ውክፔዲያ amwiki https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD MediaWiki 1.47.0-wmf.1 first-letter ፋይል ልዩ ውይይት አባል አባል ውይይት ውክፔዲያ ውክፔዲያ ውይይት ስዕል ስዕል ውይይት መልዕክት መልዕክት ውይይት መለጠፊያ መለጠፊያ ውይይት እርዳታ እርዳታ ውይይት መደብ መደብ ውይይት በር በር ውይይት TimedText TimedText talk ሞጁል ሞጁል ውይይት Event Event talk ውክፔዲያ ውይይት:Searching 5 1666 392065 6856 2026-05-08T12:57:03Z ~2026-27949-79 58481 /* grade 7 */ አዲስ ክፍል 392065 wikitext text/x-wiki መግፋት በሚለው ፈንታ ይጫኑት ቢተካ : አመሰግናለሁ፤ "መግፋት" በብዙ ፔጅ ላይ በሚታይበት በቶሎ ይተካል፤ "ልዩ ገጽ" ካልሆነ ለማስተካከል እርስዎ ችሎታ አለልዎት!!! == grade 7 == all 3zucpchyntqjihnvsanwsx2oz63um6n 392066 392065 2026-05-08T13:00:17Z ~2026-27949-79 58481 /* social study */ አዲስ ክፍል 392066 wikitext text/x-wiki መግፋት በሚለው ፈንታ ይጫኑት ቢተካ : አመሰግናለሁ፤ "መግፋት" በብዙ ፔጅ ላይ በሚታይበት በቶሎ ይተካል፤ "ልዩ ገጽ" ካልሆነ ለማስተካከል እርስዎ ችሎታ አለልዎት!!! == grade 7 == all == social study == unit 6 l49kv7me8tt8gkyciyhhkopt4j0aoty ፍሥሓ አጥላው 0 9326 392067 384779 2026-05-08T13:39:26Z Yacob 48404 Yacob moved page [[ፍስሓ አጥላው]] to [[ፍሥሓ አጥላው]]: Misspelled title: The canonical spelling as used by the subject. 384779 wikitext text/x-wiki ''' ኢንጂኔር ፍሥሓ አጥላው''' /Fesseha Atlaw '''(ፍስሐ አጥላው፤ ፍስሀ አጥላው )''' የ[[ግዕዝ]] ኢትዮጲክ /ETHIOPIC [[ፊደል]] [[ሶፍትዌር]] እንደ [[አውሮፓ]] አቆጣጠር በ1980 ዎቹ ሊቅ ናቸው። ኢንጂኔር ፍሥሓ አጥላው በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የሚታወቁት የኢትዮጵያን ፊደላት ለመጀመሪያ ጊዜ ከኮምፒውተር አዛምደው ፤ የመጀመሪያውን የአማርኛ የኮምፒውተር ቃላት ማቀነባበሪያ ( Amharic Word Processor) ፕሮግራም ለተጠቃሚዎች በማቅረባቸው ነው•. ፍሥሓ አጥላው (Fesseha Atlaw) ከአባታቸው ከአቶ አጥላው ወልደዮሐንስ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ሐመረ ገብረፃድቅ በአዲስ አበባ ከተማ 1955 ዓም ተወለዱ። ለ12 አመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አንደኛ ደረጃ ተመላላሽ /ኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት ነበር። ገና የአንደኛ ክፍል ሕፃን ተማሪ በነበሩበት ጊዜ ባስገኙት ልዩ የትምህርት ውጤት ተመርጠው ፤ ከንጉሰ ነገስቱ ፤ [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]] እጅ ወደ ቤተ መንግስት ተልከው ልዩ ሽልማት ተቀብለዋል ። አንደኛ ና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በዚሁ አሁን ኮከበ ፀባህ ተብሎ በሚጠራው ትምህርት ቤት ነው ። በዚህ ትምህርት ቤት ሳሉ ከመደበኛ ትምሄርቶች