ውክፔዲያ amwiki https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD MediaWiki 1.47.0-wmf.8 first-letter ፋይል ልዩ ውይይት አባል አባል ውይይት ውክፔዲያ ውክፔዲያ ውይይት ስዕል ስዕል ውይይት መልዕክት መልዕክት ውይይት መለጠፊያ መለጠፊያ ውይይት እርዳታ እርዳታ ውይይት መደብ መደብ ውይይት በር በር ውይይት TimedText TimedText talk ሞጁል ሞጁል ውይይት Event Event talk ጉግል 0 2315 392445 392297 2026-06-27T22:34:38Z 2600 etc 59410 /* የአርማ ለውጥ */ 392445 wikitext text/x-wiki {{ድርጅት_መረጃ | ድርጅት_ስም = ጉግል (Google, Inc) | ድርጅት_አርማ =Google 2026 logo.svg | ድርጅት_ዓይነት = የሕዝብ | ዋና_መሥሪያ_ቤት = [[ማውንቴን ቪው]]፥ [[ካሊፎርኒያ]]፥ [[አሜሪካ]] | የምስረታ_ቦታ = ማውንቴን ቪው | ቁልፍ_ሰዎች = [[ኤሪክ ሽሚት]]፥ ዳይሬክተር
[[ሰርጂ ብሪን]]፥ ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት
[[ላሪ ፔጅ]], የምርቶች ፕሬዝዳንት | ኢንዱስትሪ = [[ኢንተርኔት]] | ገቢ = $6.138 ቢሊዮን ([[2005 እ.ኤ.አ.]]) | የሰራተኞች_ብዛት = 4,989 (በ[[ሴፕቴምበር]] 30፥ [[2005 እ.ኤ.አ.]]) | ድህረ_ገጽ = [http://www.google.com.et www.google.com.et] | ድርጅት_ ምስል =Googleplex HQ (cropped).jpg}} '''ጉግል (Google)''' በ[[1998 እ.ኤ.አ.]] የግለሰብ ድርጅት ሆኖ ነው የጀመረው። የ[[ጉግል ፍለጋ]] ዌብሳይትን የሰራው እና የሚያስተዳድረው ይሄው ድርጅት ነው። የጉግል ዓላማ የዓለምን መረጃ ለማሰናዳት ፣ ለማቅረብና ጠቃሚ ማድረግ ነው።

== ታሪክ == === መጀመሪያ === ጉግል እንደ ፕሮጀክት ሆኖ በጃኑዋሪ [[1996 እ.ኤ.አ.]] በ[[ላሪ ፔጅ]] እና [[ሰርጂ ብሪን]] በ[[ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ]] ነው የጀመረው። የፕሮጀክቱ ሀሳብ የድረ ገጾችን ግንኙነት በማጥናት የተሻለ የፍለጋ አገልግሎት መሰጠት መቻል ነበር። ወደ አንድ [[ድረ ገጽ]] ብዙ መያያዣዎች ካሉ ያ ድረ ገጽ ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን አለው የሚለውን ሀሳብ ሞክረው ትክክለኛ መሆኑን አዩ (ይህ ዘዴ [[ፔጅራንክ]] ይባላል)፣ ለፍለጋ ድረ ገጻቸውም መሠረት ጣሉ። በእዚያ ጊዜ ፍለጋውን የሚያስተናግደው የስታንፎርድ ዌብሳይት ነበር። አድራሻውም [http://google.stanford.edu Information Technology Services:Google Search Appliance] ነበር። ያሁኑ አድራሻቸው google.com በ{{ቀን|15 September}}, [[1990]] (Sep. 15, 1997 እ.ኤ.አ.) ነው የተመዘገበው። [[ስዕል:Google in amharic language.png|thumb|የጉግል ዌብሳይት]] በማርች [[1999 እ.ኤ.