ሊኑክስ
From Wikipedia
ሊኑክስ፡ ዩኒክስን የሚመስል ስርአተ ክውና ሶፍት ዌር ነው። ሊኑክስ በነፃ ከሚገኙ ሶፍት ዌሮች ግንባር ቀደም ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ነው። የምንጭ ኮድንም ማለትም ሊኑክስ የተጻፈበትን ኮድ ተጠቃሚው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊቀይረው፣ ሊጠቀመው ብሎም እንደገና ሊያሰራጨው ይችላል። የሊኑክስ ከርነል ለመጀመሪያ ጊዜ በ17 ሴፕቴምበር 1991 እ.ኤ.አ. ለህዝብ ቀረበ። ይኸውም ለኢንቴል x86 ፒሲ አርክቴክቱር የተሰራው ነበር። ከዚሀም በተጨማሪ ከርነሉ ጠቃሚ ስርአተ ክወና እንዲሆን ከጂኤንዩ ፕሮጀክት በላይብራሪዎችና በሲስተም ዩቲሊቲዎች የታገዝ ነበር። ቆይቶም ጂኤንዩ/ሊኑክስ የሚለውን ስም ተሰጥቶታል። ሊኑክስ በአመዛኙ በሰርቨሮች ውስጥ ባለው ጥቅም ይታወቃል በመሆኑም ከአይቢኤም፣ ሰን ማይክሮሲስተምስ፣ ዴል፣ ሄውሌት ፓካርድና ኖቬልን ከመሳስሉ ድርጅቶች እርዳታን ሲያገኝ ቆይቶአል። ከዚሀም በተጨማሪ ሊኑክስ በተለያዪ የኮምፕዩተር ቁሥ አካላት ላይ ማለትም ሃርድ ዌር፣ በዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች ላይ፣ በምጡቅ ኮምፒዩተርዎች ማለትም ሱፐር ኮምፒዩትር ላይ ፣ በኢምቤድድ መሳሪያዎች፣ በሞባይል ስልክዎችና በራውተርዎች እንደ ስርአተ ክወና ሆኖ ያገለግላል።
ሊኑክስ በ አሁኑ ሰአት ለተለያየ ጥቅም በአካታች ውስጥ ገብቶ ማለትም "ፓኬጅድ ሆኖ" በስርጭት ላይ ይግኛል። በዚህም ምክንያት ከርነሉ በጥቂቱ ተቀያይሮ እንገኘዋለን።
[ለማስተካከል] ታሪክ
የዩኒክስ ስርአተ ክወና የተጸነሰውና የተተገበረው እ.አ.አ በ 1960 ከዛም በ 1970 ተለቀቀ። በሰፊው መገኘቱና እንዲሁም ተጓጓዥንቱ ማለትም ፖርተብሊቲው በተለያዩ የትምህርትና የንግድ ተቋምት እንዲራባ፣ እንዲቀየር ብሎም በሌሎች ስርአት ክወናዎች ላይ የዲዛይን ተጽኖ እንዲያመጣ አስችሎታል።