ውጬ በልዩ ልዩ ከለቦችና የትርፍ ጊዜ እንቅስቃሴዎች ይካፈሉ ነበር ። ለምሳሌ ለመጥቀስ ፤ የሙዚቃ ባንድ ፤ የወጣት ደራሲያን ክለብ ፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ከለብ ፤ የሬዲዮና ጋዜጣ ክለብ ይገኙበታል ። ዘጠነኛ ክፍል ሳሉ በአዲስ አበባ በተደረገ የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኤክዚቢሽን አዘጋጆች የፍሥሐ አጥላውን የዘጠነኛ ክፍልን መርጠው ወደ አዳራሹ በአውቶቢስ በመውሰድ የአሜሪካን ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ወጣቶች ዓይን በሚል ዶኪሜንታሪ ፊልም ተሰርቶ በዓለም ዙርያ ከታየ በኋላ በአሜሪካን ስቴት ዲፓርትሜንት መዝገብ ቤት ይገኛል ። በዚህም ፊልም ወጣቱ ፍሥሐ አጥላው በተደጋጋሚ ከመታየቱም በላይ ፤ ከእንግሊዝኛ አስተማሪው፤ ከወይዘሮ ብርሃኔ አስፋው ጋር ያደረገው ጥያቄና መልስም ተቀድቶ የዚህ ታሪካዊ ፊልም አካል ሆኖ ይታያል ። ፊልሙ አሁን ዩ ቲውብ ላይ “ Fesseha Atlaw USA, Ethiopia “ በሚል ማጣቀሽያ ርዕስ ይገኛል ። ቀጥሎም በአዲስ አበባ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ገብተው ፤ በኢንጅኔርንግ መስክ ትምህርታቸውን መከታተል ሲጀምሩ ፤ በተማሪዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ በተነሳ ግጭት ዩኒቨርስቲው ስለተዘጋ ፤ ከኢትዮጵያ ወጥተው ትምህርታቸውን ለመከታተል አውሮፓና አሜሪካን አገር ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ጋር መፃፃፍ ጀመሩ ። ብዙዎች ዩኒቨርቲዎች ቢቀበሏቸውም ሙሉ (100%) ስኮላርሺፕ ሰጥቶ የተቀበላቸው ኦክላሆማ የሚገኘው ኦራል ሮቤርትስ የተባለው ዩኒቨርስቲ ነበር ። ከዚሁ ዩነቨርስቲ በ ቴሌኮሙኒኬሽንና በ ማቲማቲክስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1975 ተቀብለው፤ ለሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸው ወደ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ኔብራስካ አመሩ ፤ የባዮ ሜዲካል ቴሌኮሙኒኬሽን፤ ሲስቴም ኤንጅኔርንግ እንዲሁም በአፕላይድ ማቲማቲክስ ፤ ሁለት የማስተርስ ዲግሪ በ1978 አጠናቀው ፤ ከአሜሪካን መንግስት በተሰጠ ልዩ ቪዛ ወደ ሥራ መስክ ተሰማሩ ፤ የተቀጠሩበት መሥራያ ቤት ለአሜሪካን ሥራ ሚኒስቴር (Department of Labor) አመልክቶ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቶላችው በሥራ እንዲቀጥሉ ተደረገ ። በሥራ ዓለም ተቀጥረው የሰሩባቸው ሙያዎችና መሥሪያ ቤቶች ፡ 1ኛ FMC Corporation Automated Manufacturing Machine Programming (Robotics) 2) ATARI : Manufacturing Engineering; Game console and personal Computers 3) Hewlett- Packard - Development Engineer/ScientistElectronic Power Conversion Systems 4) Agilent Technologies : Engineering Manager ; Microwave Test Instrumentation 5) Medtronic inc : Research and Development - Bio-Medical Devices Materials በግላቸውና በትርፍ ጊዜያቸው ፡ 1 ) Dashen Engineering Company - Founder and CEO እራሳቸው ባቋቋሙት ዳሽን ኢንጅነሪንግ ኩባንያ አማካይነት የመጀመሪያውን የአማርኛ ኮምፒውተር መፃፊያን ያስተዋወቁ ፈር ቀዳጅ ናቸው። 