ጣና ሐይቅ የአባይ (ብሉ ናይል) ወንዝ ምንጭ ሲሆን ከኢትዮጵያ አንደኛ ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። በቁጥር እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ብዙ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ባንዳንዶቹ ላይም የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች አሉ።
መደቦች: ኢትዮጵያ | መልክዐ ምድር | መዋቅሮች