ውክፔዲያ amwiki https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD MediaWiki 1.47.0-wmf.11 first-letter ፋይል ልዩ ውይይት አባል አባል ውይይት ውክፔዲያ ውክፔዲያ ውይይት ስዕል ስዕል ውይይት መልዕክት መልዕክት ውይይት መለጠፊያ መለጠፊያ ውይይት እርዳታ እርዳታ ውይይት መደብ መደብ ውይይት በር በር ውይይት TimedText TimedText talk ሞጁል ሞጁል ውይይት Event Event talk ቅልልቦሽ 0 13280 394252 382252 2026-07-15T17:55:18Z Tajujemal Muhammed 59638 /* growthexperiments-addlink-summary-summary:2|0|0 */ 394252 wikitext text/x-wiki ቅልልቦሽ የ[[ኢትዮጵያ]] ህጻናት በጠጠር የሚጫወቱት ሲሆን አጨዋወቱም አንዱዋን ጠጠር ወደአየር በማጉናት እሱዋ ባየር ላይ እያለች የተቻለን ያክል ጠጠር ከመሬት ማፈስ ነው። ባየር ላይ ያለችው ጠጠር ስትመለስ በተጫዋቹ እጅ "መቀለብ" ወይም "መያዝ" ይኖርባታል። ሳትያዝ መሬት ላይ ከወደቀች፣ ጨዋታው አለቀ ማለት ነው። ጨዋታው "ጠጠር" በመባልም ይጠራል። ብዙ አይነት የቅልልብልቦሽ ጨዋታዎች ሲኖሩ፡ በጣም የታወቀው "ዓይጥ አለብሽ" በመባባል የሚጫወቱት ነው። ልጆቹ ሁለት ወይም ሶስት ይሆኑና፡ አምስት ቆንጆ ድብልብል ጠጠሮች፡ ስፋትና ርዝመታቸው ከግማሽ ኢንች የማይበልጡ፡ ይለቅሙና መሬት ይቀመጣሉ። ቀድሞ "ብጀ" ያለ መጀመርያ ይጀምራል። ብጀ ማለት ብጀምር ማለት ነው። ያንን ለማለት እሽቅድምድም ነው።"ብቀ" ያለ ከርሱ የሚከተል ነው ማለት ነው፡፡ ብቀ ማለት ብቀጥል ማለት ነው። ሁለት ልጆች እኩል "ብቀ" ካሉ በድምጽም ቢሆን ቀድሞ "ብ!" ከአፉ የወጣው ሰው ሁለተኛነቱን ያገኛል። "ብቀጣጥል!" ያለ ሶስተኛ ነው። "[[እንጀራ]] ብጋግር!" ያለ አራተኛ ነው። አምስተኛ ካለ "ወጥ ብሰራ!" ብሎ ተራውን ያሳውቃል። በዚህ ተራ ተስማምተው ጀማሪው ይጀምራል። አጨዋወቱም አራት ደረጃ አለው፤ አራቱንም ደረጃ የሚጫወተው፡ በአንድ እጁ ብቻ ነው፦ የመጀመርያው፡ አንድዮሽ ነው። አምስቱን ጠጠሮች መሬት ላይ ይበትናል። አንዱዋን ያነሳል። ሲያነሳም ሌላ ጠጠር መጭረፍ/መንካት የለበትም፡ ከነካ ለሁለተኛው ያስረክባል ተራውን። ካልነካ ግን፡ ባነሳት ጠጠር አራቱንም፡ ተራ በተራ "ይበላል"- ማለትም፡ መብያ ጠጠሩን ወደላይ እየወረወረ፡ አንድ በአንድ በእጁ እያነሳቸው ይቀልባል። አንዱን ሲበላ፡ ሌላውን ከነካ፡ ወይም ቀድሞ የበላውን ከጣለ፡ "አጣ" ይባልና፡ ተራውን ለቀጣዩ ያስረክባል። ሁሉንም ከበላ ግን፡ ወደሁለትዮሽ ተራ ያልፋል።አ ምስቱንም ጠጠር እንደመጀመርያው ይበትናል። ሲበትን ግን በጣም እንዳይራራቁ ማድረግ አለበት። ምክንያቱም፡ ሁለቱን አንድ ላይ፡ ሁለቱን አንድ ላይ ነው የሚቀልባቸው፤ ከተራራቁ መቅለብ ላይችል ነው። ከበተናቸው በሁዋላ መብያ ጠጠሩን መርጦ ያነሳል። ከዚያም ሁለት ሁለቱን ይበላል። ሶስተኛው ተራ "እንቡጥዮሽ" ይባላል። መብያ ጠጠሩን ወደላይ ወርውሮ፡ አራቱን ጠጠሮች አንድ ላይ መሬት ላይ እንደተሰበሰቡ ደምድሞ ቁጭ ያደርጋቸውና፡ የወረወረውን ይቀልባል። ከዚያም፡ መብያውን ወደላይ ወርውሮ፡ ያስቀመጣቸውን አራቱንም በአንዴ ይበላል። አንዲት ጠጠር ከወደቀችበት አጣ ይባልና ተራውን ለቀጣዪ ያስረክባል። ከበላ ግን፡ "አይጥ" ይልና፡ በተቻለ መጠን አምስቱንም ጠጠሮች ከእጁ ጀርባ ወርውሮ ያስቀምጣቸዋል። አንዱዋ ወይም ሁለቱ ተፈናጥረው ቢወድቁ ችግር የለም። ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ከወደቀበት ግን፡ አይጡን በሌሎቹ ላይ ማስቆጠር አይችልም። ካልወደቁበት ግን፡ ከእጁ ጀርባ ወደ እጁ ፊትለፊት መልሶ ይቀልባቸውና፡ ያስቆጥራል ማለት ነው- አይጦቹን! መጀመርያ በብቀው ላይ፡ ከዚያም ሁለተኛ ዙር አንድዮሽ፡ ሁለትዮሽና እንቡጥዮሽ ተጫውቶ በብቀጣጥሉ ላይ፡ ወ ዘ ተ... እያለ እስኪያጣ ድረስ ማስቆጠሩን ይቀጥላል። ጨዋታው ለመዝናናት ጥሩ ሲሆን፡ አይጥ ባስቆጠሩ ቁጥር እየደመሩ ስለሚሄዱ፡ በዚያው [[ትምህርተ ሂሳብ|ሂሳብ]] ይማራሉ። {{መዋቅር}} [[መደብ:ጨዋታ]] j95ji4m390mqjh7ofrei681emcdro65 ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት 0 54474 394251 392419 2026-07-15T17:27:35Z Dagio lol 55597 /* */ 394251 wikitext text/x-wiki {{የቦታ መረጃ|ክፍፍል_ስም3=|ስም=ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት|ቦታ_ዓይነት=ክልል|መቀመጫ=[[ሶዶ|ወላይታ ሶዶ]]|መቀመጫ_ዓይነት=ዋና ከተማ|መሪ_ስም=ጥላሁን ከበደ|መሪ_ማዕረግ=ፕረስዳንት|መሪ_ስም2=[[ተስፋዬ ይገዙ]]|መሪ_ማዕረግ2=ምክትል ፕረስዳንት|ባንዲራ=Flag of Southern Ethiopia.png|አርማ=South Ethiopia Regional State emblem.png|ካርታ_አገር=|ካርታ_መግለጫ=|ስዕል=South Ethiopia in Ethiopia.svg|ስዕል_መግለጫ=የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በቀይ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ካርታ}} '''የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት''' ([[እንግሊዝኛ]]: South Ethiopia Regional State) በ[[ኢትዮጵያ]] ደቡባዊ ክፍል የሚገኝ ክልላዊ መንግሥት ነው። <ref>https://borkena.com/2023/08/19/ethiopias-two-new-regional-states-formed-central-ethiopia-south-ethiopia/</ref> የተቋቋመው ቀድሞ [[ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል|ከደቡብ ክልል]] በደቡባዊ ክፍል ያሉትን ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችን በማደራጀት ነሀሴ 19 ቀን 2010 በተካሄደው በተሳካ ህዝበ ውሳኔ በኋላ ነው። [[ሶዶ|ወላይታ ሶዶ]] የክልሉ የፖለቲካና የአስተዳደር ማዕከል ነው። በወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳውላ፣ ካራት እና ጂንካ ሌሎች የተለያዩ የክልል ቢሮዎች ተቋቁመዋል። <ref name=":0">{{Cite web|url=https://www.fanabc.com/archives/207796%3famp_markup=1|title=የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት ጸደቀ|accessdate=2024-06-19|archivedate=2023-11-24|archiveurl=https://web.archive.org/web/20231124021927/https://www.fanabc.com/archives/207796?amp_markup=1}}</ref> == ዋና አስተዳዳሪ == * [[Tilahun Kebede|ጥላሁን ከበደ]] ነሐሴ 19 ቀን 2010–አሁን == የአስተዳደር ዞኖች == የሚከተለው ዝርዝር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስራች እና አዲስ የተቋቋሙ ዞኖችን ያሳያል። {| class="wikitable sortable" |+በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዞኖች ! ቁጥር ! ዞን ! መቀመጫ |- | 1 | [[ዎላይታ|ዎላይታ ዞን]] | [[ዎላይታ ሶዶ|ወላይታ ሶዶ]] |- | 2 | [[ጋሞጐፋ ዞን]] | [[አርባ ምንጭ]] |- | 3 | የ[[ጎፋ ዞን]] | [[ሳውላ]] |- | 4 | [[ጌዴኦ ዞን]] | [[ዲላ]] |- | 5 | [[ደቡብ ኦሞ|ደቡብ ኦሞ ዞን]] | [[ዲሜካ]] |- | 6 | [[አሪ ዞን]] | [[ጂንካ]] |- | 7 | [[ኮንሶ ዞን]] | [[ካራት]] |- | 8 | [[ጋርዱላ ዞን]] | [[ጊዶሌ]] |- | 9 | [[ቡርጂ ዞን]] | [[ሶያማ]] |- | 10 | [[አማሮ|የኮሬ ዞን]] | [[ኬሌ]] |- | 11 | [[ባስከቶ ዞን]] | [[ላስካ]] |- | 12 | [[አሌ ዞን]] | [[ኮላንጎ]] |} == ዋቢዎች == {{Reflist}} == ውጫዊ አገናኞች == * [https://www.facebook.com/profile.php?id=100063901063190&locale= የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት] [[መደብ:የኢትዮጵያ ክልሎች]] gkpeqznuefi5yfxjb27ridh6r0urkv0 አባል:Tajujemal Muhammed 2 55738 394253 2026-07-15T18:09:41Z Tajujemal Muhammed 59638 /* */ 394253 wikitext text/x-wiki [[ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን|ኢትዮጵያ]] gywqufc5bkst3m20f16y7y1x8xoq212