሩ ፊት ተቀብሎ በ400 ብር ቀጠረው። ከነብይ መኮንን፣ ኤፍሬም እንዳለ፣ ሰለሞን ገ/እግዚአብሔር እና ሌሎችም ጋር ባልደረባ ሁኖ ሲሰራ ዜናንም መዝናኛንም አቀላጥፎ ሰርቷል። አዲስ አድማስ ለአንድ አመት ከሰራ በኋላ ወደ ሩህ ጋዜጣና መጽሄት አቀና፡፡ በመሀል አዲስ አድማስ እየሰራ እለታዊ አዲስ ለተሰኘው ጋዜጣ ናምሩድ ዩርታና በሚል የብእር ስም ይጽፍ ነበር፡፡
በ1994 ዓ.ም ከተመረቀ በኋላ በ500 ብር ደመወዝ ‘ዘ ፕሬስ’ ገባ። በዚያ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን ማስታወቂያ የማፈላለግ ስራንም ሰርቶ ዳጎስ ያለ ኮሚሽን እንደተቀበለ ያስታውሳል። ምን አልባት ይህቺኛዋ ኮሚሽን ሳትሆን አትቀርም ወደ ቢዝነሱ ዓለም ቀልቡ እንዲሳብ ያደረገችው። በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ማርኬቲንግን መማር ጀምሮ ነበር። ዮቴክ ኮንስትራክሽን ውስጥ በፐርሶኔልነት ለ11 ወራት እንዳገለገለም ይናገራል። የቁምነገር መጽሔት ምክትልዋና አዘጋጅና ሴልስ ሁኖም ሰርቷል።
በዚህ ሁሉ የስራ ዙረት ውስጥ ልምዶችን ሲቃርም የሰነበተው እዝራ በየካቲት 2፣ 1996 ዓ.ም “ተወዳጅ” ብሎ የሰየማትን ጋዜጣውን ማሳተም ቻለ። ማስታወቂያዎችን ብቻ ይዛ የምትወጣው ይህች ጋዜጣ በነፃ ነበር የምትታደለው። ማስታወቂያ መፈለጉ አያስቸግርም ወይ ተብሎ ሲጠየቅ “ለጥረት ነው የተፈጠርኩት” ነው ምላሹ። ገቢዋ ከሽያጭ ሳይሆን ከማስታወቂያ አስነጋሪዎች ቢሆንም ከመጀመሪያ እትሟ ብቻ 10ሺ 100 በብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ያስታውሳል። በዚያው ሰሞን “አካፑልኮ ቤይ” የትርጉም መጽሐፉ ታትሞ ከ36ሺ ብር አጠቃላይ ትርፍ 30 በመቶውን እንደወሰደ አይዘነጋም።
ቀጥሎ ለቢዝነስ እየሸፈተ ያለ ልቡን ጠቅልሎ የወሰደ ድርጅትን በሞክሼ ጓደኛው እዝራ ገ/ሥላሴ አማካኝነት ተቀላቀለ። “ጎልድ ኩዌስት” የተባለው ይህ የሆንግ ኮንግ ድርጅት በኔትወርክ ማርኬቲንግ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ሲሆን መንግስት እስኪያግደው ድረስ በሀገራችን ተንቀሳቅሷል። እዚሁ ድርጅት ውስጥ እያለ በእንግሊዝኛ ብቻ የነበሩ የኔትወርክ ማርኬቲንግ ማንዋሎችን ወደ አማርኛ ሲመልስ ከቆየ በኋላ በመጽሐፍ መልክ አሳተመው። ከመጽሐፉ ህትመት ማግስት “ኢትዮ ቪዥን የችሎታ ማግኛ” የሚል የስልጠና ማዕከል ከፍቶ በርካቶችን ከችሎታቸው ጋር ማገናኘት ቻለ።
2000 ዓ.ም ጥር ወር ላይ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቶ ቢወዳደርም ተጠባባቂ ነበር መሆን የቻለው። ከወራቶች ቆይታ በኋላ ከፋና ተደውሎለት ከፍተኛ ሪፖርተር ሁኖ በ1415 ብር ተቀጠረ። የራሱ ትርፋማ ተቋም እንደነበረውና ማሰልጠኛ ከፍቶ ሰዎችን ከተቀጣሪነት ውጡ እያለ ሲመክር መክረሙን የሚያውቅ ግማሽ ልቡ ‘ለምን ትቀጠራለህ?’ ቢለውም ሌላኛው የልቡ ክፍል ደግሞ ‘ዓላማህን ይዘህ ተቀጥረህ ሞክረው’ ይለዋል፤ ሁለተኛውን ሰማና ተቀጠረ። ተቀጠረና 13 ከዓመታት ከ 5ወር ፋና ቤት መቆየት ቻለ።ከጥር 19 2019 በኋላ ግን ፋና እና እዝራ ተለያዩ፡፡
እዝራ በእነዚህ በ13 ዓመታት ውስጥ በህይወቱ ብዙ ለውጦች ተስተናግደዋል፡፡ በግንቦት 29 2001 የዘላለም አዳኙን ኢየሱስ ክርስቶስን ከተቀበለ በኋላ ሁሉ ነገር መልካም ሆነለት፡፡ እዝራም ሲጠየቅ ፈጣሪውን ከያዘ ጀምሮ ነገሮች መልካም እንደሆኑለት አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ ፋና ውስጥ ቀድመው ያልነበሩ ፎርማቶችን ጀምሯል፣ የሀገር ውስጥ ታሪኮች እንዲለመዱ አድርጓል፣ ቴሌቭዥኑ ሲጀመር ደግሞ በርከት ያሉ አጫጭር ታሪካዊ ተንቀሳቃሽ ምስሎችንና ዶክመንተሪዎችን ሰርቷል።ለብዙዎች የሬድዮ ኤዲቲንግ ስልጠና ሰጥቷል፡፡በስራው ተባባሪ ስለመሆኑም ይነገራል፡፡ እዝራ ታሪክ በሲዲን ከጀመረ አንስቶ ከ41 ጊዜ በላይ በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ ሚድያ ተጋብዞ ቃለ-ምልልስ ሰጥቷል፡፡
