ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.39.0-wmf.25
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
Module
Module talk
Gadget
Gadget talk
Gadget definition
Gadget definition talk
ኔልሰን ማንዴላ
0
10473
372380
323040
2022-08-21T11:09:56Z
196.190.91.176
wikitext
text/x-wiki
{{}}[[ስዕል:Nelson Mandela-2008.jpg|thumb|right|ኔልሰን ማንዴላ (2008 እ.ኤ.አ.)]]
'''ኔልሰን ማንዴላ''' ዘረኛውን የ[[ደቡብ አፍሪካ]] [[መንግስት]] በመቃወማቸው ለ27 ዓመት እስር ቤት ማቀዋል። ከእስር ቤት እንደተለቀቁም የመጀመሪያዋ የነጻይቱ የደቡብ አፍሪካ [[ፕሬዚዳንት]] ሊሆኑ በቅተዋል።
ማን94 ዓመታቸውን ዛረ አከበሩ።
[[ስዕል:Nelson Mandela.jpg|thumb|left|ማንዴላ በ1993 እ.ኤ.አ.]]
{{መዋቅር-ሰዎች}}
[[መደብ:የአፍሪካ መሪዎች]]
[[መደብ:ደቡብ አፍሪካ]]
57ix9e43quxrtxiirh0z2mobnqe5p28
አሸንዳ
0
45825
372377
372371
2022-08-20T21:10:05Z
196.191.60.1
Added context
wikitext
text/x-wiki
'''አሸንዳ፡''' ወይም 'የሴቶች ቀን' በትግራይ እና አገው ሴቶች የሚከበር በአል ነው፣ በአራተኛው ክፍለዘመን በሳባውያን ህዝብ በአክሱም እንደተጀመረ የታሪክ አጥኝዋች ይናገራሉ። በዓሉ በወጣት ልጃገረድ ሴቶች በትግራይ ከሚከበሩ ታላቅ በአል አንዱም ነው፣ የትግራይ ሴቶች ይህን በአል ለማክበር በጉጉት ይጠብቃሉ። አሸንዳ ቃሉ [[ትግርኛ]] ሲሆን ትርጉሙም ከሳር ዓይነት የተሰጠ ነው፣ አንድ ነጭ ሽንኩርት ቅጠል እሚመስል ሰፊ እና እረዥም ተክል ነው። ይህ ተክል [[አሸንዳ]] ተብሎ ለሚታዎቀው በዓል መነሻ ሥምም ነው።
[[አሸንዳ]]፣ ከ[[ነሐሴ 16]] እስከ [[ነሐሴ 18]] ቀን ድረስ በትግራይ ይከበራል በአሉ በቅርብ ጊዜያት ተወዳጅነቱ በመጨመሩ በደቡብ ኤርትራ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋ፣ ኦሮሚያ እናም ሌሎች አካባቢዎች መከበር ጀምሯል
[[መደብ:የኢትዮጵያ በዓላት]]
2jdyzam33k2ikxrkdzauinxqx27p5en
ወለተ ጴጥሮስ
0
49928
372379
352601
2022-08-21T10:06:46Z
58.7.175.205
በገድለ ወለተ ጴጥሮስ አተረጓጎም ላይ ስለተነሳው ክርክር
wikitext
text/x-wiki
{{infobox|abovestyle=background:#FFBF00|above='''ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ'''|image=[[File:Portrait of Ethiopian Saint Walatta Petros, painted in 1721.tif|thumbnail|center|Portrait of Walatta Petros{{ref|a}}]]
|caption=|headerstyle=background:#FFBF00|header1=የእምነት ጥንካሬ ምሳሌ|headerstyle=background:#FFBF00|header8=<span style="color:#FFBF00">
</span>|label1=|data1=|label2=ስም|data2=ወለተ ጴጥሮስ |label3=የተወለደችው|data3=ሺ፭፻፹፬ |label4=የአባት ስም|data4=ባሕር አሰግድ|label5=የእናት ስም|data5=ክርስቶስ አዕበያ|label6=የምትከበረው|data6=[[ኅዳር ፲፯]] ቀን በመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን|label7=ያረፈችው|data7=ሺ፮፻፴፬|captionstyle=|header5=}}
'''ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ''' '''[http://www.ethiopianorthodox.org/ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን]''' ታዋቂ ከሆኑት አንስት ቅዱሳን አንድዋ ናት ። ገድልዋ በሺ፮፻፷፬ ዓ.ም.የተጻፈ ሲሆን የምትታወቀውም በተለይ የሮማን ካቶሊሲዝም በምድረ [[ኢትዮጵያ]] ላይ ለማስፈን በተደረገው ፍልሚያ ሕዝቡ ሃይማኖቱን እንዳይቀይር በማስተማር ፣ በየደብሩ እየደበቀች ከሞት ጥቃት በማዳን ፣ እንዲሁም የሃይማኖት ማኅበረሰቦችን በመመሥረት ፣ ተአምራቶችን በማድረግ ነው ።
ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ
አባቷ ባሕር አሰግድ እናቷ ደግሞ ክርስቶስ አዕበያ ይባላሉ። ትውልዷ ከዳሮ /ምስራቅ ኢትዮጵያ/ ወገን ነው። ወንድሞቿ ዮሐንስና ዘድንግል በንጉሥ ሱስንዮስ ጊዜ ታላላቅ ባለስልጣናት ነበሩ። እናት አባቷ በህግ በስርዓት ካሳደጓት በኋላ ሥዕለ ክርስቶስ የሚባል የ[[ዓፄ ሱሰኒዮስ]] የጦር አበጋዝ ቢትወደድ አግብታ ፫ ልጆች መውለድዋን ገድሏ ይናገራል። ይህ ቢትወደድ ይኖርበት የነበረው ግንብ ቤት ፍራሽ እስከ አሁን ድረስ በጋይንት ስማዳ ይታያል።
==ከሮማን ካቶሊሲዝም ጋር ትግሉዋ==
ወለተ ጴጥሮስ ከቢትወደድ ሥዕለ ክርስቶስ ጋር በሰላም በመኖር ላይ እያለች ንጉሡ '''[[ዓፄ ሱሰኒዮስ]]''' የተዋሕዶ ሃይማኖቱን ቀይሮ በሮማውያን መምህራን በመሰበክ ካቶሊክነትን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ህዝብም ካቶሊክ እንዲሆን ዐወጀ ። <ref>ነገሩ [[ግራኝ አህመድ]] በኢትዮያ ሕዝብና ሃይማኖት ላይ አስከፊ ጦርነት በማድረጉ (ዓፄ '''[[ልብነ ድንግል]]ን''' እስከ መግደል ድረስ) ከአውሮፓ ክርስቲያን አገሮች [[ኢትዮጵያ]] እርዳታ በጠየቀችው መሠረት የፖርቱጋል መንግሥት ፈቃደኛ ሆኖ በመተባበር ግራኝ አህመድ ሊሸነፍ ቻለ ። ይህም ያስከተለው የፖርቱጋል መንግሥት ውሮታውን ሲፈልግ በወቅቱ የነበሩትን ንጉሥ ማለት ዓፄ ሶስንዮስን በመስበክ ሃይማኖታቸውን ቀይረው ካቶሊክ እንዲሆኑ አደረጉዋቸው ([[እርምጃችንና የኢትዮጵያ ታሪክ ቀ.ኃ.ሥ.]])። እዚህ ላይ የመንግሥት ዋና አጀንዳ ሃይማኖትና ድምበር እንደሆነ ማስተዋል ይገባል ። በተጨማሪ [[የኢትዮጵያና አዳል ጦርነት|ይህን ይመልከቱ]] ።</ref> በዚህ ዐዋጅ የተነሣ በንጉሡ ደጋፊዎችና የቀደመ ሃይማኖታችንን አንለቅም ባሉት እውነተኛ የተዋህዶ ምዕመናን መካከል ታላቅ ጠብ ሆነ።