2 ) Ethiopian Famine Relieve Organization - Chairman በ 1984 በኢትዮጵያ ለይ በደረሰው የድርቅና የረሃብ አደጋ አሜሪካን ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ፤ አሜሪካውያንን ያስተባበረ ማኅበር ሊቀ መንበር ሆነው ፤ ወደኢትዮጵያ ገነዘብና ቁሳቁስ በመላክ ፤ የውሃ ጉድጓድም በማስቆፈር ትልቅ አስተዋፅዖ አድርገዋል 3) Unicode Technical Symposium - Life time memberበዓለም ዙርያ የሚገኙ ቋንቋና ፊደላትን በኮምፕውተር ውስጥ ለማካተት በተቋቋመው ዩኒኮድ (UNICODE) የሚባለው የአለም አቀፍ ስታንዳርድ ድርጅት (Internation Standards Organization -ISO ) ሥር በተቋቋመው ኮሚቴ ፤ ኢንጂኔር ፍሥሓ ከመስራች አባላት አንዱ ነበሩ ፤ (የዚህ ኮሚቴ ዋና ዋና አባላት Google ; IBM ; Apple : Amazon ; HP ; Adobe ያካተተ ነበር ። በዚህም ኮሚቴ አማካኝነት ኢንጂኔር ፍሥሓ የኢትዮጵያ ፊደላት ፤ ኢትዮፒክ Ethiopic) በመባል በዓለም ዙርያ የሚፈበረኩ ማንኛውም ኮምፒውተር ውስጥ ቋሚ ቦታ እንዲያዝላችው ትልቁን አስተዋፀዖ አድርገዋል ። 4 ) Director : Fesseha Atlaw Wolde Yohannes Foundation Endowment በ2020 ላይ በቤተሰባችው ስም ባቋቋሙት የበጎ አድራጎት ድርጅት ሥራ ላይ ልዩ ልዩ እርዳታን [[ኢትዮጵያ]] ውስጥ ያደርጋሉ ። ከእነዚህም ፡ የጎዳና ተዳዳሪ ወጣት እናቶችንና ልጆቻቸውን እየሰበሰቡ የሚረዳ ድርጅትን መደገፍ በኢትዮጵያ ፊደላት የሞባይል ወይንም የኮምፒውተር መተግበሪያ የሚሰሩ ወጣቶችን ለማበረታታት በየዓመቱ ውድድር በማዘጋጀት ይገንዘብ ሽልማት መስጠት የተለያዩ የኦኮኖሚ ችግር የደረሰባቸውን ወጣት ተማሪዎችንና ሌሎችም የተችገሩ የኢትዮጵያ ዜጋዎች የሚረዱ ድርጅቶችን መርዳት ። ይገኙባችዋል ። ፍሥሓ ከምህንድስና ሙያቸው ባሻገር የደራሲነት ዝንባሌ አላቸው። ገና በ12 አመታቸው መፅሀፍ ፅፈው አሳትመዋል። በ15 አመታቸው ደግሞ የፃፉት ተውኔት በሃገሪቱ ታላቁ ትያትር ቤት በሃገር ፍቅር ለመታየት በቅቷል። ትያትሩ የብዙዎችን ትኩረት ሲስብ ከነሱ መሃል ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ዋነኛው ናቸው። ተውኔቱ ኢትዮጵያን ሔራልድ ላይ "በጣም ምርጥ" ተብሎ ሲሞካሽ የኢትዮጵያ ድምፅ ደግሞ “የ15 ልጅ ቲያትር ደራሲ” በሚል ርዕስ ስለ ተውኔቱ አንድ ሙሉ ገፅ ዘገባና ቃለመጠይቅ አድርጎላቸዋል። ኢንጅነሪንግ ለማጥናት ወደ አሜሪካ ሲመጡ የድርሰት ዝንባሌያቸውን ለግዜው ወደ ጎን አስቀምጠውት ነበር ። የመጀመሪያ ስራቸውን አግኝተው ከተቀጠሩ በኋላ እንደገና ወደ መፃፍ ለመመለስ የአማርኛ ታይፕራይተር አጥብቀው መፈለግ ጀመሩ ። ነገር ግን በደርግ ዘመን የአማርኛ ታይፕራይተር ማስመጣት የማይታሰብ እና የማይቻል ሆነባቸው። በግዜው ይህንን መሞከር ከባድ ወንጀል ነበር። ብቸኛ የአማርኛ ታይፕራይተር ሰሪዎች ከሆኑት ኦሊቬቲ እና ኦሎምፒያን ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም። ኦሊቬቲ እና ኦሎምፒያ የሚሰሩትን የአማርኛ ታይፕራይተር ከኢትዮጵያ ውጪ ላለመሸጥ ከደርግ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግዴታ ገብተው ነበር። ምክንያቱም በውጭ ያሉት የመንግስት ተቃዋሚዎች ከሕዝቡ ጋር የሚገናኙት በፅሁፍ ብቻ ሰለነበር ነው (ዴሞክራሲያና የመሳሰሉትም ፀረ መንግስት ፅሁፎች የሚሰሩት ይህንኑ “የአማርኛ የፅሕፈት መኪና” ነበር ። "ችግር ብልሃትን ይወልዳል" እንደሚባለው ኢንጂኔር ፍሥሓ ለራሳችው ደርሰት መፃፊያ ሲሉ በጊዜው በነበረው የቤት ኮምፒውተር (Personal Computer) ላይ የመጀመሪያውን የአማርኛ ቃላት ማቀነባበሪያ ሊፈጥሩ ተግተው ለመስራት ወሰኑ።  