ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.39.0-wmf.22
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
Module
Module talk
Gadget
Gadget talk
Gadget definition
Gadget definition talk
አቡነ ተክለ ሃይማኖት
0
14592
372196
366990
2022-07-31T21:52:34Z
ክርስቶስሰምራ
27288
wikitext
text/x-wiki
{{infobox|abovestyle=background:#FFBF00|above=አቡነ ተክለሃይማኖት|image=[[ስዕል:Abune tekle haimanot.jpg|250px|thumb|center|ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት]]|caption=|headerstyle=background:#7CB9E8|header1= የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጳጳስ|headerstyle=background:#FFBF00|header12=<span style="color:#FFBF00">
</span>|label1=|data1=|label2=ስም|data2=ፍስሐ ጽዮን በኋላ ተክለሃይማኖት |label3=የተወለዱበት ቀን|data3=[[ታኅሣሥ ፳፬]] ፲፩፻፺፯ |label4=የትውልድ ቦታ|data4=ቡልጋ|label5=የአባት ስም|data5=ቅዱስ ጸጋዘአብ|label6=የእናት ስም|data6=ቅድስት እግዚእ ኃርያ|label7=የአቡን ስያሜ|data7=በእስክንድሪያው አቡነ [[ቄርሎስ]]|label8=ያረፉበት|data8=[[ነሐሴ ፳፬]]<ref>ታሪካቸው በኢትዮጵያ [https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sammy.mycountryquotes ሥንክሳር] በነሐሴ ፳፬ የሰማዕታትና ቅዱሳን ታሪክ ውስጥ ይነበባል</ref>
|label9=ንግሥ|data9=[[ነሐሴ ፳፬]]|label10=የሚከበሩት|data10='''በ[http://www.ethiopianorthodox.org/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን]''' በ[[:en:Coptic Orthodox Church of Alexandria|ኮፕት ቤተክርስቲያን]] '''በ[http://www.eritreanorthodox.org/ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን]''' [https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sammy.mycountryquotes ሥንክሳር]
|captionstyle=|header5=}}
'''አቡነ ተክለ ሃይማኖት '''[[ቡልጋ]] ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ [[ቅዱስ ሚካኤል]] ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ [[መጋቢት|መጋቢት ፳፬]] ቀን ተፀንሰው፤ በ[[፲፩፻፺፯]] ዓ.ም [[ታኅሣሥ ፳፬]] ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው [[ሥላሴ]]ን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የ[[ጽዮን]] ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡
በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በአሥራ አምስት ዓመታቸው ከ[[እስክንድርያ]]ው ሊቀ [[ጳጳስ]] [[አቡነ ቄርሎስ]] /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ በዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ ዱር አደን ሄደው ሳለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን [[ኢየሱስ ክርስቶስ]] ተገልጾ ለ[[ኢትዮጵያ]]ውያን ክርስቲያኖች ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መረጣቸው። ስማቸውንም «ተክለ ኃሃይማኖት» አለው፡፡ ትርጓሜውም የኃይማኖት ፍሬ ማለት ነው፡፡
አባታችንም ሐዋርያዊ ጉዟቸውን ሲጀምሩ <blockquote>
«አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የ[[መንግሥተ ሰማያት]]ን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ . . . ደካማ ለሆንኩ ለእኔ ያለ አንተ የሚያፀናኝ የለም። ለምፍገመገም ለእኔ ያለ አንተ ደጋፊ የለኝም። ለወደቅሁ ለእኔ ያለአንተ የሚያነሳኝ የለም። ለአዘንኩ ለእኔ ያለአንተ የሚያረጋጋኝ የለም። ለድሀው ለእኔ ያለ አንተ መጠጊያ የለኝም፡፡»
/ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪ - ፫
</blockquote>ይህን ብለው ትሕትና በተሞላበትና በተሰበረ ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ከለመኑ በኋላ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሰዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ፀሐይ ተብለዋል፡፡
[[ቅዱስ ጳውሎስ]] በዕብራውያን ክታቡ ስለ ቅዱሳን መንፈሳዊ ተጋድሎ ሲገልፅ:-
*«እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሱ» /ዕብ. ምዕ ፲፩ ቁ ፴፫ / እንዳለ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም በመንፈሳዊ ተጋድሎ እንዲሁም በትህትና በተአምራት አላዊ የነበረውን ንጉሥ ሞቶሎሚን ወደ ክርስትና መልሰዋል፡፡
*«ጽድቅን አደረጉ» እንዳለው አባታችን ወንጌልን በተጋድሎ ሕይወታቸው ተርጉመዋል፡፡
*«የአንበሶችን አፍ ዘጉ» ምዕ ፲፩ ቁ ፴፫ /ምዕ ፲፩ ቁ ፴፬ /እንዳለው አባታችንም የአውሬውን ፥ የዘንዶውን ራስ ቀጥቅጠዋል።
*«ከሰይፍ ስለት አመለጡ» እንዳለው አባታችንም ሞቶሎሚ ከወረወረው ጦር በተአምራት ድነዋል፡፡
*«ከድካማቸው በረቱ» እንዳለው አባታችንም ያለ ዕረፍት በብዙ ተጋድሎ በጾምና በስግደት በብዙ መከራ በርትተዋል፡፡
