ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.47.0-wmf.24
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
ሞጁል
ሞጁል ውይይት
Event
Event talk
ቶቤል
0
18891
395258
349199
2026-10-26T01:56:33Z
RitaLem
61471
/* ልማዶች ስለ ቶቤል መንግሥት በእስፓንያና በፖርቱጋል ዙሪያ */
395258
wikitext
text/x-wiki
'''ቶቤል'''፣ [[ዕብራይስጥ]]፦ תובל /ቱባል/፣ በ[[ኦሪት ዘፍጥረት]] 10 መሠረት የ[[ያፌት]] ልጅና የ[[ኖኅ]] ልጅ-ልጅ ነበረ። ከዚህ በላይ በ''[[ትንቢተ ሕዝቅኤል]]'' 38፡2-3፣ 39፡1 ቶቤል ይጠቀሳል።
==የተለያዩ ልማዶች ስለ ቶቤል መታወቂያ==
በ[[1ኛው ክፍለ ዘመን]] ዓ.ም. የ[[አይሁድ]] ሊቅ [[ፍላቪዩስ ዮሴፉስ]] እንዲህ ብሎ ጻፈ፦ «ቶቤል የቶቤላውያን (ጦቤሌስ) አባት ሆነ፤ አሁንም [[ኢቤራውያን]] (ኢቤሬስ) ይባላሉ።» ይህ በ[[አናቶሊያ]]ና በኋላ በ[[ካውካሶስ ተራሮች]] የተገኘ ሕዝብ ነበር። የካውካሶስ ኢቤራውያን ሕዝብ ከዛሬው [[ጂዮርጂያ]] ወላጆች መካከል ነበሩ።
የ[[ክርስትና]] ጳጳሳት [[አውስታጥዮስ ዘአንጥዮኪያ]] (330 ዓ.ም. ግድም) እና [[ቴዎዶሬቶስ]] (450 ዓ.ም. ግድም) ደግሞ ይህንን ታሪክ ተቀበሉ። ዳሩ ግን [[ጀሮም]] (400 ዓ.ም. ግድም)፣ [[ኢሲዶር]] (635 ዓ.ም. ግድም) እና [[ነኒዩስ]] (830 ዓ.ም. ግድም) እንዳሉት፣ የቶቤል ተወላጆች ኢቤራውያን ብቻ ከመሆናቸው በላይ፣ [[ጣልያ]]ውያን (የጥንት ጣልያን ኗሪዎች) እና [[እስፓንያ]]ውያን ከቶቤል ተወለዱ። (የድሮ እስፓንያ ሰዎች ደግሞ «ኢቤራውያን» ተባሉ።) ቅዱስ [[አቡሊድስ]] ሌላ ልማድ ዘገበ፤ የቶቤል ዘሮች «ሄታሊ» (ወይም በአንዳንድ ቅጂ [[ተሰላውያን]]) እንደ ሆኑ ጻፉ። የ[[ሱርስጥ]] ጽሑፍ ''[[መጽሐፈ ንብ]]'' (1214 ዓ.ም. ግድም) ቶቤል የ[[ቢታንያ]] ሰዎች አባት እንደ ነበር ይላል።
[[የኬጥያውያን መንግሥት]] ከወደቀ በኋላ (1190 ዓክልበ. ግድም) በአናቶሊያ [[ታባል]] የተባለ መንግሥት ተገኘ፤ ከቶቤል ልጆች እንደ ወጣ የሚያምኑ አሉ። እንዲሁም ጎረቤቶቻቸው [[ሙሽካውያን]] ከ[[ሞሳሕ]] እንደ ወጡ ይታመናል። ከዚህም ዘመን በኋላ ግሪኮች [[ቲባሬኒ]] የሚባል ሕዝብ በአናቶሊያ ያውቁ ነበር።
===ልማዶች ስለ ቶቤል መንግሥት በእስፓንያና በፖርቱጋል ዙሪያ===
