ውክፔዲያ amwiki https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD MediaWiki 1.48.0-wmf.1 first-letter ፋይል ልዩ ውይይት አባል አባል ውይይት ውክፔዲያ ውክፔዲያ ውይይት ስዕል ስዕል ውይይት መልዕክት መልዕክት ውይይት መለጠፊያ መለጠፊያ ውይይት እርዳታ እርዳታ ውይይት መደብ መደብ ውይይት በር በር ውይይት TimedText TimedText talk ሞጁል ሞጁል ውይይት Event Event talk ቡና 0 8913 395302 379950 2026-11-04T08:20:11Z Túrelio 27943 ([[c:GR|GR]]) [[c:COM:Duplicate|Duplicate]]: [[File:Carte Coffea robusta arabica 2.png]] → [[File:Carte Coffea robusta arabic-2.png]] Exact or scaled-down duplicate: [[c::File:Carte Coffea robusta arabic-2.png]] 395302 wikitext text/x-wiki [[ስዕል:John Frederick Lewis 004.jpg|300px|thumb|ቡና አቅራቢዋ - 1849 ዓ.ም. ተሳለ።]] '''ቡና''' የተክል አይነትና ከዚህ ተክል ቡን የሚባል መጠጥ የሚወጣው ነው። መጀመርያ የታወቀው በ[[ኢትዮጵያ]] ሲሆን ምናልባት በዚህ የተነሳ ቡና በተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ከፋ ከሚለው ስም ጋር ተቀራራቢ የሆነ ስሞች ተስጥተውት ይገኛል (ለምሳሌ [[እንግሊዝኛ]]፦ ''coffee'' /ኮፊ/ በፈረንሳይኛ ካፌ (café)በዳች ኮፊ (koffie) በእብራይስጥኛ ካፈ (ka-feh) በስዊድንኛ ካፈ (kaffe) ወዘተ ) ምናልባት ከድሮው [[የከፋ መንግሥት]] በተዛመደ መልኩ ሊሆን ይችላል። በአንድ ትውፊት መሠረት በመጀመርያ ያገኘው ሰው [[ካልዲ]] የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ እረኛ ፍየሎቹ ፍሬውን በልተው ሲጨፍሩ ስለተመለከተ ነበር። የቡና የስነ ፍጥረት ስሙ ''Coffea arabica '' (''ኮፊ ኣራቢካ'') ሲሆን የዚህ የኢትዮጵያ ቡና ዘር በጣዕሙ ጥሩነት የተነሳ በጣም ተወዳጅ ነው። በደራሲው [[ዊሊያም ኡከርስ]] መጽሐፍ 'ኦል አባውት ኮፊ' (ስለ ቡና ኅልዮ/ምንነት) እንደተገለጸው ቡና ወደ [[የመን (አገር)|የመን]] የገባው በ[[አክሱም]] ዘመነመንግሥት በ[[517]] ዓ.ም. አካባቢ ነበር። የ[[ፋርስ]] ሃኪም [[አል-ራዚ]] ([[857]]-[[917]] ዓ.ም. የኖሩ) ተክሉን «ቡንቹም» ብሎ ምናልባት በታሪክ አንደኛው ስለ ቡና መግለጫ የመዘገበው ጸሐፊ ይሆናል። ሌላ [[እብን-ሲና]]([[972]]-[[1029]] ዓ.ም.)የተባለ ፋርስ ሀኪም ደግሞ ስለ «ቡንቹም» ጥቅም ጽፏል። የ[[ሞሮኮ]] [[ደርቡሽ]] ሼክ [[አቡል-ሀሳን አሽ-ሻዲሊ]] ([[1167]]-[[1250]] ዓ.ም.) በ[[አሰብ]] ዙሪያ ሲጓዝ ኗሪዎች ስለ ቡና መጠጥ እንደገለጹለት ይነገራል። የ[[አደን]] ሙፍቲ ሼክ [[ጃማል-አል-ዲን አል-ዳባኒ]] በ1446 ዓ.ም. ገደማ ለመጀመሪያ ጊዜ መጠጡን እንዳስገባ ተመዝግቧል። በ[[1449]] ዓ.ም. መጀመርያው [[ቡና ቤት]] «ኪቫ ሃን» በ[[ኢስታንቡል]] [[ቱርክ]] ተከፈተ። [[ስዕል:Ethcofcerm.jpg|280px|thumb|left|ቡና አፈላል ስነ ስርዓት በኢትዮጵያ]] ሆኖም በ[[1503]] ዓ.ም. የ[[ማካህ]] ይማሞች ቡና ቤት ስላልወደዱ መጠጡን ሃራም (እርም) አሉት<ref>http://www.hoboes.com/Politics/Prohibition/Notes/Coffee/</ref>። ነገር ግን የ[[ኦቶማን]] ቱርክ ሡልጣን [[1 ሰሊም]] በ[[1509]] ዓ.ም. ማካህን በ[[1516]] ዓ.ም. ይህን ድንጋጌ ገልብጦ የተቀደሰ መጠጥ አደረገው። ከዚያ በኋላ እስላሞች ቡናን በተለይ በጣም ወደዱት። ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በ[[ኢኦተቤ|ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን]] እስከ [[1881]] ዓ.