ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.47.0-wmf.14
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
ሞጁል
ሞጁል ውይይት
Event
Event talk
ፌጦ
0
22819
394585
371319
2026-08-07T12:36:16Z
~2026-43566-05
60004
just added some information
394585
wikitext
text/x-wiki
[[ስዕል:Tere 1.JPG|300px|thumb|ፌጦ]]
[[ስዕል:Fetto(Aberra).jpg|thumb|ፌጦ]]
==የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ ==
== አስተዳደግ ==
በፍጥነት ይበቅላል። ፩ ወይም ፪ ሳምንት ብቻ ከተተከለ በኋላ፣ የሚበላው ቡቃያ በ5 - 13 ሴንቲሜትር ሲቆም፣ ይመረታል።
== በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር==
በብዙ አገር ለምሳሌ በ[[ኢትዮጵያ]]፣ [[ኢንግላንድ]]፣ [[ፈረንሳይ]]፣ [[ሆላንድ]]ና [[ስካንዲናቪያ]] ውስጥ፣ ለ[[ሰብለ ገበያ]] ይታደጋል።
==የተክሉ ጥቅም ==
ፌጦ ለተቀመመ ጻዕሙ አለም ዙሪያ በአበሳሰል ውስጥ ይወደዳል።
አቶ ሲገንጣለር (1960 እ.ኤ.አ.) ለፌጦ የሚከተሉት ጥቅሞች ዘግቧል፦
* ጥሬ ደረቅ ዘሮች እንደ ዱቄት ተደቅቀው ከውሃ ጋር ተቅላቅሎ የከብት ሆድ ችግር ለማከም ፤
* የዚህም ዱቄትና ውሃ ለጥፍ በሰነጣጠቀ ከንፈር፣ በፀሐይ መጠበስ፣ ለመሳሰሉም ቆዳ ችግሮች፣
* ዱቄቱም ከማር ተቀላቅሎ ለ[[አሚባ በሽታ]] ይወሰዳል።
* ለጥፉም በቆዳ ተቀቦ [[ቢምቢ]]ንና የመሳሰሉትን ለመከልከል፤
* ባለፉት ዘመናት፣ ጦረኞች በሌሊት ብርድ ለመታገስ ለሙቀት ያህል ይቀቡት ነበር።
* ለ[[ሆድ ጭብጠት]]፦ ፌጦ፣ [[ጥቁር አዝሙድ]]ና [[ጨው]] አንድላይ እንደ ሊጥ ይፈጫል፤ ለ፯ ቀን ከቦካ በኋላ ፩ ሻይ ማንኪያ በየቀኑ ለሆድ ጭብጠት፤
* ዱቄቱም ከ[[ፍትፍት]] ጋር ተቀላቅሎ [[ፌጦ ፍትፍት]] የተባለ ምግብ ይሠራል። ይህ በማለዳ እንደ ሞርሟሪ ይበላል። በ[[በጌምድር]] ባሕል በ[[ዕንቁጣጣሽ]] ዋዜማ ይበላ ነበር።
በ[[ሐረር]]፣ ፌጦ የላሞች ግት በሽታ ወይም «[[ጊጎ]]» ለማከም እንደ ጠቀመ ተዘግቧል።
በሰዎች አብዝቶ መብላት ያደረገውን የጎን ሕመም ለማከም ተጠቅሟል።<ref>[http://www.ethnopharmacologia.org/prelude2016/pdf/biblio-hg-07-getahun.pdf አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE] {{Wayback|url=http://www.ethnopharmacologia.org/prelude2016/pdf/biblio-hg-07-getahun.pdf |date=20170731133747 }} March 1976 እ.ኤ.አ.</ref>
በ2006 እ.ኤ.አ. በጥላሁን ተክለሃይማኖት በተመራ ጥናት፣ የሚከተሉት ጥቅሞች በ[[ደብረ ሊባኖስ]] ዙሪያ ተገኙ፦
* ፌጦ ዘር ተደቅቆ በውሃ ወይም በ[[ሎሚ]] ጭማቂ፣ ለ[[መጋኛ]]፣ ለሆድ ቁርጠት ወይም ለ[[ትኩሳት]] («ምች»)፣ ይሰጣል
* ለ«ምች» ደግሞ፣ ፌጦ፣ የ[[ነጭ ባሕር ዛፍ]]ና የ[[ብሳና]] ቅጠል፣ [[ዳማ ከሴ]]ና [[ጥንጁት]] ቅጠሎችም አገዶችም፤ በውሃ ተፈልተው በአፍንጫ እንፋሎቱን በመተንፈስ ነው።
* ለሆድ ቁርጠትም፦ ፌጦ በ[[ነጭ ሽንኩርት]] ልጥ መብላት፣ ወይም ፌጦ ከ[[ጤና አዳም]] ፍሬና ቅጠል ጋር መብላት፤ ወይም
* ለሰው ሆድ ቁርጠት፣ ወይም ለከብት [[ጎሎባ]]፦ ፌጦ፣ ጤና አዳም ፍሬ/ቅጠል እና የ[[ጠጅ ሳር]] ሥር መብላት
* ለከብትም ጎሎባ፦ ፌጦ፣ [[የምድር እምቧይ]]ና የ[[እንሶላል]] (Anethum foeniculum) ሥር፣ የነጭ ሽንኩርት አኩራች፣ ተደቅቆ በውሃ ለከብቱ ይሰጣል።<ref>[https://www.researchgate.net/publication/6612429_Knowledge_and_use_of_medicinal_plants_by_people_around_Debre_Libanos_Monastery_in_Ethiopia በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም] 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም</ref>
በ2013 እ.ኤ.አ. በዓቢዩ እኒየው በተመራ ጥናት፣ በ[[ፍቼ]] ወረዳ የፌጦ ዘር ዱቄት ደግሞ ለ[[ወባ]] ወይም ለአባለዘር በሽቶች ይሰጣል።<ref>[http://maxwellsci.com/print/crjbs/v6-154-167.pdf የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት] 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች</ref>