በአንድ [[ካታሎኒያ]] (ምሥራቅ እስፓንያ) ተውፊት ዘንድ፣ የያፌት ልጅ ቶቤል ከ[[ኢዮጴ]] (አሁን [[ተል አቪቭ]]) ከቤተሠቡ ጋር በመርከብ ወደ እስፓንያ [[ፍራንኮሊ ወንዝ]] ከ[[ባቢሎን ግንብ]] ውድቀት በኋላ 12 ዓመት ደረሰ፤ በዚያም ስለ ልጁ «ታራሆ» ስም ከተማ መሠረተ (የአሁን [[ታራጎና]])። ከዚያ ወደ [[ኤብሮ ወንዝ]] ወጣ፤ ይህም የሁለተኛው ልጅ «[[ኢቤሩስ|ኢቤር]]» ስም አለው፣ [[አምፖስታ]]ን እዚያ ሠራ። የሦስተኛው ልጁ ስም «ሰምፕቶፋይል» ይባላል። ኖህ (ወይም የኖህ 4ኛው ልጅ [[ያኑስ]]) ከመቶ አመት በኋላ እዚህ እንደ ጎበኛቸው ይጨምራል። በዚህ ተውፊት፣ ቶቤል ለ155 አመት በእስፓንያ ነገሠ፣ ወደ [[ማውሬታኒያ]]ም (አሁን [[ሞሮኮ]]) ለመስፋፋት ሲል ሞተና ልጁ ኢቤር ተከተለው። ከዚህ በላይ [[ራቬና]] በጣልያ፣ [[ሴቱባል]] በ[[ፖርቱጋል]]፣ [[ቶሌዶ]]፣ [[ካስትሮ-ኡርዲያሌስ]] (ሴት ልጁ [[ሳውሚራ]] የተወለደችበት) እና ብዙ ሌሎች ከተሞች በእስፓንያ<ref>ከነዚህም ውስጥ [[ቱዴላ]]ና [[ታፋላ]] ይጠቀሳሉ።</ref> ሁላቸው በቶቤል ያፌት እንደ ተመሠረቱ የሚሉ ልማዶች አሉ። በተጨማሪ፣ የቶቤል ሚስት ስም «ኖያ» እንደ ነበር፣ በ[[ሳን ቪንሴንቴ ርእሰ ምድር]] ፖርቱጋል እንደ ተቀበረ፣ ወይም በመሞቱ 65፣000 ተወላጆች እንደ ነበሩት የሚሉ ልማዶች አሉ። ንጉስ ቶቤል ሕግጋቱን በ[[ከላውዴዎን]] ቋንቋ አወጣ፤ የ1ዱ አመት ልክ በ365 ቀኖች እና 6 ሰዓቶች አደረገው፤ የቤትንም አሠራር፣ እህልንም ወደ ዳቦ መጋገር፣ ወዘተርፈ ኑሮ ዘዴ ለሕዝቡ እንዳስተማረ ይባላል።<ref>[http://books.google.com/books?id=CFqRVdvQIgsC&pg=PA3#v=onepage&q&f=false ''የእስፓንያ ኣጭር ታሪክ'' (1692 ዓ.ም. በእንግሊዝኛ ታተመ)]</ref>
የነዚህ ትውፊቶች ምንጭ [[አኒዮ ዳ ቪቴርቦ]] በ[[1490]] ዓ.ም. ያሳተመው ''[[ሀሣዊ ቤሮሦስ]]'' የተባለው ሰነድ ይመስላል፤ ይህ ጽሑፍ ግን ባብዛናው እንደ እውነተኛ ታሪክ አይቆጠረም። ነገር ግን ከዚያ በፊት በ[[አራጎን]] መምህር-ንጉስ [[4 ፔድሮ]] (1360 ዓ.ም. ግድም) መሠረት ቶቤል መጀመርያ በእስፓንያ የሰፈረ ሰው ነበር፣ ጀሮምና ኢሲዶርም እንደ ጻፉ እቤራውያን ከርሱ ተወለዱ፣ በቀድሞ «ሴቱባሌስ» ተብለው በኤብሮ ወንዝ ሠፈሩ፣ በኋላም ስለዚያ ወንዝ ስማቸውን ወደ «ኢቤራውያን» ቀየሩ። እንዲሁም በ1270 ዓ.