የንጉሡ ሠራዊትም በተዋሕዶ ምእመናን ላይ ዘመቱ። ቢትወደድ ሥዕለ ክርስቶስ ከዘመቻ ሲመለስ የጳጳሱን የ[[አቡነ ስምዖን]]ን ልብስ እንደግዳይ ሰለባ ለንጉሡ ይዞለት መጣ። ይህንን የሃይማኖቷን መናቅ የአባቶቿን መደፈር የተመለከተችው ወለተ ጴጥሮስ እንደዚህ ካለው ከሀዲ ጋር በአንድ ቤት አብሮ መኖር አያስፈልግም ብላ ቆረጠች። ከዚህም በኋላ ከቤቱ የምትወጣበትን ዘዴ ያለ እረፍት ማሰላሰል ጀመረች:: ከዚያም ወደ ገዳም ለመግባት እንዲረዷት ከጣና መነኮሳት ጋር መላላክ ጀመረች። የ[[ጣና ቂርቆስ]] ገዳም አበምኔት አባ ፈትለ ሥላሴም ወለተ ጴጥሮስን ይዘዋት እንዲመጡ ሁለት መነኮሳትን ላኩ። በዚያ ጊዜ ልጆቿ ሁሉ ሞተውባት ነበር። ወለተ ጴጥሮስ ከመነኮሳቱ ጋር መጥፋቷን ያወቀው ቢትወደድ ሥዕለ ክርስቶስ ይዘው ያመጡለት ዘንድ አያሌ ሠራዊት ከኋላዋ ሰደደ። ነገር ግን ወለተ ጴጥሮስና ሁለቱ መነኮሳት '''በ[[እግዚአብሔር]]''' ረዳትነት በዱር ውስጥ ተሰውረውባቸዉ ሊያገኟቸው አልቻሉም። ይህ ተሰውረውበት የነበረዉ ቦታ እስከዛሬ ድረስ [[ሳጋ ወለተ ጴጥሮስ]] ይባላል። በኋላ ዘመንም በስሟ ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶበታል።
== ምንኩስናዋና ተጋድሎዋ==
ከዚህ በኋላ ወደ [[ደብረ ዕንቁ ገዳም]] ገብታ ስርዓተ ምንኩስናን ተምራ መነኮሰች። ታላቁ ገድሏ የተጀመረውም ከዚህ በኋላ ነው። ወለተ ጴጥሮስ ከምንኩስናዋ በኋላ በመላ ሀገሪቱ እየተዘዋወረች ሕዝቡ በ[[ተዋህዶ]] እምነት እንዲፀና፣ በ[[ጸሎተ ቅዳሴ]]ም ጊዜ ሃይማኖቱን የለወጠው የንጉሡ የሱስንዮስ ስም እንዳይጠራ ትመክር ጀመር። ብዙ ሰዎችም በምክሯ ተስበው በሃይማኖታቸው እየጸኑ [[ሰማዕት]]ነትን መቀበል ያዙ።
ይህንን የወለተ ጴጥሮስን ተጋድሎ የሰማው ንጉሥ ሱስንዮስ ተይዛ ለፍርድ ትቀርብ ዘንድ ብዙ ወታደሮች በየአካባቢው አሰማራ። በመጨረሻም በሰራዊቱ ተይዛ በሱስንዮስ ፊት ቀረበች። መሳፍንቱ መኳንንቱና ለእንጀራቸው ሲሉ ሃይማኖታቸውን የለወጡ ሊቃውንት በተሰበሰቡበት ትመረመር ጀመር።
== በቁም እሥር ላይ==
ከሳሽዋ " ንጉሡን ካድሽ፣ እግዚአብሔርን ካድሽ፣ ትዕዛዙን እምቢ አልሽ፣ ሃይማኖቱን ዘለፍሽ፣ሌሎች ሰዎችም ሃይማኖቱን እንዳይቀበሉ ልባቸውን አሻከርሽ" ሲል ከሰሳት። ወለተ ጴጥሮስ ግን እንደ አምላኳ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በከሳሾቿ ፊት ዝም አለች። ንጉሡም ርቃ እንዳትሄድ ነገር ግን ከቅርብ ዘመዶቿ ጋር እንድትኖር / የቁም እስር/ ፈረደባት።
[[ሃይማኖት]] ተንቃ፣ [[ቤተ ክርስቲያን]] ተዋርዳ የመናፍቃን መጨዋቻ ስትሆን ማየት የሃይማኖት ፍቅርዋ ያላስቻላት ወለተ ጴጥሮስ በግዞት መልክ ከተቀመጠችበት ቦታ ጠፍታ ዘጌ ገዳም ገባች። አብርዋትም [[ወለተ ጳውሎስ]]ና [[እህተ ክርስቶስ]] የተባሉ እናቶች ነበሩ። በዚያም በገዳሙ የነበሩ መነኮሳት እና የአካባቢው ምእመናን በ[[ተዋህዶ]] ሃይማኖታቸው እንዲጸኑ እየመከረች ጥቂት እንደቆየች የሚያሳጧትና የሚከሷት ስለበዙ ቦታውን ለቃ ወደ [[ዋልድባ]] ገዳም ገባች። ዋልድባ ገብታ ሱባዔዋን ከፈጸመች በኋላ በገዳሙ የነበሩትን አባቶችና እናቶች በእምነታቸው ጸንተው እንዲቆዩ ትመክራቸው ጀመር።
አጼ ሱስንዮስ የወለተ ጴጥሮስን ተጋድሎ፣ መነኮሳትንና ምእመናንን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ፣ የካዱትም ከክህደታቸው እንዲመለሱ ማድረጓን ሲረዳ ብዙ ወታደሮችን ይልክባት ነበር። በዋልድባ እያለችም የንጉሡ ሰራዊት ሊያስኖሯት ስላልቻሉ ወደ ጸለምት አመራች። በጸለምት የወለተ ጴጥሮስ ትምህርት እንደ ሰደድ እሳት ተስፋፋ። ምእመናን እየውደዷትና እየተቀበሏት እራሳቸውን ለሰማዕትነት አዘጋጁ። ይህንን የሰማው ሱስንዮስ ይቺ ሴት እኔ ብተዋት እርሷ አልተወችኝም፣ አለና የጸለምቱን ገዥ ባላምባራስ ፊላታዎስን ወለተ ጴጥሮስን ይዞ እንዲያመጣለት አዘዘው።
ወለተ ጴጥሮስ በጸለምቱ ገዥ ተይዛ ወደ ሱስንዮስ መጣች። አስቀድመው ሃይማኖቷን እንድትለውጥ ሊያግባቧት ሞከሩ። እርሷ ግን ጸናች። ሦስት የ[[ካቶሊክ]] ቀሳውስት መጥተው ስለሃይማኖትዋ ተከራከሯት። ወለተ ጴጥሮስ ግን የሚገባቸውን መልስ ሰጥታ አሳፈረቻቸው። በየቀኑ የካቶሊክ ቀሳውስት ሃይማኖቷን ትታ ካቶሊክ እንድትሆን በምክርም በትምህርትም ለማታለል ሞከሩ። ይሁን እንጂ ወለተ ጴጥሮስ በተዋሕዶ ዓለት ላይ ተመስርታ ነበርና ፍንክች አላለችም፡፡
== ሃይማኖቱዋን ለማስቀየር==
በመጨረሻ አንዱ የካቶሊክ ቄስ "እርሷን እቀይራለሁ ማለት በድንጋይ ላይ ውኃ ማፍሰስ ነው" ሲል ለንጉሡ አመለከተ። ሱስንዮስ ይህንን ሲሰማ ሊገላት ቆረጠ። አማካሪዎቹ ግን "አሁን እርስዋን ብትገል ህዝቡ ሁሉ በሞቷ ይተባበራል፣ ስለ ሃይማኖቱ እንደ እርሱዋ መስዋዕት ይሆናል። ደግሞ ሰው ሁሉ ካለቀ በማን ላይ ትነግሣለህ? ይልቅስ ታስራ ትቀመጥ።" ብለው መከሩት። ንጉሡም ገርበል ወደተባለው በርሃ ሊልካት ወሰነ።
መልክዐ ክርስቶስ የተባለው ዋነኛ የካቶሊኮች አቀንቃኝ ወደ ሱስንዮስ ፊት ቀርቦ "ንጉሥ ሆይ በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ ክረምቱ እስኪያልፍ ድረስ ከእኔ ጋር ትክረም። እኔ እመክራታለሁ። የፈረንጆቹ መምህር አልፎኑስም ሁልጊዜ መጽሐፉን ያሰማታል። ይህ ሁሉ ተደርጎ አሻፈረኝ ካለች ያንጊዜ ግዞት ትልካታለህ" ሲል ለመነው ንጉሡም ተስማማ።