በጊዜው ዊንዶውስ ና ማውስ ገና አልተፈጠረም። የቤት ኮምፒውተሮች ገና ዳዴ በማለት እርምጃ ውስጥ ነበሩ። ምንም እንኳን HP የሚሰሩበት HP-150 የተባለ ኮምፒውተር የስራ ዴካቸው ላይም ቢኖር ፤ ከመሥሪያ ቤት ውጭ ገና በጥቅም ላይ ያልዋለና ልዩ የሆነ ሲስትመና ፕሮሴሰር የሚጠቀም ነበር ። በዚያን ጊዜ (በ80 ዎቹ ማለት ነው ) አዳዲስ የቤት ኮምፒውተሮች ወጣ ወጣ ማለት ቢጀምሩም ለመግዝት በጣም ውድ ነበሩ። ኢንጂኔር ፍሥሓ እርካሽ የተባለውን ኮምፒውተር(8086 ፕሮሰሰር) እና ዶት ማትሪክስ ፕሪንተር በ380$ በወር ተከራይተው በግል ጊዜያቸው አማርኛን ከኮምፕውተር ለማዛመድ ጥረታቸውን ጀመሩ። በ1980 በመጀመሪያ ፊደላቱን አንድ ባንድ በእጃቸው በሰንጠረዥ ውስጥ እየቀረፁ ኮምፒውተር ሜሞሪ ላይ ማስገባት ጀመሩ ። ይህም ጊዜ የሚፈጅ ሂደት ከመሆኑም አልፎ የኢትዮጵያ ፊደላት ብዛትና የቅርፆቹም ስፋት በጣም አስቸጋሪ ነበሩ ። ለኮምፒውተር ስክሪንና ለማተሚያ ( Printer)የተለያየ ዲዛይን ያስፈልጋቸው ነበር ፤ የተለያዮ የስክሪን ዓይነቶችና ፤ የማተሚያ ዓይነተች እያንዳንዳቸው የተለያየ ዲዛይን ያስፈልጋቸው ነበር ። ይህንንም ሥራ ለማቅለል ለአማርኛ ተደጋጋሚ የሚመስሉ ፊደላትን ለመቀነስ የመጣላቸውን ሃሳብ ለቋንቋ ምሁራን አማክረው ፤ ፊደሎቹ ለአማርኛ ተደጋጋሚ ቢመስሉም ፤ ለትግርኛ ና ለግዕዝ ልዩ ትርጉም ያላቸው አስፈላጊዎች እንደሆኑ ስለተረዱ የፊደሎቹን የመቀነስ ሃሳብ ትተው እንደውም በጊዜ በነበረው ታይፕ ራይተር ላይ ያልተካተቱ ከአማርኛ ውጭ አዳዲስ ፊደላትን (ለምሳሌ ለትግርኛ “ቐ” የሚለውንና ለፋን [[ኦሮሞ]] “ዸ” የሚለውን በማካተት ፊደሎቹ የአማርኛ ብቻ ሳይሆኑ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚወክሉ መሆናቸውን በቋሚ መልክ እንዲቀመጥ አድርገዋቸዋል ። በአለም ዙሪያም የኢትዮጵያ ፊደላት ‘ኢትዮፕክ” በሚባለው ስም የትኛውም ኮምፕውተር ላይ ተጨማሪ ትሮግራም መጬን ሳያስፈልግ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚዎች ቀርቦ ይገኛል ። ስለዚህም ከማንኛውም ቋንቋ ወደ [[አማርኛ]] ወይንም ከአማርኛ ወደ [[እንግሊዝኛ]] ና ሌሎችም ቋንቋዎች ትርጉሞች ና ፤ በድምፅ የሚያነብና የመሳሰሉ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎች ቋንቋችን ተጠቃሚ ሊሆን የቻለው። {{መዋቅር-ሰዎች}} ==የውጭ መያያዣ== *https://ethiopicsoftware.org/index.html {{Wayback|url=https://ethiopicsoftware.org/index.html |date=20221129040710 }} *http://www.tadias.com/04/06/2018/how-ethiopic-script-was-introduced-to-modern-computers-interview-with-fesseha-atlaw/ *http://abyssiniagateway.net/fidel/legends/FessehaAtlaw/ {{Wayback|url=http://abyssiniagateway.net/fidel/legends/FessehaAtlaw/ |date=20160421122948 }} *http://www.ethiomedia.com/ace/engineer_fesseha_atlaw.html {{Wayback|url=http://www.ethiomedia.com/ace/engineer_fesseha_atlaw.html |date=20070902233153 }} [[መደብ:የኢትዮጵያ ሰዎች]] [[መደብ:ኮምፒዩተር]] bj8mcmqq9kqhcl7oygs6tvxfhnizfv8 ቀነኒሳ በቀለ 0 36132 392071 388609 2026-05-09T07:29:39Z ~2026-27852-18 58495 392071 wikitext text/x-wiki * በኦሎምፒክ የ 3ወርቅ የ 1ብር * በወርልድ ሻምፕዮን የ 5ወርቅ የ 1ነሃስ * በወርልድ የቤት ውስጥ ሻምፕዮን የ 1ወርቅ * በአፍሪካ ሻምፕዮና የ 2ወርቅ * በኦል አፍሪካንስ ጌም የ 1ወርቅ * በወርልድ ክሮስ ካንትሪ የ 11ወርቅ የ 1ብር ሜዳሊያዎች ባለ ክብር የተወለደው [[ሰኔ]] 6 ቀን በ1974 አ.ም በአርሲ ተወለደ. በሀገር አቋራጭ፣ በጎዳና እና በሜዳ ላይ ያከናወናቸው ውድድሮች እና አንፀባራቂ ድሎቹ በታሪክ ከታዩት ታላላቅ አትሌቶች መካከል እንዲመደብ አድርገውታል።<ref>ከራሱ አፍ ካሊድ እስማኤል</ref> በረጅም ርቀተ ሩጫ የመጨረሻውን ዙር እንደ አጭር ርቀት ሯጭ ሲሮጥ ያዩት ብዙዎች ፍጥነቱን ሲገልጹ “አቦ ሸማኔ” ይሉታል። ከርሱ ጋር የሮጠው የኬኒያ አትሌት ክፕሮፕ ደግሞ የቀነኒሳን ፍጥነት ሲገልጽ “ከኃይሌ ጋር ስትሮጥ እስከ መጨረሻው እንደምታሸንፍ ተስፋ አድርገህ ትሮጣለህ፤ ተወዳዳሪህ ቀነኒሳ ሲሆን ግን ገና ከመነሻው ያሸንፍሃል” በማለት ነው። ከ1 ሺህ 500 ሜትር እስከ ማራቶን በተሳተፈባቸው ውድድሮች ከ17 በላይ ክብረ-ወሰኖችን ሰባብሯል። በአንድ የኦሊምፒክ ውድድር ሁለት ክብረ-ወሰኖችን የሰበረ ድንቅ ሯጭ ነው። ሀገር አቋራጭ እና የወጣቶች ሻምፒዮናን ጨምሮ ሀገራችንን ወክሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተወዳደረባቸው ርቀቶች 26 የወርቅ፣ 3 የብር እና 2 የነሐስ አጠቃላይ 31 ሜዳሊያዎችን ለኢትዮጵያ አስገኝቷል። ከረጅም ጉዳት በኋላ በተካፈለበት የቫሌንሺያ ማራቶን በ4ኛነት ቢያጠናቅቅም የጨረሰበት 2:04:19 ሰዓት ከ40 ዓመት በላይ ዕድሜ ከ2፡05 ሰዓት በታች የጨረሰ የመጀመሪያው አትሌት አድርጎታል። ይህንኑ ተከትሎ የኬንያ ጋዜጦች ለቀነኒሳ “ዕድሜ የማይገድበው” የሚል ቅፅል ስም ሰጥተውታል። የተወለደው ሰኔ 6 ቀን 1974 ዓ.ም በአርሲ ዞን ቦቆጂ ከተማ ነው። በትምህርት ቤት እያለ በስፖርት ክፍለ ጊዜ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የተመለከቱት አርቆ አሳቢ መምህሩ ወደ አትሌትክሱ ቢገባ ውጤታማ እንደሚሆን በነገሩት መሠረት ነው ሩጫ የጀመረው። እንደተባለውም ወደ አትሌትክሱ በገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግቦ ዓለምን አስደምሟል። ዓለም አቀፍ ውድድር የጀመረው እ.አ.አ በ2001 ሲሆን፣ በመጀመሪያ ሩጫውም የወጣቶች ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮን የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ አጠናቅቋል። በተመሳሳይ ዓመት 3 ሺህ ሜትር ክብረ-ወሰን የሰበረ ሲሆን፣ ይህ ክብረ-ወሰን ለሦስት ዓመት ተኩል ቆይቷል። እ.አ.