ም. ግድም የጻፉት የ[[ካስቲል]] መምህር-ንጉሥ [[10 አልፎንሶ]] ተመሳሳይ አፈ ታሪክ አቀረቡ፤ በርሳቸው ጽሁፍ ግን ቶቤል በ[[ፒሬኔስ ተራሮች]] ውስጥ በአስፓ ተራራ ሠፈረ፤ «ሴቱባሌስ» የሚል ስም መጀመርያ ክፍል ከ«ሴቱስ» መጥቶ ትርጉሙ ነገድ ማለት መሆኑን ጨመሩ። በሳቸው ዘንድ ስማቸው በኋላ «ሴልቲቤራውያን» ([[ቄልቲቤራውያን]]) ሆነ።
ከዚህም በፊት በ740 ዓ.ም. ያህል የጻፈው ታሪክ ጸሐፊ [[አቡልቃሲም ታሪፍ አበንታሪክ]] እንዳለው፣ የያፌት ልጅ ቶቤል (ወይም «ሴም ቶፋይል») እስፓንያን በ3 ልጆቹ መካከል አካፈለው፤ በኲሩ ታራሆ ወደ ስሜን-ምሥራቅ ያለውን ክፍል (ታራሆን፣ በኋላ አራጎን) ተቀበለው። ሁለተኛው ልጅ፣ ዳግማዊ ሴም ቶፋይል፣ በምዕራብ በውቅያኖስ አጠገብ ያለውን ክፍል (ሴቱባል) ወረሰ፤ ታናሹም ኢቤር በምሥራቅ በሜድትራኔአን አጠገብ ያለውን ክፍል (ኢቤሪያ) ተቀበለ። ከዚያ ቶቤል ለራሱ «ሞራር» የተባለ ከተማ ሠራ፣ ይህም አሁን [[ሜሪዳ፣ እስፓንያ]] ነው። አበንታሪክ ይህን ዝርዝር ከከተማው ዋና መግቢያ በር በላይ ከተገኘው ድንጊያ ተቀርጾ እንዳነበበው ወደ [[አረብኛ]]ም እንዳስተረጎመው ይለናል።
በስሜን እስፓንያ በሚገኘው [[ባስክ]] ብሔር በኩል ደግሞ የባስክ ሊቅ [[ፖዛ]] ([[15ኛው ክፍለ ዘመን]] ዓ.ም.) የጻፈው ቶቤል የባስኮች (የኢቤራውያንም) አባት እንደ ነበር ነው። የፈረንሳይ ባስክ ጸሐፊ [[ኦጉስተን ቻሆ]] ([[19ኛው ክፍለ ዘመን]] ዓ.ም.) «የአይቶር ተውፊት» አሳተመ፤ የባስኮች አባት [[አይቶር]] ከቶቤል ዘር እንደ ነበር ይላል።
{{S-start}}
{{Succession box
|before= የለም (አዲስ መንግሥት)
|title=የቱባሊያ ([[ኢቤሪያ]]) ንጉሥ
|years=2420-2265 ዓክልበ. ግድም <br>(አፈ ታሪክ)
|after= [[ኢቤሩስ]]}}
{{end}}
[[መደብ:የእስፓንያ አፈታሪካዊ ነገሥታት]]
===የአይሁድ ረቢዎች ልማዶች ስለ ቶቤል በጣልያን===
በአይሁድ ረቢዎች ምንጮች የቶቤል ልጆች ስሞች ይለያያሉ። በ[[ሀሣዊ ፊሎ]] (62 ዓ.ም. ግድም) ልጆቹ «ፓናቶባ» እና «ኤቴባ» ሲሆኑ፣ «ፔዔድ» የሚባል አገር ለርስታቸው ተሰጡ። በመካከለኛ ዘመን የታየው [[የይራሕሜል ዜና መዋዕል]] ልጆቹን «ፋንቶንያ» እና «አቲፓ» አገራቸውም «ፓሃጥ» ይላቸዋል። በሌላ ሥፍራ ይህ መጽሐፍ ከጀሮም የመጣ መረጃ አለው፤ የቶቤል ልጆች በኢቤርያና እስፓንያ ሠፈሩ ይላል። በሌላ ሥፍራ እንደገና ከ[[ዮሲፖን]] (950 ዓ.