አ.]] ድርጅቱ ወደ ''165 ዩኒቨርስቲ አቬኑ, [[ፓሎ አልቶ]]'' መስሪያ ቤቱን አዛወረ። ከዚያ በኋላ ሌሎች ሁለት ቦታዎች ቢቀያይሩም በ[[2003 እ.ኤ.አ.]] 1600 አምፊቲያትር ፓርክዌይ, [[ማውንቴን ቪው]] ወደ ሚገኙ ሕንጻዎች አረፉ። አብዛኛው በዚህ ጊዜ ይጠቀምበት የነበረው የ[[ኮምፒዩተር]] ዕቃዎች ከ[[ኢንቴል]] እና [[አይቢኤም]] የተለገሡ ነበሩ። በፍጥነት የሚያድገው የ[[ኢንተርኔት]] ተጠቃሚዎች ጉግልን ማድነቅ ጀመሩ። ተጠዋሚዎች ወደ ዌብሳይቱ ቀላል እና ዓይን የሚስብ ዲዛይን ተሳቡ። በ[[2000 እ.ኤ.አ.]] በፍለጋ ቃላት ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ጀመሩ። ነጻ የዌብሳይት ዲዛይን አንዲኖርና የዌብሳይቱን የመጫን ጊዜ ፈጣን እንዲሆን ማስታወቂያዎቹ የምስል ሳይሆን የጽሁፍ ብቻ ናቸው። ሌሎች ተወዳዳሪዎቹ እየወደቁ ሲመጡ ጉግል ግን እያደገ እና እየታወቀ መጣ። በ{{ቀን|4 September}}, [[1993]] (Sep. 4, 2001 እ.ኤ.አ.) የ[[ዩናይትድ ስቴትስ]] [[ፓተንት]] ቢሮ የ[[ፔጅራንክ]] ዘዴን ፓተንት ለስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሰጠ። በፌብሩዋሪ [[2003 እ.ኤ.አ.]] ጉግል [[ፓይራ ላብስ]] የሚባለውን የ[[ብሎገር]] ባለቤት ገዛ። በ[[1996|2004 እ.ኤ.አ.]] መጀመሪያ ጉግል በ[[ወርልድ ዋይድ ዌብ]] ከነበረው የፍለጋ ጥያቄዎች 84.7 በመቶውን በራሱ ዌብሳይትና በሌሎች ጓደኛ ዌብሳይቶች ያስተናግድ ነበር። በፌብሩዋሪ 2004 እ.ኤ.አ. [[ያሁ!]] ከጉግል ጋር የነበረውን ጓደኝነት አቆመ። በበዓል ቀናት፣ የአንድ ነገር መታሰቢያ ቀናት እና ልዩ ቀኖች የጉግል ዌብሳይት አስቂኝ ነገሮችን ይይዛል። ከነዚህም ታዋቂው የድርጅቱን አርማ መለወጥ ነው። ይህም 'ጉግል ዱድልስ' ይባላል። በየጊዜው አዲስ ነገር ከጉግል ይመነጫል። ጉግል ላብስ የሚባለው የዌብሳይቱ ክፍል አዲስ በሙከራ ያሉ ውጤቶችን ይይዛል። ይህም የተጠቃሚዎችን አስተያየት ስለሚያስገኘው ከተጠቃሚዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ያዳብራል። ይህም አዲሶቹን ምርቶች አሰራር ያሻሽላል። === የአርማ ለውጥ === በዓመታት ውስጥ [http://www.google.com/intl/en/stickers.html የጉግል አርማ] ተለውጧል። <gallery> Image:The first name that Google has.jpg|
ከ1995 እስከ 1997 ዓ.ም
Image:Logotipo de Google en 1997.jpg|
ከ1997 እስከ 1998 ዓ.ም
Image:googlelogo_5.jpg|
ከ1998 እስከ 1998 ዓ.ም
Image:Google logo (1997-1999).jpg|
ከ1998 እስከ 1999 ዓ.ም
Image:Logo de Google 1999-1999.jpg|
ከ1999 እስከ 1999 ዓ.ም
Image:googlelogo_current.gif|
ከ1999 እስከ 2010 ዓ.ም
Image:Google logo 2010-2013.jpg|
ከ2010 እስከ 2013 ዓ.ም
Image:Google 2013-2015.jpg|
ከ 2013 እስከ 2015
Image:Google 2015 logo.svg|
ከ 2015 እስከ 2026