አ 2000 እና 2001 በኔዘርላንድ የተደረጉትን የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በአንደኝነት አጠናቅቋል። በ19 ዓመቱ የጀመረውን ሀገር አቋራጭ ውድድር ለተከታታይ አምስት ዓመታት በአሸናፊነት በማጠናቀቅ 11 የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል። የ5 ሺህ እና የ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ-ወሰኖችን እ.አ.አ ከ2004 እስከ 2020 ባሉት ተከታታይ 16 ዓመታት ማንም ሳይሰብራቸው የግሉ አድርጓቸው ቆይቷል። በ2004 የአቴንስ ኦሊምፒክ ላይ በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም በ5 ሺህ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል። በ2008 የቤጂንግ ኦሊምፒክ ደግሞ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር ውድድሮች በሁለቱም ውድድሮች ክብረ-ወሰን በመስበር ጭምር የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ ደማቅ ታሪክ ጽፏል። በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ታሪክ በ12 ኪሎ ሜትር ስድስት እና በ4 ኪሎ ሜትር ደግሞ አምስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን፣ በአጠቃላይ 11 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያሸነፈ እጅግ ስኬታማ አትሌት ነው። እ.አ.አ በ2003፣ 2005፣ 2007 እና 2009 በተካሄዱ አራት ተከታታይ የዓለም ሻምፒዮናዎች በመሳተፍ በ10 ሺህ ሜትር 4 የወርቅ፣ በ5 አንድ የወርቅ እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያዎችን አሸንፏል። ቀነኒሳ በ2003 በ10 ሺህ ሜትር ዓለም አቀፍ ሩጫ ማድረግ ከጀመረበት እስከ 2011 ድረስ ያልተሸነፈ ብቸኛ አትሌት ነው። በ2006 በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናም በ3 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነበረ። በ2014 የውድድር ዘመን በፓሪስ ማራቶን ድል የተቀዳጀ ሲሆን፣ ያስመዘገበው ሰዓት በታሪክ ስድስተኛውን ፈጣን የማራቶን ውድድር ሰዓት ሆኖ ተመዝገቧል። እ.አ.አ መስከረም 25 ቀን 2016 የበርሊን ማራቶንን 2:03.03 በሆነ ሰዓት አሸንፏል። በውድድሩ አዲስ የግል ምርጥ ሰዓቱን ያስመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በውድድሩ ታሪክ ሦስተኛው ፈጣን የማራቶን ሰዓት ነበረ። ቀነኒሳ ኢንተርናሽናል ውድድሮችን መሳተፍ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 22 ዓመታት ከ168 በላይ ኢንተርናሽናል ውድድሮችን አድርጓል። ይህም በአማካይ ከ7 በላይ ኢንተርናሽናል ውድድሮችን በየዓመቱ አድርጓል ማለት ነው። 5 ሺህ ሜትርን ስድስት ጊዜ ከ12 ደቂቃ ከ48 ሰኮንድ በታች ገብቷል፤ አራት ጊዜ ደግሞ ከ12 ደቂቃ ከ49 ሰኮንድ እስከ 12 ደቂቃ ከ53 ሰኮንድ ውስጥ ገብቶታል። 10 ሺህ ሜትርን ሰባት ጊዜ ከ26 ደቂቃ ከ46 ሰኮንድ በታች፤ ሦስት ጊዜ ደግሞ ከ26 ደቂቃ ከ48 ሰኮንድ እስከ 26 ደቂቃ ከ53 ሰኮንድ ውስጥ አጠናቋል። የእንግሊዙ ሞ ፋራ የቀነኒሳን አይቶ እሱ የሮጠውን ያህል እሮጠዋለሁ ብሎ አስቦ የነበረ ቢሆንም፣ ሞክሮ ሲያየው ሊቀርብ ቀርቶ ለመጠጋት ሲያቅተው “ወላሂ እሱ ጨካኝ ነው” ሲል ገልጾታል። አትሌት ቀነኒሳ በአትሌቲክሱ መድረክ የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት ተሰጥቶታል። ቀነኒሳ ጉዳት ተደጋግሞበት ለረጅም ጊዜ ከውድድር ባያርቀው በአትሌቲክሱ ዘርፍ ማንም ሊደርስበት የማይችለውን ታሪክ ሊያስመዘግብ ይችል እንደነበረ ብዙዎች ይናገራሉ።     