መልክዐ ክርስቶስ ወለተ ጴጥሮስን የካቶሊኮች ጳጳስ ወደሚኖርበት ጎንደር አዘዞ ወሰዳት። ሁለቱ ተከታዮቿ ወለተ ክርስቶስ እና እኅተ ክርስቶስ አብረዋት ሰነበቱ። ወለተ ጳውሎስ ዘጌ ቀርታለች። አልፎኑስሜንዴዝም ዘወትር እየሄደ የልዮንን ክህደት ያስተምራት ነበር። ንጉሡም የወለተ ጴጥሮስን ወደ ካቶሊክነት መቀየር በየጊዜው ይጠይቅ ነበር፣ የሚያገኘው መልስ ግን ሁልጊዜ አንድ ነው "በፍጹም"። ክረምቱ አለፈ። ኅዳርም ታጠነ። ወለተ ጴጥሮስም በትምህርትም በማባበልም ከተዋሕዶ ሃይማኖቷ ንቅንቅ አልል አለች። ስለዚህ ወደ ስደት ቦታዋ ገርበል በርሃ በሱስንዮስ ወታደሮች ተጋዘች። ወለተ ጴጥሮስ ብቻዋን ገርበል ወረደች። በእርጅና ላይ ያለችው እናቷ ይህንን ስትሰማ አንዲት አገልጋይ ላከችላት። ቆራጧ ተከታይዋ እኅተ ክርስቶስም ወዲያው ወደ እርሷ መጣች።
==በገርበል በረሃ==
[[ገርበል በርሃ]] ለ፫ አመት ስትኖር ብዙ ጊዜ ትታመም ነበር። ስለዚህ መከራውን ሁሉ ስለሃይማኖቷ ቻለችው። ከግዞቱ ከተፈታች በኋላ ደንቢያ ውስጥ ጫንቃ በተባለ ቦታ ተቀመጠች። በስደቱ ምክንያት ቆባቸውን አውልቀው የነበሩ አያሌ መነኮሳትም ስደቱ መለስ ሲል በዙሪያዋ ተሰበሰቡ: በገዳማቸዉም ፀንተዉ እንዲኖሩ ትመክራቸዉ ነበር።በኋላም ወደ ጣና ቂርቆስ ተጉዛለች።ከዚያም ምጽሊ ወደተባለው ደሴት ሄዳ በዙርያዋ አያሌ መነኮሳትን ሰብስባ ለሃይማኖታቸዉ እንዲጋደሉ መከረቻቸዉ።። ነገር ግን መከራ ያልተለያት ወለተ ጴጥሮስ መዝራዕተ ክርስቶስ የተባለው ሰው ካቶሊክ ያልሆኑ ምእመናንን አስገድዶ የሚያስጠምቅበትን ደብዳቤ ይዞ ወደ አካባቢው መምጣቱን ስለሰማች መነኮሳቱን መክራና አስተምራ ወደ እየበረሃው ከሰደደች በኋላ እርሷም እንደገና ስደት ጀመረች። ተመልሳ ወደ ምጽሊ የመጣችው አገር ሲረጋጋ በ፵፱ አመቷ ነው።
==ከስደት መልስ==
ከስደት ስትመለስ መኖርያዋ ያደረገችው [[መንዞ]] የተባለውን ቦታ ነው። በዚያ ቦታ ላይ በጸሎትና በስግደት ተጠምዳ ኖረች። በምጽሊ ገዳም አብሯት የነበረው የ[[:en:Debre Mariam|ደብረ ማርያም]] አበምኔት አባ ጸጋ ክርስቶስም መጽሐፈ ሐዊን ይተረጉምላት ነበር።
አጼ ሱስንዮስ ምላሱ ተጎልጉሎ ከ[[እግዚአብሔር]] ቅጣቱን ሲቀበልና የተዋሕዶ ሃይማኖት ስትመለስ [[አቡነ ማርቆስ]] ግብጻዊው ጵጵስና ተሹመው ወደ [[ኢትዮጵያ]] ሲመጡ ከመንገድ ላይ ጠብቃ ቡራኬ ተቀበለች። እርሳቸውም ሊቀ ዲያቆናት አድርገው ሾሟት። ስለሃይማኖቷ ብላ ከባሏ መለየትዋ እና መከራ መቀበሏ እስከ [[ግብጽ]] ድረስ መሰማቱን ጳጳሱ ነግረዋታል።
==የመጨረሻ ሕይወት ታሪኳ==
ከዚያም በመንዞ ገዳም አቋቁማ በተጋድሎ ተቀመጠች። ያቋቋመችው ገዳም የወንዶችም የሴቶችም ነበር።
የተዋሕዶ ሃይማኖት በዐዋጅ ከተመለሰችና [[አፄ ፋሲል]] ከነገሠ በኋላ ንጉሡን ለማግኘትና ወንድሞቿንና ዘመዶቿን ለማየት ወደ [[ጎንደር]] መጣች። ንጉሡም በታላቅ ክብር ተቀበላት። በየቀኑም ሳያያት አይውልም ነበር። ወደ እርስዋ ሲገባም አደግድጎ ነበር። ይህም ስለሃይማኖትዋ ጽናትና ስለቅድስናዋ ክብር ነው።
ወለተ ጴጥሮስ በተጋድሎና በምንኩስና ኖራ በ፶ አመቷ በቆረቆረችው ገዳም ዐረፈች። መታሰቢያዋም ኅዳር ፲፯ ቀን ይከበራል። የተከታይዋ [[ወለተ ክርስቶስ]] በዓል ደግሞ ኅዳር ፯ ቀን ይውላል። በሃይማኖት ጸንቶ መጋደል ወንድ ሴት አይልም። ቤተ ክርስቲያናችን እንደነ ወለተ ጴጥሮስ ያሉ አያሌ ልጆች አሏት። የዛሬዎቹ እህቶችና እናቶችም በምግባር ታንፆ በሃይማኖት ጸንቶ በእምነት መጋደልን ከእነዚህ እናቶች ሊቀስሙ ይገባል። የእናታችን የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ እና የተከታዮቿ ረድ ኤትና አማላጅነት አይለየን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
<references />'''በገድለ ወለተ ጴጥሮስ ላይ የተነሳ ክርክር'''
ከፕሪንስተን ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር ዌንዲ ቤልቸር የምትባል አሜሪካዊት፣ ማይክል ክላይነር ከሚባል ጀርመናዊ ጋር በመተባበር ገድለ ወለተ ጴጥሮስን The Life and Struggles of Our Mother Walatta Petros: A Seventeenth-Century African Biography of an Ethiopian Woman በሚል ርዕስ ተርጉማዋለች፡፡ ይህ የትርጉም ስራ የኢትዮጵያ የግእዝ ምሁራንን ወደጎን በመተው የተርጓሚወቹን በተለይም የቤልቸርን የግል ሃሳብ ያንጸባረቀ ነበር። በተለይም ዋናዋ ተርጓሚ ፕሮፌሰር ቤልቸር የግእዝ ቋንቋ እውቀት ፈጽሞ የሌላትና የምትተረጉመውን ጽሁፍማንበብ የማትችል ምሁር ነች።
በአውስትራሊያ አስተማሪ የሆነው ዶክተር ይርጋ ገላው ወልደየስ ይህንን ትርጉም የተዛባና ሆን ተብሎ የኢትዮጵያን ታሪክና ቤተክርስቲያን ለማራከስ የተጻፈ ነው በሚል [https://www.hagerbekelethiopia.org/_files/ugd/e058e2_7fee34c4a96f403a9255e6eac05ab1cc.pdf Colonial Rewriting of African History: Misinterpretations and Distortions in Belcher and Kleiner’s Life and Struggles of Walatta Petros] በሚል ርዕስ 95 ገጽ ያለው ጆርናል አሳትሟል፡፡
በተጨማሪም ከአርባ በላይ አለማቀፍ ምሁራን የፕሮፌሰር ዌንዲ ቤልቸር ስራ የምሁርነት ደረጃን የጠበቀ ስላልሆነ እንዲሰበሰብና በቀጣይነት በታምረ ማርያምና በክብረነገስት ላይ የጀመረችው ተመሳሳይ የማያነቡትን-መተርጎም ስራ እንዲቆም [https://www.sbs.com.au/language/amharic/am/article/open-letter-to-princeton-university-black-history-matters-too/r5uuwk3w1 በግልጽ ደብዳቤ] ጠይቀዋል።
7l6uyo0j0rwu11ti9hn3fdfb4dejgyb
ሀጫሉ ሁንዴሳ
0
52662
372378
2022-08-21T10:00:32Z
1901sams
40424
Created by translating the page "[[:en:Special:Redirect/revision/1105624221|Hachalu Hundessa]]"
wikitext
text/x-wiki
{| class="infobox biography vcard"
! colspan="2" class="infobox-above" style="font-size:125%;" |ሀጫሉ ሁንዴሳ
|-