Image:Google 2026 logo.svg|
ከ 2026 እስከ ዛሬ
</gallery> * የጉግል [http://www.google.com/holidaylogos.html አርማዎችን ስብስብ] ለማየት * የጉግል አርማዎችን [http://google.abrahamjoffe.com.au/ ያለቅጥ የሚያሳይ] {{Wayback|url=http://google.abrahamjoffe.com.au/ |date=20060110202337 }} ዌብሳይትም አለ * [http://www.logoogle.com/ ይህ ዌብሳይት ደግሞ] {{Wayback|url=http://www.logoogle.com/ |date=20060318104503 }} ሰዎች በጉግል የሰሩትን የውሸት አርማዎች ያሳያል === የቃል አመሠራረት === ጉግል (Google) የሚለው ቃል [[ጉጎል]] (Googol) ከሚለው የመጣ ነው። ጉጎል የሚባለው ቃል የተፈጠረው በ[[ሚልተን ሲሮታ]] በ[[1938 እ.ኤ.አ.]] በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ሚልተን [[ኤድዋርድ ካስነር]] የሚባል [[ማቲማቲሻን]] ወንድም/እሀት? ልጅ ነው። የቃሉ አጠቃቀም የጉግልን በኢንተርኔት የሚገኘውን ኢንፎርሜሽን ለማሰናዳት ያለውን ዓላማ ያንፀባራቃል። የጉግል ጠቃላይ መምሪያ ጉግልፕሊክስ (Googleplex) ይባላል። ዛሬ 'ጉግል' በአንዳንድ ቋንቋዎች እንደ ቃል ይወሰዳል። ትርጉሙም 'የዌብሳይት ፍለጋ ማድረግ' ነው። === ፋይናንስ === የጉግል የመጀመሪያ ዕርዳታ ከ[[አንዲ ቤክቶልሸም]] የተጻፈ የ$100,000 ቼክ ነው። === ዛሬ === ጉግል እያደገ ሲመጣ ትልቅ ውድድር እየሳበ ይመጣል። አንድ ምሳሌ በጉግል እና [[ማይክሮሶፍት]] መሀል ነው። ማይክሮሶፍት [[ኤምኤስኤን ሰርች]] የሚባለውን የፍለጋ አገልግሎት በየጊዜው እየለወጠ ከጉግል ጋር የተወዳዳሪ ቦታ እንዲይዝ ይሞክራል። ከዚህም በላይ ሁለቱ ድርጅቶች አንድአይነት አገልግሎቶችን ማቅረብ ጀምረዋል። ጉግል በፍለጋ አገልግሎት መሪ ስለሆነ እንደ [[ያሁ!]] ያሉትን ተወዳዳሪዎች ለማሸነፍ ይጥራል። የጉግልና ያሁ ትኩረት የተለያየ ቢሆንም ጉግል ግን አዳዲስ አገልግሎቶችን እየከፈተ ነው። በ[[ጁን 21]], [[2005 እ.ኤ.አ.]] ጉግል እንደ [[ኢቤይ]] ያሉትን የንግድ ዌብሳይቶችን ለመወዳደር ያለውን ዕቅድ አሳውቋል። == ሠራተኞች == በጉግል የመጀመሪያ ዓመታት የሠራተኞች ደሞዝ ትንሽ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ግን ዩጉግል ሼር በከፍተኛ መጠን እያደገ ስለመጣ የሠራተኞች ደሞዝ በአንጻሩ ጨምሯል። ከደሞዝ ሌላ ታዋቂነት እና ሌሎች ጥቅሞች ብዙ አመልካቾችን ስቧል። ከአንድ ላነሰ የሥራ ቦታ አንድ ሺህ አመልካቾች እንዳሉ ተገምቷል። የድርጅቱ መሥራቾችና ሌሎች ዋና ሠራተኞች አንድ የአሜሪካን ዶላር እየተከፈላቸው ይሰራሉ። እነዚህ ሰዎች የድርጅቱን ብዙ ሼር ይይዛሉ። ማርች 31 2007 የተለቀቀው መረጃ እንደሚያመለክተው ጉግል 12238 ሰራተኞች አሉት። == ቴክኖሎጂ == የጉግል አገልግሎቶች በብዙ [[ሰርቨር|ሰርቨሮች]] ውስጥ በሚገኙ ተራ ኮምፕዩተሮች ላይ ነው ያሉት። ኮምፒዩተሮቹ የ[[ሊኑክስ]] ኮምፒዩተር ፕሮግራም ይጠቀማሉ። ድርጀቱ ስለሚጠቀመው ማሽኖች ብዙ ዝርዝር