አራታ

From Wikipedia

አራታ በማእከል ምስራቅ የተገኘ ጥንታዊ መንግስት ነበር። በተለይ የሚታወቀው ከሱመር ጥንታዊ አፈ ታሪክ "ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ" ነው። በዚያ አራታ ሀብታም፣ ተራራማ፣ በወንዞቹ ምንጭ ያለበት አገር ይባላል። የአራታ ንጉስ ኤንሱህከሽዳና ከኡሩክ ንጉስ ኤንመርካር ጋር እንደ ታገለ ይመዝገባሉ። ደግሞ ኢናና የምትባል ንግሥት ከአራታ ግቢ ወደ ኡሩክ ግቢ በመዛወርዋ የአንጋሽ ሚና እየተጫወተች ነው። የሁለቱም ነገሥታት ሚስት ትባላለች፣ ኋላም እንደ አምላክ ተቆጥራ የብዙዎች አማልክት ሚስት በሱመር ሀይማኖት ተባለች።

ታሪክ ሊቃውንት ሁሉ ስለ ስፍራው በአንድነት አይስማሙም፤ አብዛኞቹ ግን የአዘርባይጃንና የአራክስ ወንዝ አካባቢ እንደ ጠቀለለ የሚል አስተያየት አላቸው። ጠረፎቹ በግምት ከካውካሰስ ተራሮች ጀምሮ እስከ ዛግሮስ ተራሮች ድረስና ከካስፒያን ባህር እስከ ጥቁር ባህር (ማኦቲስ) ድረስ ተዘረጉ።

አራታ ብዙ ጊዘ የሚጠቀሰው በዚያች አራራት አገር በኋላ ዘመን በኖሩት ሃያላት፣ በማኒ፤ በኡራርቱና በሜዶን ላይ በሚነካ ጉዳይ ሲያውሩ ነው።

ግሪኩ ሄሮዶቶስ ታሪክ, የፋርስ ሕዝብ "አርታዮይ" (= አርታያውያን) ተባሉ (VII, 61. 150)። በሄሮዶቶስ ጊዜ የኖረ ሌላ ግሪክ ጸሐፊ ሄላኒኮስ ደግሞ እነዚህ "አርታያ" በሚባል አውራጃ እንደ ኖሩ የመስክራል።

በሌሎች ቋንቋዎች