ም. ግድም) የወረደ ትውፊት አል። በዚህ ትውፊት የቶቤል ልጆች በ[[ቶስካና]] (የጣልያን ክፍል) ሠፈሩ፤ «[[ሳቢኖ]]» የተባለ ከተማ ሠሩ። የ[[ኪቲም]] ([[ያዋን]]) ልጆች ግን በዚህ አጠገብ በ[[ካምፓንያ]] ክፍላገር ከተማቸውን «ፖሶማንጋ» ሠሩ። [[ቲቤር ወንዝ]] በመካከላቸው ጠረፋቸው ሆነ። ኪቲሞች ግን የሳቢኖ ሴቶች በግድ ከያዙ በኋላ ወደ ጦርነት ሔዱ። ኪቲሞች ለቶቤል ልጆች የጋራ ክልሶቻቸውን ባሳያቸው ጊዜ ጦርነቱ ተጨረሰ። ይህም ትውፊት በአጭሩ በ[[ሠፈር ሀያሻር]] ይገኛል፤ በዚያም የቶቤል ልጆች «አሪፒ»፣ «ኬሴድ»ና «ታዓሪ» ይባላሉ።
===የቶቤል ተወላጆች ካዝሮችና ስላቮች ሆኑ የሚለው ሌላ የእስላም ሃልዮ===
የ[[አረብኛ]] መዝገበ ቃላት «ታጅ አል-አሩስ» (በአል-ዙባይዲ፣ [[1782]] ዓ.ም.) እንደ ዘገበው፣ አንዳንድ የ[[እስላም]] ደራሲ [[ካዛሮች]] (በአሁኑ [[ሩስያ]] የኖሩ) ከሞሳሕ እንደ ተወለዱ ሲያምኑ፣ ሌሎች ግን ካዛሮችና [[ስላቮች]] ከወንድሙ ቶቤል እንደ ተወለዱ ይላሉ።<ref>''D.M. Dunlop, ''History of the Jewish Khazars'' 1954, p. 13.</ref>
==ነጥቦች==
{{Reflist}}
== ዋቢ መጽሐፍ ==
*[http://books.google.es/books?id=fghXAAAAMAAJ&pg=PA41&lpg=PA41&dq=idubeda+tubal&source=bl&ots=7_dOkCVgtp&sig=WUdYtLcEZb6696VCM5QdD9_SGao&hl=ca&sa=X&oi=book_result&resnum=2&ct=result#PPR1,M1 Electronic edition of G. Pujades, ''Crónica Universal del Principado de Cataluña''] {{es}}
{{የኖህ ልጆች}}
[[መደብ:የኖህ ልጆች]]
lv64353j54saosjod4lngbyrvaiqwkk
ብሪጉስ
0
30941
395259
315424
2026-10-26T01:56:57Z
RitaLem
61471
395259
wikitext
text/x-wiki
[[ስዕል:Heraldic Sign of the King of Castile (1171-1214).svg|thumb|100px|የካስቲል ምልክት -በብሪጉስ እንደ ተፈጠረ ይሚል ትውፊት አለ]]