| colspan="2" class="infobox-image" |[[File:Hachalu_Hundessa_in_2018_(cropped).png|250x250px]]<div class="infobox-caption">ሃጫሉ በ 2018</div>
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ተወለደ
| class="infobox-data" |1986 አምቦ ፣ኢትዮጵያ
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ሞተ
| class="infobox-data" |በ(33-34)እድሜ አ አ ኢትዮጵያ
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ሞቱ ምክንያት
| class="infobox-data" |[[Gunshot wounds|ጥይት ቆስሎ]]
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ሙያ
| class="infobox-data role" |ዘፋኝና -ገጣሚ
|-
! class="infobox-label" scope="row" |የኖረው
| class="infobox-data" |2008–2020
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ባልቤት
| class="infobox-data" |ፋንቱ ደምሴ
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ልጅ
| class="infobox-data" |2
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ቤተሰብ
| class="infobox-data" |<div class="plainlist ">
* ጉደቱ ሆራ
* ሁንዴሳ ቦንሳ
</div>
|-
| colspan="2" class="infobox-full-data" |ሙዚቃ ህይወት
|-
! class="infobox-label" scope="row" |ምድብ
| class="infobox-data" |ኢትዮጵያዊ ድምጻዊ
|-
! class="infobox-label" scope="row" |መሳሪያ
| class="infobox-data note" |<div class="hlist hlist-separated">
* በድምጽ
</div>
|-
! class="infobox-label" scope="row" |አሳታሚ
| class="infobox-data" |አፎምያ ስቶዲዮ
|-
| colspan="2" |
<div class="shortdescription nomobile noexcerpt noprint searchaux" style="display:none">Musical artist</div>
|}
[[Category:Articles with hCards]]
'''ሀጫሉ ሁንዴሳ''' ( ; አማርኛ ;ሀጫሉ ሁንዴሳ<sub>፣</sub> 1986 <ref name="BBC2">{{Cite news|title=The singer whose murder sparked Ethiopia protests|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53238206|work=BBC News|date=2 July 2020|access-date=13 July 2020}}</ref> - 29 ሰኔ 2020) ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ፣ ዘፋኝ እና የሲቪል መብት ተሟጋች ነበር። ሁንዴሳ እ.ኤ.አ. በ2014-2016 በተካሄደው የኦሮሞ ተቃውሞ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ።[[ዐቢይ አህመድ|አብይ አህመድ]] [[የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት|የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ]] እና [[የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር|የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር]] በኃላፊነት <ref>{{Citation|url=https://global.chinadaily.com.cn/a/202007/03/WS5efe91dba310834817256fd7.html|title=Ethiopian unrest fans destruction of Hailie Selassie statue in London|access-date=July 3, 2020}}</ref> እና በመቀጠልም በ2018 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ አድርጓል ።
== የግል ሕይወት ==
ሀጫሉ ሁንዴሳ [[ኦሮሚያ ክልል|በኦሮሚያ ክልል]] [[አምቦ]] ከአባታቸው ከጉዳቱ ሆራ እና <ref name="BBC2">{{Cite news|title=The singer whose murder sparked Ethiopia protests|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53238206|work=BBC News|date=2 July 2020|access-date=13 July 2020}}</ref> ቦንሳ በ1986 ተወለደ። [[ኦሮሞ|የኦሮሞ]] ወላጆች ልጅ <ref>{{Cite news|title=Ethiopian singer buried amid ethnic unrest|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53262998|access-date=2020-07-21}}</ref> ሁንዴሳ በትምህርት ቤት ክበብ ውስጥ እየዘፈነ ያደገው ከብት በመጠበቅ ነው። <ref name="LNSA">{{Cite news|title=Hachalu Hundessa Death, Dead - Hachalu Hundessa Died, Killed, Wife, Wiki, Bio|url=https://www.latestnewssouthafrica.com/2020/06/30/oromo-music-star-hachalu-hundessa-reportedly-killed/|access-date=30 June 2020}}</ref> እ.ኤ.አ. በ 2003 ፣ በ 17 ዓመቱ ፣ በተቃውሞ ሰልፎች ውስጥ ተሳትፏል ተብሎ ታሰረ። <ref name="BBC">{{Cite news|title=Deadly protests erupt after Ethiopian singer killed|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53233531|access-date=30 June 2020}}</ref> በቀርጫሌ አምቦ ለአምስት ዓመታት ታስሮ በ2008 <ref name="LNSA" /> ሁለት ሴት ልጆች ያሉት ፋንቱ ደምሴን አግብቷል። <ref>{{Citation|title=Hachalu Hundessa - Ethiopia's murdered musician who sang for freedom|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53238206|access-date=July 2, 2020}}</ref>