ባይሰጥም በ[[1996]] ከ60,000 በላይ ኮምፒዩተሮችን እንደሚጠቀሙ ይገመታል። === ፔጅራንክ === ፔጅራንክ (PageRank) ጉግል የፍለጋ ገጾቹ ላይ የዌብሳይቶችን ቅድመተከተል ለማግኘት የሚጠቀመው ዘዴ ነው። በፔጅራንክ እያንዳንዱ ዌብሳይት ቁጥር አለው። ይህ ቁጥር ከፍ ባለ ጊዜ የዛ ዌብሳይት ደረጃ በፍለጋ ገጹ ላይ ይጨምራል። ይሄ ቁጥር የሚወሰነው ሌሎች ወደዚህ ዌብሳይት በሚያመለክቱ ዌብሳይቶች ነው። የእነዚህ ዌብሳይቶች ቁጥር ከፍተኛ ከሆነ የዚኛውም በአንጻሩ ይጨምራል። በኣንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ ይህ ኣስተማማኝ ላይሆን ይችላል። == የድርጅቱ ባሕል == === ፍልስፍና === ጉግል የራሱ የተለያዩ ዕምነቶች አሉት። አንዱ 'መጥፎ ነገር ሳትሰራ ገንዘብ ማግኘት ትችላለህ' ይላል። ሊሎች ዋና ሀሳቦች [http://www.google.com/corporate/tenthings.html እዚህ ይገኛሉ]። === 'ሃያ በመቶ' ጊዜ === ሁሉም የጉግል ኢንጅነሮች 20 በመቶ የሥራ ጊዜያቸውን እነሱ በሚስባቸው ሥራ ላይ እንዲያሳልፉ ያበረታታል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንድ ሥራዎች የጉግል ሌላ አገልግሎት ይሆናሉ። === ጉግልፕሌክስ === የጉግል መጥላይ መምሪያ ጉግልፕሌክስ (Googleplex) ይባላል። ይህ ቦታ ለሠራተኞች የተለያዩ መዝናኛዎችን ያቀፈ ነው። ከነዚህም ውስጥ የአካል ማጎልመሻ ክፍል፣ የተለያዩ ስፖርቶች፣ የተለያዩ ምግብና መጠጦች ይጠቀሳሉ። == የስራ ትብብር == የሚከተሉት የሥራ አጋሮች ናቸው፦ * [[ናሳ]] * [[ሰን ማይክሮሲስተምስ]] * [[ሞዚላ]] == ዓለምአቀፍ == ጉግል ከደርዘን በላይ በሚሆኑ ሀገሮች [http://www.google.ie/intl/en/corporate/address.html ቢሮዎች] አሉት። የተለያዩ ሀገሮች የተለያየ ሕጎች ስላሏቸው ጉግል ሁሉንም ለማስማማት ይሞክራል። == የፍለጋ ዓይነቶች == * ምስሎች (Images) - ይህ በኢንተርኔት ላይ ያሉ ምስሎችን ብቻ ለመፈለግ ያገለግላል * የውይይት መድረኮች(Groups) - የመወያያ [[ግሩፕ|ግሩፖችን]] ለመፈለግ * [[ጉግል ዜና|ዜና]] (News) - ከተለያዩ ምንጮች ዜናን ለማንበብ * ፕሮዳክት ፍለጋ (Product Search) (የድሮ "ፍሩግል" Froogle) - ይህ ድረ-ገጽ ተጠቃሚዎች በኢንተርኔት ዕቃ እንዲገዙ ያስችላል። [[ፍሩግል]]ን ይዩ * ሎካል (Local) - በአቅራቢያዎ ያሉ ሱቆችንና ሌሎች የንግድ ቦታዎችን ለመፈለግ ያገለግላል * እርዝ (Earth) - የዓለም የሳይተላይት ፎቶዎችን የሚያሳይ ፕሮግራም ወደ ኮምፒዩተሮ መጫን ይችላል * ዴስክቶፕ (Desktop) - በኮምፒዩተሮ ላይ ያሉትን ሰነዶች (ፅሁፍ፣ ፎቶ፣ ድምፅ፣ ምስል) ለመፈለግ * ቪዲዮስ (Videos) - በኢንተርኔት ላይ ያሉ ቪዲዮችን ለመፈለግ * ብሎግስ (Blogs) - በኢንተርኔት ላይ ያሉ [[ብሎግ|ብሎጎችን]] ለመፈለግ * ስኮላር (Scholar) - ትምህርታዊ ጽሁፎችን ለመፈለግ * ፋይናንስ (Finance) - የንግድ መረጃ፣ ዜና እና ሰንጠረዦች ለመፈለግ * ካርታ (Maps) - ካርታዎችንና የመንጃ መመሪያዎችን