ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.47.0-wmf.2
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
ሞጁል
ሞጁል ውይይት
Event
Event talk
ደማስቆ
0
3811
392122
380337
2026-05-18T04:29:15Z
Dagio lol
55597
392122
wikitext
text/x-wiki
'''ደማስቆ''' (ወይም ፡ '''ደማስቆስ''' ፤ [[አረብኛ|ዓረብኛ]] ፦ دمشق) የ[[ሶርያ]] ፡ [[ዋና ከተማ|ዋና ፡ ከተማ]] ፡ ነው ።
የሚኖርበት ፡ የህዝብ ፡ ቁጥር ፡ የአካባቢውን ፡ ኗሪ ፡ ሲጨምር 2,381,800 ሆኖ ፡ ሲገመት ፡ የራሱ ፡ የከተማው ፡ ኗሪ ፡ ቁጥር ፡ ደግሞ 1,861,900 ሆኖ ፡ ይገመታል ። ከተማው {{coor dm |33|30|N|36|19|E}} ላይ ፡ ተቀምጦ ፡ ይገኛል።
በአንዳንድ ፡ ሊቃውንት ፡ ዘንድ ፣ ደማስቆ ፡ ከሁሉ ፡ ይልቅ ፡ ረጅሙ ፡ እድሜ ፡ ያለው ፡ ከተማ ፡ ነው ። በ[[መጽሐፍ ቅዱስ|መጽሐፍ ፡ ቅዱስ]] ፡ ዘንድ ፡ በ[[አብርሃም]] ፡ ዘመን ፡ ይገኝ ፡ ነበር ። በ[[ፍላቪዩስ ዮሴፉስ|ፍላቪዩስ ፡ ዮሴፉስ]] ፡ ዘንድ ፡ በ[[አራም (የሴም ልጅ)|አራም]] ፡ ልጅ ፡ በ[[ዑፅ]] ተሠራ ። [[ሚካኤል ሶርያዊው|ሚካኤል ፡ ሶርያዊው]] ([[12ኛው ክፍለ ዘመን|12ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን]]) እና ፡ ባር ፡ ሄብራዩስ ([[አቡል-ፋራጅ]]) ([[13ኛው ክፍለ ዘመን]]) እንዳሉ ፡ ግን ፡ ዮሴፉስ ፡ ተሳተና «ሞርፎስ» ወይም «ሙሪፖስ» በተባለ ፡ [[ኬጢያውያን (መጽሐፍ ቅዱስ)|ኬጢያዊ]] ፡ ሰው ፡ ተሠርቶ ፡ ነበር ።
ደማስቆ ፡ በ[[ኤብላ]] ፡ በተገኙት ፡ [[የኤብላ ጽላቶች|የኤብላ ፡ ጽላቶች]] (2100 ዓክልበ. ግድም) «ደማሽኪ» ተብሎ ፡ ይጠቀሳል ። የ[[ሁክሶስ]] ፡ ሕዝብ ፡ በ17ኛ ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ዓክልበ. [[ግብጽ]]ን ፡ በገዙበት ፡ ወቅት ፣ ደማስቆ ፡ በ[[አሞራውያን|አሙሩ]] ፡ ግዛት ፡ ውስጥ ፡ ነበር ። በ[[አማርና ደብዳቤዎች|አማርና ፡ ደብዳቤዎች]] (1350 ዓክልበ. ገዳማ) '''ዲማስቁ''' ፡ ተብሎ ፡ በንጉሱ ፡ [[ቢርያዋዛ]] ፡ እንደ ፡ ተገዛ ፡ ይጻፋል ። ከ1100 እስከ 740 ዓክልበ. ድረስ ፡ የ[[አራም-ደማስቆ|አራም]] ፡ ከተማ-አገር ፡ ነበር ። በዚያን ፡ ጊዜ ፡ የ[[አሦር]] ፡ ንጉስ [[3 ቴልጌልቴልፌልሶር]] ፡ ያዘው ።
{{መዋቅር}}
[[መደብ:ዋና ከተሞች]]
[[መደብ:የሶርያ ከተሞች]]
[[መደብ:መጽሐፍ ቅዱስ]]
az2rzjynz8f5da3hq1x2790f7o6rgiw