== ሙያ ==
ሁንዴሳ እስር ቤት እያለ የመጀመርያውን አልበሙን ግጥሞች ያቀናበረ እና የጻፈው። አልበሙ, ''Sanyii Mootii'', በ 2009 ተለቀቀ. እ.ኤ.አ. በ 2013 [[አሜሪካ|ዩናይትድ ስቴትስን]] ተዘዋውሮ ሁለተኛውን አልበሙን አወጣ, ''Waa'ee Keenyaa'', ይህም በአማዞን ሙዚቃ ላይ #1 በጣም የተሸጠው የአፍሪካ የሙዚቃ አልበም ነበር። <ref name="LNSA">{{Cite news|title=Hachalu Hundessa Death, Dead - Hachalu Hundessa Died, Killed, Wife, Wiki, Bio|url=https://www.latestnewssouthafrica.com/2020/06/30/oromo-music-star-hachalu-hundessa-reportedly-killed/|access-date=30 June 2020}}</ref> ሁንዴሳ ከመሞቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በሶስተኛው አልበሙ ''ማዓል ማሊሳ'' ላይ እየሰራ መሆኑን ገልጿል። እ.ኤ.አ. በ 2021 አልበሙ የተለቀቀው በሞተበት አመታዊ በዓል ላይ ነው። <ref name="Maal">{{Cite news|url=https://www.bbc.com/afaanoromoo/oduu-57611399.amp|title=Albamiin Haacaaluu Hundeessaa walleewwan 14 qabu torban dhufu akka gadhiifamu maatiin himan}}</ref>
የሃንዴሳ የተቃውሞ መዝሙሮች የኦሮሞን [[ኦሮሞ|ህዝብ]] አንድ አድርገው ጭቆናን እንዲቋቋሙ አበረታተዋል። በ2014–2016 በኦሮሞ ተቃውሞ ወቅት የእሱ ዘፈኖች ከፀረ-መንግስት ተቃውሞ ጋር በቅርብ የተቆራኙ ናቸው። “ማላን ጅራ” (የኔ ህልውና) የኦሮሞ ተወላጆችን [[አዲስ አበባ|ከአዲስ አበባ]] መፈናቀል ያሳስበዋል። ነጠላ ዜማው በሰኔ 2015 ከተለቀቀ ከወራት በኋላ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በመላው [[ኦሮሚያ ክልል|የኦሮሚያ ክልል]] ተቃውሞ ተካሄዷል። ዘፈኑ ለተቃዋሚዎች መዝሙር ሆነ እንዲሁም በብዛት ከታዩት የኦሮምኛ የሙዚቃ ቪዲዮች አንዱ ሆኗል። <ref>{{Cite news|author=Ademo|title=Oromo Person of The Year 2017: Haacaaluu Hundeessaa|url=https://www.opride.com/longform/opride-oromo-person-year-2017-haacaaluu-hundeessaa/|work=OPride|date=31 December 2017|access-date=30 June 2020}}</ref>
በዲሴምበር 2017 ሁንዴሳ በሶማሌ ክልል ብሔር ተኮር ጥቃት ለተፈናቀሉ 700,000 ኦሮሞዎች ገንዘብ በማሰባሰብ በአዲስ አበባ በተዘጋጀ ኮንሰርት ላይ ዘፈነ። ኮንሰርቱ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በቀጥታ ተላልፏል። <ref>{{Cite news|title="We are here": The soundtrack to the Oromo revolution gripping Ethiopia|url=https://africanarguments.org/2018/03/30/we-are-here-the-soundtrack-to-the-oromo-revolution-gripping-ethiopia/|work=African Arguments|date=30 March 2018|access-date=30 June 2020}}</ref>
የሃንዴሳ ዘፈኖች የኦሮሞን ተስፋ እና ብስጭት ያዙ። መምህር አወል አሎ እንዳሉት " ሀጫሉ የኦሮሞ አብዮት ማጀቢያ፣የግጥም አዋቂ እና የኦሮሞን ህዝብ ተስፋ እና ምኞት ያንጸባረቀ አክቲቪስት ነበር።" <ref name="NYT">{{Cite news|title=Hachalu Hundessa, Ethiopian Singer and Activist, Is Shot Dead|url=https://www.nytimes.com/2020/06/30/world/africa/ethiopia-hachalu-hundessa-dead.html|work=The New York Times|date=30 June 2020|access-date=30 June 2020}}</ref>
== ግድያ እና በኋላ ==
ሁንዴሳ እ.ኤ.አ. ሰኔ 29 ቀን 2020 ምሽት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ዳርቻ በሚገኘው ገላን ከተማ በሚገኘው ገላን ኮንዶሚኒየም በጥይት ተመትቷል። <ref>{{Citation|title=Media implicated in violence following Hachalu's death|url=https://www.thereporterethiopia.com/article/media-implicated-violence-following-hachalus-death?