'''ብሪጉስ''' በ[[እስፓንያ]] [[አፈ ታሪክ]] ዘንድ ከ[[ዩቤልዳ]] ቀጥሎ የ[[ኢቤሪያ]] 4ኛው ንጉሥ ነበረ። የዩቤልዳ ልጅ ሆኖ ለ52 ዓመታት እንደ ነገሠ ይባላል (ምናልባት 2162-2109 ዓክልበ. ግድም)። በአንዳንድ ምሁር ዘንድ እሱ መጀመርያ ወርቃማ አምባ በቀይ ጋሻ ላይ የነበረው በኋላ [[የካስቲል መንግሥት]] አርማ ፈጠረ።<ref>[http://books.google.com/books?id=CFqRVdvQIgsC&pg=PA4&dq=tubal+%2Biberus&hl=en#v=onepage&q=tubal%20%2Biberus&f=true A brief history of Spain (የእስፓንያ ታሪክ ባጭሩ) 1700 እ.ኤ.አ.] {{en}}</ref>
[[ዮሐንስ አቬንቲኑስ]] በ[[ጀርመንኛ]] ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ ዩባልዳ ያለ ወራሽ ወንድ ልጅ አርፎ ነበር፣ የ[[ጀርመን]] ንጉሥ የ[[ኢንጋይዎን]] አለቃ ብሪጉስ ወይም ብሪጎ ግን ሴት ልጁን አግብቶ የኢቤሪያን ዙፋን ወሰደ። እርሱ የመሳይ ([[ሞሳሕ]]) ልጅ ፣ የ[[ብሪጋውያን]] አባትና በ[[ቱዊስኮን]] ዘመን የ[[ሞይስያ]] አገረ ገዥ ሆኖ ይለዋል። በኢንጋይዎን ዘመን ታላቅ ከተማ በአርጽቡርግ (አሁን [[ቬልተንቡርግ ገዳም]] በ[[ኬልሃይም]] [[ጀርመን]]) ሠርቶ ነበር፣ እንዲሁም ብሪጋንቲዮን ([[ብሬገንጽ]]) በ[[ኮንስታንጽ ሃይቅ]] በ[[ኦስትሪያ]] ሠራ። በብሪጉስ ዘመን በኢቤሪያ ላይ፣ [[አማዞኖች]] የታባሉት ሴት ወታድሮች በንግሥታቸው [[ሚሪና]] ሥር ከ[[ሊብያ]] ዘምተው ዛቻ በኢቤሪያ ላይ እንዲሁም በመላው አውሮፓ ላይ ጣሉ ይለናል።
በ[[እስፓንያ]]ና በ[[ፖርቱጋል]] ብዙ ቦታዎች በጥንት -ብሪጋ የሚለው መድረሻ በስማቸው ላይ ስለ ነበር፣ በብሪጉስ ዘመን እንደ ተሠሩ የሚል ልማድ አለ። ከነዚህም ውስጥ፦
[[ስዕል:Prehispanic languages.gif|thumb|left|250px|በ -ብሪጋ የሚጨረሱ ጥንታዊ ቦታዎች በዚህ ካርታ በምዕራቡ (አረንጓዴና ጥላ-ሐምራውዊ ክፍሎች) ይታያሉ]]
*አቦብሪጋ - [[ባዮና]]
*ኔሜቶብሪጋ - [[አ ፖብራ ዴ ትሪቬስ]]
*[[ብሪጌኩም]] - [[ቤናቬንቴ፣ ዛሞራ]]
*አማሎብሪጋ - [[ሜዲና ዴ ሪዮ ሴኮ]]
*ዴሶብሪጋ - [[ኦሶርኖ ላ ማዮር]]
*[[ዴዮብሪጉላ]] - [[ታርዳሖስ]]
*[[ቄሣሮብሪጋ]] - [[ታላቬራ ዴ ላ ሬና]]
*[[ሴጎብሪጋ]] - [[ሴሊሴስ]]
*[[ኔርቶብሪጋ]] - [[ላ አልሙኒያ ዴ ዶኛ ጎዲና]]
*[[ኔርቶብሪጋ ኮንኮርዲያ ዩሊያ]] - [[ፍሬኄናል ዴ ላ ሲዬራ]]
*[[አርኮብሪጋ]] - [[ሞንሬያል ዴ አሪዛ]]
*[[ኬንቶብሪጋ]] - [[ብሪዌጋ]]?