ይህን ሁሉ ገድልና ትሩፋት እየፈጸሙ ዕረፍታቸውም በደረሰ ጊዜ ደቀመዝሙሮቻቸውን «ልጆቼ ሆይ ሁሉም መነኮስ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት አይደለም፤ ዓለምን በሚገባ የናቀ ብቻ ይገባል እንጂ መጀመሪያ የ[[እግዚአብሔር]]ን ጽድቁን ብቻ ፈልጉ፤ [[ጾም]]ና [[ጸሎት]]ን አዘውትሩ፤ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ እያሉ ይመክሯቸው ነበር. . .» በኋላም «ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ፤ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ፣ ከእውነተኛው ዳኛ ከጌታዬ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ?» እያሉ በፍጹም ትህትና እና በልዩ መንፈሳዊ ተመስጦ ይጸልዩ ነበር፡፡
በመጨረሻም አባታችን በ[[ነሐሴ ፳፬]] ቀን ዕረፍታቸው ሆነ። በዚህም መሠረት [[የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን|ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን]] ለእኚህ ዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው ለጻድቁ ተክለ ሃይማኖት በየዓመቱ በ[[ነሐሴ ፳፬]] ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡ እኛንም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡
በበለጠ ለማወቅ ስለ '''አባታችን''' ሰፊውን ገድላቸውን ማንበብ እጅግ አርጎ ይጠቅማል ።
'''''ደብረ''''' አሚን ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን
የምክሖ ደናግል ማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር
[[አዲስ አበባ]]
ስብሐት ለእግዚአብሔር
{{መዋቅር}}
=ምንጭ=
* http://eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=346&Itemid=26
* [http://st-takla.org St-Takla.org]
[[መደብ: ቡልጋ]]
[[መደብ:ተዋህዶ]]
[[መደብ:ተክለ ሃይማኖት]]
[[መደብ:የኢትዮጵያ ሰዎች]]
h5z0fjpt2md1j45f9pucsc68x68th1i
መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል
0
18358
372197
351563
2022-08-01T10:18:58Z
NisrTobiya
39276
wikitext
text/x-wiki
'''መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል''' በ[[ኢኦተቤ|ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን]] [[መጽሐፍ ቅዱስ]] ከብሉይ መጻሕፍት የሚፈረጅ ነው።
መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ከ[[ዲዩተሮካኖኒካል]] መጻሕፍት ተቆጥሮ የ[[ዕዝራ]] (ሱቱኤል) ትንቢት ነው።
==ትርጉም==