ም. ድረስ ቡና እንደ ተከለከለ ዛሬ በሰፊ አይታወቅም። ከ[[1872]] እስከ [[1878]] ድረስ ቡና በመጠጥነት በኢትዮጵያ በጣም ስለ ተስፋፋ [[አጼ ምኒልክ]] ከጠጡት በኃላ በ1881 ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ሆነው [[አቡነ ማቴዎስ 10ኛ]] ቡናን አጸደቁት። ቡና ወደ [[አውሮፓ]] ለመጀመርያ ጊዜ በ16ኛ ክፍለ ዘመን ያስገቡት ነጋዴዎች ከ[[ቬኒዝ]] [[ጣልያን ]] ነበሩ። በ[[1592]] ዓ.ም. የ[[ሮማ]] [[ጳጳስ]] [[8 ቄሌምንጦስ]] ስላጸደቁት በፍጥነት ዘመናዊ መጠጥ ሊሆን በቃ ። የመጀመርያው ቡና ቤት በአውሮፓ በ[[ጣልያን]] በ[[1637]] ዓ.ም. ተከፈተ። [[አረብ|አረቦች]] ግን በጣም አጥብቀው ለምለሙ ተክል ከአረብ ዓለም እንዲወጣ ምንም ባይፈቅዱም፣ በ1600-1650 ዓ.ም. ገደማ አንድ ስሙ ሃጂ [[ባባ ቡዳን]] የሚባል [[ህንዳዊ]] እስላም ከ[[ሞቃ]] [[የመን (አገር)|የመን]] በስውር የቡና ዘር ይዞ ወደ [[ሚሶር]] ሕንድ አገር ተመለሰና ተክሉን እዚያ አበቀለው። በ[[1608]] ዓ.ም. የ[[ሆላንድ]] ሰዎች ለ [[አደን]] መጥተው ለምለም የቡና ዘር ይዘው ወደ አገራቸው ተመለሱ። በ1690ዎቹ በሆላንድ ቅኝ አገሮች በ[[ጃቫ]] (ዛሬ [[ኢንዶኔዥያ]]) እና በ[[ሱሪናም]] (ደቡብ አሜሪካ) በብዛት እንዲስፋፋ አደረጉት። በአሁኑ ጊዜ ቡና በዓለም ላይ ከሚጠጡ መጠጦች አንደኛን ስፍራ ይዟል። በተጨማሪም የቡና ቅጠል በወተት ተፈልቶ ቁጢ እንዲሁም የቡና ዘር ሽፋኑ/ቅርፊቱ ተፈልቶ የሚጠጣው አሻራ ተወዳጆች ናቸው። ቁጢና አሻራ ከኢትዮጵያ ውጪ እንደሚታውቁ መረጃ የለም። <gallery> ስዕል:Carte Coffea robusta arabic-2.png|ቡና የሚገኝባቸው አገራት ስዕል:Roasted coffee beans.jpg|ቡና ቡን ስዕል:A small cup of coffee.JPG|ቡና በስኒ </gallery> == ተመልከት == *[[ዮርባ የትዳር]] *[[ሻይ]] <references/> ==የኢትዮጵያ የቡና አፈላል ስርአት== *1,የቡና እቃ አጥበን እናቀራርባለን፦ረከቦት፣ሲኒ፣ብረት ምጣድ ወ.ዘ.ተ.... *2,ከሰል እናቀጣጥላለን *3,ቡናችንን ለቅመን እናጥብና ወደ ብረት ምጣድ አድርገን ምድጃዉ ላይ ይጣዳል *4,በመቀጠል ቡናዉ እንዳያር በመቁያ እናማስላለን *5,ቡናዉ አጋም ሲመስል ከእሳት ላይ እናወርዳለን *6,ከዛም በመቀጠል ቡናውን በሙቀጫ እስኪደቅ ድረስ እንወቅጣለን *7,ዉሀ በጀበና ምድጃዉ ላይ እንጥዳለን *8,ዉሀዉ ሲፈላ ደቀቀዉን ቡና ወደ ጀበናዉ ጨምረን በድጋሚ እንጥዳለን *9,ቡናዉ ሲንተከተክ ጀበናዉን ከእሳት ላይ አዉርደን እስኪሰክን ድረስ 5 ደቄቃ ድረስ እንቆያለን *10,በምድጃዉ ላይ በብረት ጀበና ዉሀ እንጥዳለን *11,ከዛ በእርጋታ ጀበናዉን ይዘን ወደ ሲኒዋቹ ላይ እንቀዳለን *12,ቡናዉ ሲያልቅ በብረት ጀበናዉ ላይ የጣድነውን ዉሀ ወደ ጀበናዉ ገልብጠን እንጥዳለን *13,እንደዛዉ እየተባለ እሰከ 3ተኛ(በረካ)ድረስ ይጠጣል። ለጠቅላላ እዉቀት፦1ኛ(አቦል) 2ተኛ(ሲና/ቶና) 3ተኛ(በረካ) == የውጭ መያያዣ == * [http://www.saudiaramcoworld.com/issue/199705/yemen.s.well-traveled.bean.htm መረጃ ስለ ቡና (እንግሊዝኛ)] {{Wayback|url=http://www.saudiaramcoworld.com/issue/199705/yemen.s.well-traveled.bean.htm |date=20070219003719 }} * [http://www.ethiopic.com/aplants.htm ስመ ኣትክልት Ethiopian Plant Names ከዶ/ር ኣበራ ሞላ By Dr. Aberra Molla] {{Wayback|url=http://www.ethiopic.com/aplants.htm |date=20080224151756 }} {{መዋቅር}} [[መደብ:አትክልት]] [[መደብ:መጠጦች]] neqimox63a1uq4nnz81vr39256ftmb2