__cf_chl_jschl_tk__=pmd_daca0338f5f323d4a7bbcc857c882b6c58df0830-1627973068-0-gqNtZGzNAiKjcnBszQeO}}</ref> <ref name="BBC">{{Cite news|title=Deadly protests erupt after Ethiopian singer killed|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53233531|access-date=30 June 2020}}</ref> ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስዶ ህይወቱ አልፏል። <ref name="LNSA">{{Cite news|title=Hachalu Hundessa Death, Dead - Hachalu Hundessa Died, Killed, Wife, Wiki, Bio|url=https://www.latestnewssouthafrica.com/2020/06/30/oromo-music-star-hachalu-hundessa-reportedly-killed/|access-date=30 June 2020}}</ref> ፖሊሶች ህዝቡን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ሲጠቀሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሃዘንተኞች በሆስፒታሉ ተሰበሰቡ። በዘፋኙ የቀብር ስነስርአት ላይ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመተው 7 ሰዎች ቆስለዋል። በአምቦ የሚገኘው የተቃዋሚው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባል ፋይንባር ኡማ የጸጥታ ሃይሎች በጥይት መተኮሳቸውን “ሰዎች ወደ ቀብር ሥነ ሥርዓቱ እንዳይሄዱ ተደርገዋል” ሲሉ ገልጸዋል ። <ref>{{Cite web|title=Police block mourners from Ethiopian singer Hachalu Hundessa's funeral|url=https://www.trtworld.com/africa/police-block-mourners-from-ethiopian-singer-hachalu-hundessa-s-funeral-37831|language=tr-TR}}</ref> የሃንዴሳ ሬሳ ሣጥን [[አምቦ|በአምቦ]] ስታዲየም ውስጥ በጥቁር መኪና ከነሐስ ባንድ እና በፈረስ ፈረሰኞች ታጅቦ ገባ። በኋላም በቤተሰቡ ፍላጎት መሰረት በከተማው ውስጥ በሚገኝ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተቀበረ። ፖሊስ ከግድያው ጋር በተያያዘ በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። <ref name="BBC" /> ሁንዴሳ ከመሞታቸው በፊት በነበረው ሳምንት ውስጥ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ ጨምሮ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው ተናግሯል። <ref name="BBC" />
የሃንዴሳ ሞት በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞዎችን የቀሰቀሰ ሲሆን ወደ 160 የሚጠጉ <ref>{{Cite web|url=https://www.aljazeera.com/opinions/2020/7/5/haacaaluu-hundeessaa-a-towering-musician-and-an-oromo-icon|title=Haacaaluu Hundeessaa: A towering musician and an Oromo icon}}</ref> ተገድለዋል። [[አዳማ|በአዳማ]] በተደረጉ ሰልፎች 9 ተቃዋሚዎች ሲገደሉ ሌሎች 75 ቆስለዋል። <ref name="NYT">{{Cite news|title=Hachalu Hundessa, Ethiopian Singer and Activist, Is Shot Dead|url=https://www.nytimes.com/2020/06/30/world/africa/ethiopia-hachalu-hundessa-dead.html|work=The New York Times|date=30 June 2020|access-date=30 June 2020}}</ref> በጭሮ ሁለት ሰዎች በጥይት ሲገደሉ [[ሐረር|በሐረር]] ከተማ ተቃዋሚዎች የልዑል [[ራስ መኮንን|መኮንን ወልደ ሚካኤልን]] ሃውልት አፍርሰዋል። እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2020 በካኒዛሮ ፓርክ ፣ ዊምብልደን ፣ ደቡብ ምዕራብ ለንደን የሚገኘው [[ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ|የአፄ]] [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ|ኃይለ ሥላሴ]] ሐውልት በኦሮሞ ተቃዋሚዎች ወድሟል። ብዙ የኢትዮጵያ ብሄረሰብ ኦሮሞ ተወላጆች በሃይለስላሴ ዘመን ተጨቁነዋል ይላሉ። <ref name="BBC 2 July">{{Cite web|title=Haile Selassie statue destroyed in London park|url=https://www.bbc.co.uk/news/uk-53259409}}</ref> ሁንዴሳ አጎት በግጭቱ ተገድሏል። የመብት ተሟጋቾች ሶስት ሰላማዊ ሰልፈኞች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ሲገልጹ በድሬዳዋ ከተማ ህዝባዊ ተቃውሞውን ለመበተን በጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት ስምንት ሰዎችን ማከም መቻሉን አንድ ዶክተር ተናግረዋል። <ref>{{Cite news|title=Slain Ethiopian activist and singer buried as 81 killed in protests|url=https://www.cnn.com/2020/07/02/africa/ethiopian-singer-buried-protests-intl/index.html|access-date=3 July 2020}}</ref>