ለድሬ ቲዩብና ለመሳሰሉ የሚድያ ተቋማት ታሪካዊ ጽሑፎችን ማድረስ መጀመሩም ብዙ ትውውቆችን ፈጠረለት።
በ2008 ዓ.ም የግለሰቦችን ታሪክ በሲዲ የመሰነድ ሀሳቡን ሲያነሳ ብዙዎች እንደ እብደት ቢቆጥሩበትም፤ ያለውን ከማድረግ ሰንፎ አያውቅምና የተሾመ ገ/ማርያም ታሪክን በሲዲ በማውጣት ትርፋማ መሆን ቻለ። የጸሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ፣ የአርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ፣ የአማረ አረጋዊን ጨምሮ 44 ሲዲዎችን አሳተመ፡፡ ማማ በሰማይ፣ የኤርትራ ጉዳይ፣ ማህሌት፣ ምንትዋብና ሌሎች 10 የሚደርሱ መጽሐፍትንም በኦዲዮ አሳተመ። ከአካፑልኮ ቤይና ኔትወርክ ማርኬቲንግን በተጨማሪ ‘10 ነገሮች አለኦቲዝም’ እና ‘የአንኮበሩ ሰው በጄኔቭ’ የሚሉ ሌሎች መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል።ወደ ራስ መመለስ የሚለውንም መጽሀፍ ከወዳጁ ሲሳይ ገብረማርያም ጋር አውጥቷል፡፡
ፋና በቆየባቸው ጊዜያት 1476 ፕሮግራሞችን አየር ላይ ሲያውል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 67 ያህሉ ለቲቪ የተሰሩ ናቸው፡፡ ስራዎቹን ሰንዶ የማስቀመጥ ባህል ያለው እዝራ በየጊዜው ያለፉ ስራዎቹን የማየት ልምድ አለው፡፡
ይህ ሁሉ እንዲሆን ከፈጣሪ ቀጥሎ ዋጋ የምትከፍለው ባለቤቱ ድርሻዋ የጎላ መሆኑን ያወሳል። በመጀመሪያ ትውውቃቸው “አንቺን ነው የማገባው” ያለው ሰምሮለት በጥቅምት 7፣ 2002 ዓ.ም በመሰረተው ትዳር ክርስቲያን እዝራ እና ካሌብ እዝራ የተባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል።
ወደ ሰላሳ ለሚደርሱ ጸሐፍትና ሌሎች ባለሙያዎች የስራ እድል ፈጥሮ ትርፉን እያጋራ ይገኛል፤ አብረውት የሰሩት ሁሉ ስለእዝራ ሲናገሩ ባንድ ድምጽ ስለትጋቱና አንድ ነገር ከጀመረ ሳያሳካ አለመልቀቁን ያወራሉ። ታሪካቸውን ከሰነደላቸው ሰዎች አንዷ ዝናሽ ማሞ ስለእዝራ ስትናገር እዝራ ከጀመረ አይለቅም ደጋግሞ ለመደወል አይታክትም፤ ለማሳመን አይደክምም፤ ተከታትሎ ታሪኩን በእጁ ለማስገባት አይሰለችም፤ ምንም የሚፃፍ ታሪክ የለኝም፣ ስራ ይበዛብኛል፣ ጊዜ የለኝም የመሳሰሉት መልሶች ተስፋ አያስቆርጡትም። በጥበብ አስተናግዶ የማሳመን ተሰጥኦ አለው።” ትላለች።
“38 ዓመታት በትምህርት አብረን ነበርን” የሚለው አብሮ አደጉ ናይእግዚ ህሩይ፤ የእዝራ ንባቡ ላይ የሙጥኝ ማለት እንደእናቱ ሁሉ ይገርመው ነበር “እንደልጅም እንደጎረምሳም ሳይሆን ማሳለፉ ይገርመኛል” ይላል። የራሱን ስራዎች፣ ታሪካዊ ብሎ የሚያምንባቸውን ነገሮች እና በቴሌቭዥን ይተላለፉ የነበሩ ዜናዎች በካሴት ቀርጾ ማስቀመጡን እያስታወሰ “በወቅቱ የግሉ ዩቲዩብ ነበረው ማለት እንችላለን” ይላል። እዝራ ባለፉት 22 አመታት በሚድያው አለም በቆየባቸው አመታት የሚወደውን እና የሚችለውን ሲሰራ ኖሯል፡፡በአሁኑ ሰአት ታሪክን መሰነድ የሚለውን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ በሙሉ ሀይል እየሰራ ይገኛል፡፡ መዝገበ-አእምሮ በጠንካራ ሽፋን የምትወጣ መጽሀፍ ስትሆን እዝራ አቅሙ በፈቀደ መጠን ሀያሉ እግዚአብሄርን ይዞ ህልሙን ያሳካል፡፡
9ouk48ka3k3zfv2alj0i3v53vkywoir