ለማየት == የውጭ መያያዣዎች == * [http://www.google.com Google] - የጉግል ዌብሳይት * [http://www.google.com/intl/am/ Google] - የጉግል ዌብሳይት በአማርኛ * {{Cite journal|last=Brin|first=Sergey|author-link=Sergey Brin|last2=Page|first2=Lawrence|author-link2=Larry Page|year=1998|title=The anatomy of a large-scale hypertextual Web search engine|url=http://infolab.stanford.edu/pub/papers/google.pdf|url-status=live|journal=Computer Networks and ISDN Systems|volume=30|issue=1–7|pages=107–117|citeseerx=10.1.1.115.5930|doi=10.1016/S0169-7552(98)00110-X|issn=0169-7552|archive-url=https://web.archive.org/web/20150927004511/http://infolab.stanford.edu/pub/papers/google.pdf|archive-date=September 27, 2015|access-date=April 7, 2019}} * {{cite journal |last=Barroso |first=L.A. |last2=Dean |first2=J. |last3=Holzle |first3=U. |date=April 29, 2003 |title=Web search for a planet: the google cluster architecture |journal=IEEE Micro |volume=23 |issue=2 |pages=22–28 |doi=10.1109/mm.2003.1196112 |issn=0272-1732 |quote=We believe that the best price/performance tradeoff for our applications comes from fashioning a reliable computing infrastructure from clusters of unreliable commodity PCs.|url=https://semanticscholar.org/paper/8db8e53c92af2f97974707119525aa089f6ed53a }} [[መደብ:ጉግል]] 81eno5az5va889uo3fdm3u8namcfiky የአፍሪካ ቀንድ 0 51370 392444 380587 2026-06-27T20:51:21Z Dagio lol 55597 392444 wikitext text/x-wiki '''የአፍሪካ ቀንድ''' [[ኢትዮጵያ]] ሶማልያ ኤርትራ ጅቡቲ ናቸው ከፊል የምስራፍ አፍሪካ አገራትን ይይዛል ከ 160 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖርበታል ተብሎ ይገመታል:: [[File:የአፍሪካ ቀንድ ካርታ.png|thumb|300px|የአፍሪካ ቀንድ ካርታ]] 5ufpll2coz2u0bg7go5blvmmwdlrk6v አባል:PrinceAzuka131 2 55733 392443 2026-06-27T14:06:53Z PrinceAzuka131 59402 Created my user page 392443 wikitext text/x-wiki Hello. i58dgc9lb8rjd4uc54d7lh6m5d22aep