ሰኔ 30 ቀን 2020 ከቀኑ 9፡00 ላይ፣ [[ኢንተርኔት በኢትዮጵያ|በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት]] በአብዛኛው ተቋርጧል፣ ይህ እርምጃ ቀደም ሲል በሁከትና ብጥብጥ ወቅት በመንግስት ይወሰድ ነበር። <ref>{{Cite web|last=|first=|date=2020-06-30|title=Internet cut in Ethiopia amid unrest following killing of singer|url=https://netblocks.org/reports/internet-cut-in-ethiopia-amid-unrest-following-killing-of-singer-pA25Z28b|language=en-US}}</ref> <ref>{{Cite web|last=|first=|date=2020-07-01|title=Internet shutdown in Ethiopia amid unrest at singer's death|url=https://www.euronews.com/2020/07/01/hachalu-hundessa-internet-shutdown-in-ethiopia-amid-unrest-at-singer-s-killing-thecube|language=en}}</ref> <ref>{{Cite web|first=Bethlehem|last=Feleke|date=|title=Internet cut off in Ethiopia after death of singer-activist|url=https://www.cnn.com/2020/06/30/africa/ethiopia-singer-killing-sparks-protest-intl/index.html}}</ref> ጠቅላይ ሚንስትር [[ዐቢይ አህመድ|አብይ አህመድ]] የሁንዴሳ ቤተሰቦች ማዘናቸውን ገልጸው ረብሻ እየባሰ ባለበት ሁኔታ እንዲረጋጋ አሳስበዋል። <ref name="BBC">{{Cite news|title=Deadly protests erupt after Ethiopian singer killed|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53233531|access-date=30 June 2020}}</ref> የመገናኛ ብዙሃን እና አክቲቪስት [[Jawar Mohammed|ጃዋር መሀመድ]] ሁንዴሳን በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ሲመልስ "ሀጫሉን የገደሉት ብቻ አይደለም:: በኦሮሞ ብሔር እምብርት ላይ ተኩሰው እንደገና! ! . . . ሁላችንም ልትገድሉን ትችላለህ፣ በፍጹም ልታስቆመን አትችልም! ! በጭራሽ! ” <ref>{{Cite news|title=Ethiopian singer Hachalu Hundessa shot dead in Addis Ababa|url=https://www.aljazeera.com/news/2020/06/popular-ethiopian-singer-hachalu-hundess-shot-dead-addis-ababa-200630071931911.html|date=30 June 2020|access-date=30 June 2020}}</ref> መንግስት [[Jawar Mohammed|ጃዋር]] መሃመድን እና ደጋፊዎቹን የከሰሰው የሃንዴሳ አስከሬን ወደ ትውልድ ከተማው [[አምቦ]] ሲወሰድ 100 ነው [[አዲስ አበባ|ከአዲስ አበባ]] በስተ ምዕራብ ኪሜ ከሁንዴሳ ቤተሰብ ፍላጎት ውጪ። የጃዋር የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ባለስልጣን አቶ ጥሩነህ ገመታ ለእሱ መታሰራቸው እንዳሳሰባቸውና “በጸጥታ ችግር ምክንያት የታሰሩትን” እንዳልጎበኙ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ አገልግሎት ተናግረዋል። ጃዋር በቀደሙት መንግስታት በፖለቲካ የተገለሉት የኢትዮጵያ ትልቁ ብሄር ለሆነው [[ኦሮሞ|የኦሮሞ ህዝብ]] የበለጠ የመብት ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ቀደም ሲል የለውጥ አራማጁን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ደግፎ እራሱ ኦሮሞ ቢሆንም ከዚያን ጊዜ ወዲህ ጠንከር ያለ ተቺ ሆኗል። <ref name="auto">{{Cite web|url=https://www.bbc.com/news/world-africa-53243325|title=Protests over Ethiopian singer's death 'kill 81'|date=1 July 2020}}</ref> ጃዋርን ጨምሮ 35 ሰዎች ከጠባቂው ስምንት ክላሽንኮቭ፣ አምስት ሽጉጦች እና ዘጠኝ የራዲዮ ማሰራጫዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል። <ref name="auto" />
የሃንዴሳ ግድያ [[አዲስ አበባ|በአዲስ አበባ]] እና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ሁከትና ብጥብጥ ከቀሰቀሰ በኋላ አብይ ፍንጭ የሰጠው ለግድያው ግልፅ የሆነ ተጠርጣሪ እና ግልጽ ምክንያት ሳይኖር ሁንዴሳን በውጪ ሃይሎች የተገደለ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። <ref name=":5">{{Cite web|title=As Ethiopians Take to the Streets to Protest a Musician's Murder, Prime Minister Abiy Ahmed Is Stuck in a Precarious Position|url=https://time.com/5864684/ethiopia-abiy-ahmed-hachalu-hundessa/}}</ref> አንድ የግብፅ ዲፕሎማት ግብፅ አሁን ካለችበት ውጥረት ጋር ምንም ግንኙነት የላትም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። <ref>{{Cite web|title=Cairo has ‘nothing to do’ with current tensions in Ethiopia: Egyptian diplomat - Politics - Egypt|url=http://english.ahram.org.eg/NewsContent/1/64/373676/Egypt/Politics-/Cairo-has-%E2%80%98nothing-to-do%E2%80%99-with-current-tensions-in.aspx}}</ref> ኢያን ብሬመር ''በታይም መጽሄት'' መጣጥፍ ላይ ጠ/ሚኒስትር አብይ “ኢትዮጵያውያንን በጋራ ጠላት የሚታሰበውን አንድ የሚያደርጋቸው ፍየል እየፈለጉ ሊሆን ይችላል” ሲል ጽፏል። <ref name=":5" />
== ዲስኮግራፊ ==
* ''ሳንዪ ሞቲ'' (2009)
* ''ዋኢ ኬኒያ'' (2013)
* ''ማዓል ማሊሳ'' (2021) <ref name="Maal">{{Cite news|url=https://www.bbc.com/afaanoromoo/oduu-57611399.amp|title=Albamiin Haacaaluu Hundeessaa walleewwan 14 qabu torban dhufu akka gadhiifamu maatiin himan}}</ref>
== ዋቢዎች ==