የተጻፈው በ[[ዕብራይስጥ]] ወይም በ[[አራማያ]] ሲሆን በኋላ (250 አክልበ.) ከ[[70 ሊቃውንት]] ብሉይ ኪዳን ጋር ወደ [[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪክ]] ተተረጎመ፤ ከዚሁም ግሪክ ወደ [[ሮማይስጥ]]። እንዲሁም የ[[ግዕዝ]] ትርጉም ከዕብራይስጡ ተሠራ። ከክርስቶስ ስቅለት ውዲህ ግን የአይሁድ ጉባኤ መጽሐፉን ስለ ከለከለው፣ የዕብራይስጥና የግሪክ ትርጉሞች በፍጹም ጠፍተዋል። መጽሐፉ ዛሬው የሚታወቀው ከሮማይስጥ፣ ከግዕዝ፣ ከ[[ሶርያ ቋንቋ]] (ከጥንቱ አራማያ የሚለይ)፣ ከ[[አረብኛ]]ና ከ[[አርሜንኛ]] ትርጉሞች ብቻ ነው።
==ይዘት==
[[ስዕል:3-apoch-1-cr.pdf|thumb|280px| የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [http://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B5%E1%8B%95%E1%88%8D:3-apoch-1-cr.pdf] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች ማንበብ ይችላላሉ|page=1]]
የመጽሐፉ ይዘት እንዲሁ ነው፦
*ምዕ. 1፦ ዕዝራ በ[[ባቢሎን ምርኮ]] ላይ አዝኖ ወደ [[እግዚአብሔር]] ሲጸለይ፣ ስለ [[አዳም]]፣ [[ኖኅ]]፣ [[አብርሃም]]፣ [[ዘጸአት]]፣ [[ዳዊት]]ና የምርኮው ታሪክ ይተርካል። [[ባቢሎን]] በዕውኑ ከ[[ጽዮን]] ይልቅ እንደ ጸደቀች እግዚአብሔርን ይጠይቀዋል፤ ጽዮንን በባቢሎን ስለሚቀጣት፣ ጽዮንም ስትሠቃይ ባቢሎንም ስትደሰት ነውና።
*ምዕ. 2፦ መልአኩ [[ዑርኤል]] ዕዝራን መልስ ለመስጠት ይላካል። የእግዜርን ፍርድ ለማወቅ አይችልም ይለዋል። ከዚሁ ዓለም መጨረሻ ቀጥሎ በእግዜር መንግሥት ጽድቅ ዋጋውን የሚገኘው ይሆናል። እዝራ ይህ ሁሉ መቼ ይሆንን ቢጠይቀው ዑርኤል የሞቱት ጻድቃን ደግሞ ይህን ለማወቅ ፈልገው ቁጥራቸው ሳይሞላ ግን አይሆንም ብሎ መለሰለት። ለሙታን ትንሳኤ መጠበቁ ለእርግዝና መውለድን እንደ መጠበቅ ይመስላል ብሎ ጨመረለት።
*ምዕ. 3፦ ዑርኤል የዓለሙን መጨረሻ ሁናቴና ትልልቆቹን ምልክቶች ለእዝራ ያስረዳዋል። ከዚህ በላይ ለመማር 7 ቀን መጾም አለበት። ከ7 ቀን በኋላ ዑርኤልን እንደገና ጠይቆት የእግዜር መንግሥት ቶሎ እንዲመጣ ሰዎች ሁሉ አንድላይ ለምን አልተፈጠሩም ይላል። መሬቲቱ የሰው ልጆች ሁሉ አንዴ መውለድ ከቶ አትችልም ብሎ ዑርኤል ይመልስለታል። እግዜር የሰው ልጅ ሆኖ ወደ ፍጥረቱ እንዴት እንደሚገባ መልአኩን ይጠይቀዋል።
*ምዕ. 4፦ በዑርኤል አማካኝነት እግዜር እንደ ሰው ልጅ ዓለሙን ለመጎብኝት በፍጥረት መጀመርያ እንዳቀደው ይገልጽለታል። እዝራ የዚህን አለም መጨረሻ ከእግዜር መንግሥት መጀመርያ ምን ይለየዋል ቢጠይቅ፣ [[ያዕቆብ]] ከ[[ኤሳው]] ቀጥሎ እንደ ወጣ ይከተላል የሚል መልስ ሰጠ። ስለዚያው ዘመን ሌላ ምልክት ሲጠይቀው፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በታላቅ ድምጽ እግዚአብሔር በዓለም የኖሩትን የተነሡትን ሙታን ለመፍረድ በምጽአት መምጣቱን አዋጃ። ከዚህም የተሻለ ኑሮና ከፍተኛ ሥልጣኔ በእግዜር መንግስት ይከተላል። ዕዝራም እንደገና 7 ቀን ይጾማል።