*[[አውጉስቶብሪጋ]] - [[ታላቬራ ላ ቪዬሓ]]
*[[ዩሊዮብሪጋ]] - [[ሬቶርቲዮ (ካምፖ ዴ ኤንሜዲዮ)|ሬቶርቲዮ]]
*[[ዴዮብሪጋ]] - [[ሚራንዳ ዴ ኤብሮ]]
*[[ሙንዶብሪጋ]] - [[ሙኔብረጋ]]
*[[ፍላቪዮብሪጋ]] - [[ካስትሮ-ኡርዲያሌስ]]
*[[ኤቤሮብሪጋ]] - [[ታላቫን]]
*[[ሚሮብሪጋ]] - [[ካፒያ፣ ባዳሖዝ]]
በ[[ፖርቱጋል]]፦
*[[ሚሮብሪጋ]] - [[ሳንቲያጎ ዴ ካሰም]]
*[[ላኮብሪጋ]] - [[ላጎስ፣ ፖርቱጋል]]
*[[ታላብሪጋ]] - [[ላማስ ዶ ቩጋ]]፣
*ላንጎብሪጋ - [[ፊያይስ]]
*ኮሩምብሪጋ፣ [[ኮኒምብሪጋ]] - [[ኮይምብራ]]
*አራብሪጋ
*አውብሪጋ
*አክሳብሪካ - [[ሐብረጋስ]]
*ብሪጋንቲያ - [[ብራጋንሳ]]
*ካይቶብሪጋ - [[ሴቱባል]]
*ካላምብሪጋ - [[ቫሌ ዴ ካምብራ]]
*ኮታዮፕብሪጋ - [[አልሜዳ]]
*ኤላኔዮብሪጋ
*ኤርኮብሪጋ
*ኤቶብሪኮ
*ሄራብሪካ
*ሎንጎብሪጋ - [[ሎንግሮይቫ]]
*ሉብሪጎስ - [[ቪላ ሬያል]]
*ሜድሮብሪጋ - [[ማርቫን]]
*ሜዱብሪጋ
*ሜሪብሪጋ
*ሴሊዮብሪጋ - [[ሳን ማርቲኖ ዴ ፔድሩላይስ]]
*ታሜዮብሪጋ
*ቱንቶብሪጋ
...ወዘተ. አሉ።
{{S-start}}
{{Succession box
|before= [[ዩቤልዳ]]
|title=የ[[ኢቤሪያ]] ንጉሥ
|years=2162-2109 ዓክልበ. ግድም
|after= [[ታጉስ ኦርማ]]}}
{{end}}
<references/>
[[መደብ:የእስፓንያ አፈታሪካዊ ነገሥታት]]
ovmsravca9gzp20zaoqy1mw61kpi3ie
ውይይት:ገብስ
1
55974
395257
2026-10-25T15:39:22Z
Riggus
61459
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «Can you also say https://en.wiktionary.org/wiki/ሰገም ?--~~~~»
395257
wikitext
text/x-wiki
Can you also say https://en.wiktionary.org/wiki/ሰገም ?--[[አባል:Riggus|Riggus]] ([[አባል ውይይት:Riggus|talk]]) 15:39, 25 ኦክቶበር 2026 (UTC)
ssv7b06els8k762u58x2zdywdnfajrp