n8icfnj5min52rmd4wiz5r78m28l44u ኢካሮስ 0 38158 392069 384175 2026-05-08T18:23:46Z JackyM59 56712 Photograph updated 392069 wikitext text/x-wiki [[ስዕል:Pieter Bruegel the Elder - Landscape with the Fall of Icarus - Brussels, Royal Museums of Fine Arts of Belgium - Google Arts & Culture.jpg|250px|thumbnail|right| የኢካሮስ ውድቀት፣ በ፲፭፻፶ በ[[ፒተር ብሮየል]] እንደተሳለ]] '''ኢካሮስ''' እንደ ጥንቱ [[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] አፈ ታሪክ የታላቁ እጅ ጥበበኛ የ [[ዴድለስ]] ልጅ ነበር። ስለ ኢካሮስ ከተነገሩ ዋና ታሪኮች አንዱ ይኖሩበት የነበረውን ደሴት በረው እንዲያመልጡ፣ ዴደለስ ለልጁና ለራሱ ከ[[ሰም]]ና ከወፎች ላባ አራት ክንፎች እንደሰራና ክንፎቻቸውን እየለበሱ እያለ ዳዲለስ ልጁን ኢካሮስን እንዲህ ብሎ እንዳስጠነቀቀው ነበር፦ «ወደ ፀሐይዋም ሆነ ወደ ባሕሩ እንዳትጠጋ፣ ይልቁኑ የኔን የበረራ መስመር ተከተል።» አባትና ልጅ ክንፋቸውን እያራገቡ መብረር ሲጀምሩ ኢካሮስ ልቡ እንደሸፈተና በኋላም መሬትን እየለቀቁ ወደ አየሩ ሲቀዝፉ ኢካሮስ በደስታ እራሱን መቆጣጠር እንዳቃትው ታሪኩ ያትታል። የአባቱን ምክር ረስቶ፣ ወደ ሰማይ፣ ወደ ላይ ፀሐይን ተጠግቶ በመብረሩም ክንፉን አጣብቆ የያዝው [[ሰም]] በመቅለጡ ኢካሮስ ወደ ባሕሩ ወደቆ እንደተከሰከሰ አፈታሪኩ ያትታል። ይህ ባሕር እስከ አሁን ዘመን የኢካሮስ ባሕር ወይንም [[ኢካርያ]] ይባላል።<ref>{{cite book|first = Robert|last = Graves|authorlink = Robert Graves|year = 1955|title = [[The Greek Myths]]|chapter = 92&nbsp;– Daedalus and Talus|isbn = 0-14-007602-6}}</ref><ref>[[Thomas Bullfinch]] - The Age of Fable Stories of Gods and Heroes [http://www.kundaliniawakeningsystems1.com/downloads/thomas-bulfinchs-mythology-age-of-fable-vols1&2.pdf ''KundaliniAwakeningSystem.com''] {{Wayback|url=http://www.kundaliniawakeningsystems1.com/downloads/thomas-bulfinchs-mythology-age-of-fable-vols1%262.pdf |date=20130124162013 }} & The Internet Classics Archive by Daniel C. Stevenson : Ovid - [http://classics.mit.edu/Ovid/metam.8.eighth.html Metamorphoses - Book VIII ] + Translated by [[Rolfe Humphries]] - [http://www.dl.ket.org/humanities/literature/litpacket/metamorphoses.htm KET Distance Learning ] {{Wayback|url=http://www.dl.ket.org/humanities/literature/litpacket/metamorphoses.htm |date=20120614120213 }} 2012-01-24</ref><ref>Translated by [[A. S. Kline]] - [[University of Virginia Library]][http://etext.lib.virginia.edu/latin/ovid/trans/Metamorph8.htm#_Toc482327661/ .edu] {{Wayback|url=http://etext.lib.virginia.edu/latin/ovid/trans/Metamorph8.htm#_Toc482327661/ |date=20110217152723 }} Retrieved 2005-07-03</ref> አንድ አንድ ታሪክ አጥኘወች የዚህን አፈታሪክ መልዕት ሰዎች ከመጠን ያለፈ የገንዘብ፣ የስልጣልን፣ የመታዎቅ ወዘተ...ፍላጎት ባደረባቸው ጊዜ ውድቀታቸውም በዚያው ልክ ይፋጠናል እሚል ነው። ==ማጣቀሻ== <references/> [[መደብ: የግሪክ አፈታሪክ]] 21npwabjzgoycxp4qqstlhtn66m4jho ጌሎራ ቡንግ ካርኖ ስታዲየም 0 53200 392070 380881 2026-05-09T05:40:30Z CommonsDelinker 186 ፋይሉ «GBK_Complex_at_night.jpg» ከCommons ምንጭ በ[[c:User:Krd|Krd]] ዕጅ ጠፍቷል! ምክንያቱም፦ [[:c:Commons:Deletion requests/File:GBK Complex at night.jpg|]] 392070 wikitext text/x-wiki '''ጌሎራ ቡንግ ካርኖ ዋና ስታዲየም''' ([[ኢንዶኔዥኛ]]: ''Stadion Utama Gelora Bung Karno'') ; በጥሬው "Bung Karno Sports Arena Main ስታዲየም")፣ ቀደም ሲል '''ሴናያን ዋና ስታዲየም''' እና '''Gelora Senayan ዋና ስታዲየም''' ፣ በማዕከላዊ [[ጃካርታ]] ፣ [[ኢንዶኔዥያ]] ውስጥ በጌሎራ ቡንግ ካርኖ ስፖርት ኮምፕሌክስ መሃል ላይ የሚገኝ ሁለገብ ስታዲየም ነው። በአብዛኛው ለ[[እግር ኳስ]] ግጥሚያዎች ይውላል። ስታዲየሙ የተሰየመው በወቅቱ የኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት በነበሩት በ[[ሱካርኖ]] ስም ነው ፣ እሱም የስፖርት ውስብስቡን የመገንባት ሀሳብ ቀስቅሷል። ከ 1962ቱ የእስያ ጨዋታዎች በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፈት ስታዲየሙ 110,000 የመቀመጫ አቅም ነበረው። በእድሳት ወቅት ሁለት ጊዜ ቀንሷል፡ በመጀመሪያ በ2006 ወደ 88,306 ለ 2007 AFC Asian Cup እና ወደ 77,193 ነጠላ መቀመጫዎች እንደ የ 2018 የእስያ ጨዋታዎች እና የእስያ ፓራ ጨዋታዎች እድሳት አካል ሆኖ ክብረ በዓላትን እና የአትሌቲክስ ውድድሮችን ያስተናግዳል ። የ 88,083 አቅም በዓለም 7ኛ ትልቁ ማህበር የእግር ኳስ ስታዲየም ያደርገዋል። በቅርብ ጊዜ በተደረገው እድሳት ምክንያት ሁሉም የቀሩት የነጠላ ወንበሮች በነጠላ ወንበሮች ተተክተዋል፣ በአለም 28ኛው ትልቁ ማህበር የእግር ኳስ ስታዲየም እና በእስያ 8ኛው ትልቁ ማህበር የእግር ኳስ ስታዲየም ነው። [[መደብ:ኢንዶኔዥያ]] [[መደብ:ስታዲየም]] hiyt91rtoh9v9xzvs3s8wpqvgtsdsjv ፍስሓ አጥላው 0 55673 392068 2026-05-08T13:39:26Z Yacob 48404 Yacob moved page [[ፍስሓ አጥላው]] to [[ፍሥሓ አጥላው]]: Misspelled title: The canonical spelling as used by the subject. 392068 wikitext text/x-wiki #REDIRECT [[ፍሥሓ አጥላው]] c7hnwbva1gbyinxfuvp3ybkxn3nncvx