# "ግድያው የኢትዮጵያውያንን ተቃውሞ የቀሰቀሰበት ዘፋኝ" የቢቢሲ ዜና. ጁላይ 2 2020። በጁላይ 13 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 13 የተገኘ
# የኢትዮጵያውያን የአመፅ ደጋፊዎች በለንደን የሚገኘው የሀይሊ ስላሴ ሃውልት ፈርሶ ሐምሌ 3 ቀን ተመለሰ
# "ኢትዮጵያዊው ዘፋኝ በብሄር ብጥብጥ ተቀበረ" የቢቢሲ ዜና. ጁላይ 2 2020። ኦገስት 7 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 21 የተገኘ
# ደስታ (ሰኔ 30 ቀን 2020)። "Hachalu Hundessa Death, Dead - Hachalu Hundessa ሞተ, ተገደለ, ሚስት, ዊኪ, ባዮ" የቅርብ ዜና ደቡብ አፍሪካ. በጁላይ 1 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። በሰኔ 30 የተገኘ
# "ኢትዮጵያዊው ዘፋኝ ከተገደለ በኋላ ገዳይ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ" የቢቢሲ ዜና. 30 ሰኔ 2020። በጁላይ 1 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁን 30 ተገኘ።
# ሀጫሉ ሁንዴሳ - አልፈራም (Official Music Video) Hachalu Hundessa - አልፈራም (Official Music Video)
# "ባለ14 ትራክ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል ይላል ቤተሰብ" (በእንግሊዘኛ)።
# አዴሞ፣ መሐመድ (ታህሳስ 31፣ 2017)። "የ2017 የኦሮሞ ምርጥ ሰው፡ ሀጫሉ ሁንዴሳ" OPride በጁላይ 19 2019 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁን 30 የተገኘ
# ሰላም፣ አመሰግናለሁ (መጋቢት 30 ቀን 2018)። ""እዚህ ነን"፡ የኢትዮጵያ አብዮት ማጀቢያ ሙዚቃ የአፍሪካ ክርክሮች. በጁላይ 1 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። በሰኔ 30 የተገኘ
# ዳሂር፣ አብዲ ላፍ (30 ሰኔ 2020)። " ኢትዮጵያዊው ዘፋኝ እና አክቲቪስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመትቷል" ኒው ዮርክ ታይምስ. በጁላይ 1 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። በሰኔ 30 የተገኘ
# የሃጫሉ ሞት ተከትሎ ብጥብጥ ውስጥ የተሳተፉ ሚዲያዎች፣ ጁላይ 4
# "የኢትዮጵያ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ስነስርአት ላይ ፖሊስ አገደ" የኢትዮጵያዊው ዘፋኝ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ስነስርአት (በቱርክ) ለቅሶ ላይ የነበሩትን ፖሊስ አገደ። በጁላይ 21 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 21 ላይ የተገኘ
# አሎ፣ አወል ኬ "የ19ኛው ክፍለ ዘመን 1000ኛ ዓመት በዓል" www.aljazeera.com
# "በለንደን ፓርክ የሃይለስላሴ ሃውልት ፈርሷል" የቢቢሲ ዜና. የቢቢሲ ዜና. ጁላይ 2 2020። በጁላይ 7 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 2 ተገኘ።
# ገዳም ፣ ፈለቀ ፣ አዴባዮ ፣ ተፈራ ፣ ቤተልሔም ፣ ቡኩላ። "የተገደለው ኢትዮጵያዊ አክቲቪስት እና ዘፋኝ በተቃውሞ 81 ሰዎች ሲገደሉ ተቀበረ" ሲ.ኤን.ኤን. በጁላይ 2 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 3 የተገኘ
# "በኢትዮጵያ ዘፋኝ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል" NetBlocks 30 ሰኔ 2020። በጁላይ 6 ከመጀመሪያው የተመዘገበ
# "በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋቱ በዘፋኙ ሞት ምክንያት አለመረጋጋት ተፈጠረ" ዩሮ ኒውስ ጁላይ 1 2020። በጁላይ 3 ላይ ከመጀመሪያው የተመዘገበ
# ፊሊክስ፣ ቤተልሔም ዘፋኝ አክቲቪስት ከሞተ በኋላ የኢንተርኔት አገልግሎት በኢትዮጵያ ተቋርጧል። ሲ.ኤን.ኤን. ጁላይ 7 ላይ ከመጀመሪያው የተመዘገበ
# "ኢትዮጵያዊው ዘፋኝ ሃጫሉ ሁንዴሳ በአዲስ አበባ በጥይት ተመትቷል" አልጀዚራ 30 ሰኔ 2020። በጁላይ 1 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁን 30 ተገኘ።
# "በኢትዮጵያ ዘፋኝ ሞት ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ገደለ የቢቢሲ ዜና. ጁላይ 1 2020። በጁላይ 3 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 3 ተገኘ።
# "ኢትዮጵያውያን የአንድን ሙዚቀኛ ግድያ ለመቃወም ጎዳናዎች በወጡበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል" ጊዜ። በጁላይ 14 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 11 ላይ የተገኘ
# "ካይሮ "ከአሁኑ የኢትዮጵያ ውጥረት ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም: የግብፅ ዲፕሎማት - ፖለቲካ - ግብፅ" አህራም ኦንላይን. በጁላይ 11 2020 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ጁላይ 11 ላይ የተገኘ
== ውጫዊ አገናኞች ==
ከሃጫሉ ሁንዴሳ ጋር የተገናኘ ሚዲያ በዊኪሚዲያ ኮመንስ{{Authority control}}
[[መደብ:ኢትዮጵያን ድምጻዊ]]
[[መደብ:ግድያ]]
[[መደብ:ፋየር አርም ግድያ]]
[[መደብ:ከኦሮሚያ ከተማ]]
[[መደብ:ኦሮሚያ ዘፍ ን]]
[[መደብ:የኦሮሞ ህዝብ]]
[[መደብ:ወንድ]]
[[መደብ:21 ክፍለ ዘመን]]
[[መደብ:2020]]
[[መደብ:1986]]
[[መደብ:አርቲክልስ]]
[[መደብ:ዊኪዳታ]]
[[መደብ:ገጾች]]
[[መደብ:ውጫዊ አገናኝ]]
fquu3c46v0r62nht60535mofv82fjux