*ምዕ. 5፦ ዑርኤል ተመልሶ ጠባብ መግቢያዎች ያሉት ሀገር የሚለውን ምሳሌ ይነግረዋል። አዳም በገነት በደል ባደረገ ጊዜ፣ ወደ እግዜር መንግሥት የሚሔደው መንገድ ጠባብ ሆነ ይለዋል። እግዜርን የሚንቁት በ[[ገሐነም]] መጥፋታቸውን ይገልጻል፣ በጎ ሥራ የሚሠሩ ግን መንግሥት ይወርሳሉ። ኅሩያን ስለሚያውቁት ጊዜያዊ መሢሓዊ መንግሥት የሚለውንም ትምህርት ይገልጻል። መሢሓዊው ንጉሥ ከሞቱ በኋላ ሰው ሁሉ ይሞታል፤ ስው ሁሉ ከሞተ በኋላ ምድር ለ7 ቀን ዝም ትላለች። ከ7ቱም ቀን በኋላ፣ የሙታን ትንሳኤ፣ ዕለተ ደይን፣ ለክፋት መሪዎችም ቅጣት፣ ለጻድቃንም መንግሥተ ሠማያት፣ ሁሉም በየተራው ይዘረዝራሉ።
*ምዕ. 6፦ ዕዝራ ነፍስ ከሰውነት ከተለየ በኋላ ምን ይሆናል ብሎ ይጠይቀዋል። ዑርኤልም መልሶ እስከ ትንሳዔ ድረስ ሲጠብቁ፣ የሙታን ነፍሳት ለክፉዎች ስቃይ ለጻድቃንም ሞገስ እንደሚቀበሉ የ7ቱን ሥርዓት ምስጢር ይገልጻል። በዕለተ ደይን እያንዳንዱ ግለሰብ የግል ፍርዱን ይቀበላል። ሆኖም በሕይወታቸው ገና ሳሉ ንሥሐ ከገቡ ሀጢአትን ማሸነፍ እንደሚቻላቸው ያስተምራል።
*ምዕ. 7፦ ዕዝራ እግዚአብሔር ምሕረት እንዲያሳይ በለመነበት ጊዜ የእግዜር መልስ ሰው ሁሉ እንዲድን አይቻልም በማለት አስጠነቀቀው። ዘርን የሚዘራው ገበሬው ያለውን ምሳሌ ይነግረዋል። በእድሜያቸው እግዜርን ከቶ ስላልፈለጉት ስለ ሀጥአን ጥፋት እንዳይጨንቅበት እዝራን ይለዋል። ዕዝራ የእግዜር መንግሥት በመጨረሻ ዘመን መቅረቡን ስለሚያሳዩት ምልክቶች እንደገና ይጠይቃል።
*ምዕ. 8፦ እግዜር ዕዝራን እንደሚለው፣ ያስተማራቸውን የመጨረሻ ዘመን ምልክቶችን ሰው መፈልግ አለበት። የዝንጉ ሰዎችና የታማኝ ሰዎች እድሎች ምስጢር ደግሞ ይናገራል። ከዚያ ዕዝራ ለ7 ቀን በምድረ በዳ ፍራፍሬን ብቻ እየበላ እንዲቆይ አዘዘው። ከ7ቱ ቀንም በኋላ፣ በልጇ ላይ እያለቀሰች አንዲትን ሴት ያገኛል።
*ምዕ. 9፦ ዕዝራ ካለቀሰችው ሴት ጋር ለመወያየት ሲወድድ፣ ድንገት አገር ሆነችና መልአኩ ተመልሶ እርሷ በዚሁ አለም የእግዚአብሔር መንግሥት ሥር ምሳሌ ኢየሩሳሌም መሆኗን ይገልጽለታል።
[[ስዕል:Triple Eagle 2 Esdras.gif|280px|thumbnail|ባለ ሦስት ራስ አሞራ ከዕዝራ ራዕይ]]
*ምዕ. 10፣ 11፦ ነቢዩ ዳንኤል ቀድሞ እንዳየ ሁሉ፣ ዕዝራ የባቢሎን ተከታይ መንግሥታት መጨረሻ ሁናቴ የሚገልጽ ራዕይ ያያል። ነገር ግን ያልታወቁ አዛጋጆች አስተሳሰባቸውን ወደ ኢትዮጵያዊው ትርጉም አስገብተዋል። እነዚህ ምዕራፎች በሌሎቹ ልሳናት (ሮማይስጥ፣ ፅርዕ፤ ወዘተ.) ለጠፋው ዕብራይስጥ ቅጂ የተሻለውን ትርጉም እንዳላቸው ይሆናል። በቅንፍ ውስጥ ስለ [[አፊፋኖስ አንጥያኮስ]] የተጨመረው ቋንቋ መቸም አልተገኘበትም። አፊፋኖስ በ[[2ኛ መቶ ዘመን ዓክልበ.]] ስለ ኖረ እንጂ፤ ራዕዩ ግን በተለይ ስለዚሁ አለም መጨረሻ ጥፋት ዘመን ነው። [[ክርስቶስ]] ከአፊፋኖስ በኋላ ኖሮ የዳንኤል ራእይ ገና ወደፊት ነው በግልጽ ቢያስተምርም፣ አይሁዶች ግን ዳንኤል ስላለፈው አፊፋኖስ ትንቢት ተናገረ ብለው አስተማሩ። ይህ የአይሁዶች ትምህርት በቅንፉ ውስጥ መታየቱ ስንኳ ጥንታዊነቱን ይመስክራል። ቅንፉን ያስገባው የ[[ከስሙናይን ሥርወ መንግሥት]] ደጋፊ እንደ ነበር ይመስላል (11፡32 ይዩ)። የሚከተለው ከሮማይስጥ / ፅርዕ ትርጉሞች ይወሰዳል፦