ፌጦ ልክ እንደማንኛውም መድሀኒት ከተፈላጊው መጠን (dosage) በላይ መወሰድ የለበትም።
{{መዋቅር}}
[[መደብ:የኢትዮጵያ እጽዋት]]
[[መደብ:ወባ]]
i00wcmxpum0sdlr57gkhmgbkj57mckf
ውቅሮ መድሃኔ አለም
0
23151
394587
268695
2026-08-08T11:05:20Z
Zelalem kefyalew
60016
አዲስ ታሪካዊ፣ ጂኦግራፊያዊና የኪነ-ሕንጻ መረጃዎች ተካተዋል
394587
wikitext
text/x-wiki
{{አለት ፍልፍል
|ስም = {{PAGENAME}}
|infoboxwidth= 22.8em
|ስዕል = [[ስዕል:ውቅሮ መድኃኔ አለም ወይንም ውቅሮ ላሊበላ.jpg|200px]]
|ስዕልcaption = ውቅሮ መድኃኔ አለምን እሚያካልለው ቦይ
|አገር = [[ኢትዮጵያ]]
|ዓይነት = አለት ፍልፍል
|አካባቢ = ክምር ድንጋይ
|ዓመት = ላሊበላ
|አደጋ =
|ሌላ ስም = ውቅሮ ላሊበላ
|Extension =
|locmapin = Ethiopia
|relief = 1
|latitude = 11.852
|longitude = 38.185
|map_caption = ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ
}}
'''{{PAGENAME}}''' ደብረ ሐይማኖት ውቅሮ መድኃኔዓለም ገዳም በኢትዮጵያ በደቡብ ጎንደር ዞን በጉና በጌምድር ወረዳ የሚገኝ ከአለት የተፈለፈለ ጥንታዊ ገዳም ነው።
ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ
ገዳሙ በደቡብ ጎንደር ዞን ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ደብረ ታቦር በግምት ከ'''37''' እስከ '''39''' ኪሎሜትር፣ እንዲሁም ከወረዳው ዋና ከተማ ክምር ድንጋይ '''7''' ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በወሰን ደረጃም ከክምር ድንጋይ በስተስሜን እና ከአይብ በእንቅብ አጠገብ በስተምዕራብ ይገኛል።
ታሪክና አመሠራረት
'''«'''ውቅሮ መድኃኔዓለም'''»''' የሚለው ስያሜ ከቤተክርስቲያኑ አሰራር ዘዴና ቅርጽ የተወሰደ ሲሆን፣ ትርጉሙም ከአለት የተወቀረ '''('''የተፈለፈለ''')''' ማለት ነው።
ከትውፊት አንጻር ቤተክርስቲያኑ በንጉሥ ገብረ መስቀል ላሊበላ '''('''ቅዱስ ላሊበላ''')''' ታንጾ እንደተጀመረ ይታመናል። በኋላም በ'''14'''ኛው ክፍለ ዘመን በሰይፈ ዓርዕድ ንግስና ዘመን '''(1344-1371''' ዓ'''.'''ም''')''' በአቡነ መልከ ጼዴቅ መሪነት '''400''' ወንድና '''600''' ሴት መነኮሳት ተሳታፊ በመሆን እንደተጠናቀቀ ይነገራል። በተጨማሪም በ'''13'''ኛው ክፍለ ዘመን በአጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግስት '''«'''ደብረ'''-'''ገዳም'''»''' ተብሎ ይፋዊ ዕውቅናና ስያሜ አግኝቷል።
የኪነ'''-'''ሕንጻ ቅርጽና ውስጣዊ ይዘት
የውቅሮ መድኃኔዓለም የመቅደስ ክፍል ስፋት '''20''' ሜትር በ'''15''' ሜትር ሲሆን፣ ቁመቱ '''3''' ሜትር ያህል ነው። በውስጡም፦
ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስት እና መቅደስ
ከግድግዳው ጋር የተያያዙ የቀብር ቦታዎችና የጥምቀት ክፍሎች
ልዩ ልዩ የጥንት ብራና መጻሕፍትና የቅዱሳን አጽሞች ይገኛሉ።
ሃይማኖታዊ አገልግሎትና ክብረ በዓል
ገዳሙ ለወንዶች በገዳምነት አገልግሎት የሚሰጥ መንፈሳዊ ስፍራ ሲሆን፣ ዓመታዊ ክብረ በዓሉም በየዓመቱ መጋቢት '''27''' ቀን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚመጡ ምእመናን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።{{መዋቅር}}
[[መደብ:አለት ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት]]
[[መደብ: ደብረ ታቦር]]
[[መደብ:አለት ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት]]
kd6qvkuhp1fhr5s5a3kp1tjjxtfs2g2
መለጠፊያ:-
10
36503
394586
264476
2026-08-08T10:23:10Z
PK2
3589
ወደ [[መለጠፊያ:Clear]] መምሪያ መንገድ ፈጠረ
394586
wikitext
text/x-wiki
#REDIRECT [[መለጠፊያ:Clear]]
0ilxsy8ke72ayf1pzbmishwjjblexyx