:በሕልሙ ሳለ፤ ዕዝራ ባለ ሦስት ራስ [[ንሥር]] ወይም [[አሞራ]] ያያል። 12 ታላላቅ [[ክንፍ|ክንፎች]]ም አሉበት። እነዚህም 12 ታላላቅ ክንፎች እያንዳንዱ በየተራው ይገዛሉ። 2ኛው ታላቅ ክንፍ ከሌሎቹ ሁሉ የረዘመው ዘመነ መንግሥት ይቀበላል። ከርሱም ዘመን በኋላ ድምጽ ከንሥር ሰውነት ይናግራል። «ከዚህ በኋላ የመጡት ክንፎች እንደዛኛው ክንፍ ብዙ ዘመኖች እንዳይቀበሉ፣ ያኛው ክንፍ ከተቀበሉት ዘመኖች ግማሽ ይልቅ አይበልጡ» ይጮሃል። ከዚያ በኋላ የተረፉት ታላላቅ ክንፎች እስከ 12ኛው ታላቅ ክንፍ ድረስ ዘመኖቻቸውን ይጨርሳሉ። በመካከላቸው ደግሞ፣ መንግሥት ሊወድቅ እንደሚል ቢመስልም፣ ሆኖም መንግሥት የዛኔ አይወድቅም።
:ከ12ቱ ታላላቅ ክንፎች ቀጥሎ፣ 8 ትንንሽ ክንፎች ይነሣሉ። እነዚህ ሁሉ እስከ ንጉሥ ማዕረግ ድረስ አይደርሱም፤ አንዳንድ ምክትሎች ብቻ ናቸው። መጀመርያ ሁለት ከድንገት በዘመናቸው መካከል ይጠፋሉ። የሚከተሉ ሁለት ዘውድን በመጫን ፋንታ፡ ወደ ቀኝ ባለው ራስ ውስጥ መቆየት ይመርጣሉ። (እኚህ ሦስት ራሶች የንሥሩ መንግሥት ምንጮች ይባላሉ።) ከዚህ መንግሥታዊ ቀውስ የተነሣ፣ 4 ትንንሽ ክንፎች ይተርፋሉ። ከነዚህ አራት 1ኛው ትንሽ ክንፍ ለአጭር ዘመን ብቻ ይገዛል፤ 2ኛው ከዚያ ያነሰ እጅግ አጭር ዘመን ይቆያል። የተረፉት 2 ክንፎች ሊገዙ ሲሉ፤ ድንገት ከንሥሩ 3 ራሶች መካከለኛው ራስ ይነሣል፤ እርሱም ከሁሉ ጨካኝ የሆነ የአለም ንጉሥ ይሆናል። ከ[[ታላቁ መከራ]] አመታት በኋላ ግን በአልጋ ላይ ይሞታልና ወደ ቀኝ ራስ የሄዱት 2ቱ ትንንሽ ክንፎች የዛኔ ለጥቂት ዘመን ይገዛሉ። በነርሱ ዘመን ግን ብሔራዊ ጦርነት አለና አለም በእሳት ይጠፋል። በተጨማሪ [[አንበሳ]] ([[መሢኅ]]) ንሥሩን በፍጹም ይገስጻል።
*ምዕ. 12፦ ሰባት ቀን ካለፉ በኋላ ዕዝራ በሌላ ራዕይ አንድ ሰው ከባሕር ሲወጣ ያያል። ሠራዊቶች ሊዋጉ ሲሉ፣ ሰውዬው ተራራን ፈጥሮ ይቀመጥበታልና እሳት ከአፉ እስትንፋሽ ወጥቶ ያጠፋቸዋል። ከዚያ በኋላ ሌላ ሕዝብ ወደርሱ በሰላም ይመጣል። ከዚያም መልዓኩ የራዕዩን ፍች ይሰጠዋል። ይህ ምዕራፍ በአማርኛ ዲዩትሮካኖን እንደገና ከለሎቹ ትርጉሞች (ከጽርዕ ወዘተ.) ይለያል። በሌሎቹ ትርጉሞች ዘንድ፣ ይህ ራዕይ ስለመሢሁ መጨረሻ ምጽአት መሆኑ ግልጽ ነው። የተራራውም ትርጉም [[ደብረ ጽዮን]] ወይም የእግዚአብሔር መንግሥት ይባላል። አገሮች ሁሉ በጦርነት ተይዘው ዝም ብሎ በተራራ ላይ ይታያልና ካሸነፋቸው በኋላ ምድርን ለዘላለም ይገዛል። የአማርኛ ትርጉም ግን እንደገና በሌላ አስተያየት ተዛባ፤ በዚያ ውስጥ ተራራ መስቀል ሆኗል፤ ራዕዩም ስለዚሁ አለም መጨረሻ ቀን ሳይሆን፣ ስለ ክርስቶስ ስቅለት የሚተነብይ ሆኗል።
[[መደብ:አዋልድ መጻሕፍት]]
[[መደብ:ትንቢት]]
41rzbj6prc2twga2rfu2nnxrvnabijk