ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.47.0-wmf.21
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
ሞጁል
ሞጁል ውይይት
Event
Event talk
ቅዱስ ያሬድ
0
49116
395132
392448
2026-09-25T19:34:24Z
Mudalad
45863
removed hyperlinks linking to external page in the body text
395132
wikitext
text/x-wiki
'''ቅዱስ ያሬድ''' [[ሚያዝያ ፭]] ቀን በ[[፭፻፭]] ዓ.ም በ[[አክሱም]] ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይስሐቅ ይባላል እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ትባላለች።
ቅዱስ ያሬድ በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እንዲያሳድገውና እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡
'''ያሬድ''' ከአጎቱ ዘንድ [[መዝሙረ ዳዊት]] በሚማርበት ጊዜ ስለሚቆጣውና ስለሚገርፈው መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል ቦታ ሄዶ ተደበቀ ያም ቦታ የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ወደ አንዲት ዛፍ ስር ተጠግቶ አርፎ እያለ አንዲት ትል የዛፍ ፍሬ ለመብላት ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ሲወጣና ሲወርድ ከቆያ በኃላ በሰባተኛው ከዛፉ ላይ ወጥቶ የዛፉን ፍሬ ሲበላ ተመለከተ፡፡ ቅዱስ ያሬድ የትሉን ተስፋ አለመቁረጥ ከፍተኛ የሆነ ትጋቱን እንዲሁም ወደላይ ለመውጣት ብዙ ጊዜ እየሞከረ ቢወድቅም ከዓላማው ሳይናወጥ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበው እንደተፈጸመለት ተመልክቶ “ሰውነቴ ሆይ ግርፋትን ለምን አትታገሽም፤ መከራንስ ለምን አትቀበይም” ብሎ ሰውነቱን ከገሰጸ በኃላ ወደ መምህሩ ተመልሶ “አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝ እንደቀድሞ አስተምረኝ” አለው፡፡ መምህሩ ጌዴዋንም ተቀብሎ ያስተምረው ጀመር፡፡
ያሬድ ከተወለደ
== ጥበብና ቅዱስ ያሬድ ==
ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን አዘውትሮ እየሄደ ጥበብና እውቀትን የሚገልጽ '''[[ኢየሱስ|የጌታዬ]] [[ማርያም|እናቱ እመቤቴ ሆይ]]''' አይነ ልቦናዬን ያበራልኝ ዘንድ ለምኝልኝ እያለ ይለምን ነበር፡፡ ከዚያም በአንድ ቀን 150 መዝሙረ ዳዊት፣ መኃልየ ነቢያት፣ መኃልየ ሰሎሞን ሌሎችን እና ትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳትን አወቀ፡፡ በዚያ ዘመን ድምጽን ከፍ አድርጎ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ዜማ አልነበረም ቀስ ብሎ እንደ ውርድ ንባብ እያዜሙ ያመሰግኑ ነበር እንጂ፡፡ '''እግዚአብሔርም በያሬድ ቃልና ከፍ ባለ ዜማ መመስገን በወደደ ጊዜ''' ኅዳር 5 ቀን 527ዓ.ም በኤዶም ገነት በሥላሴ አምሳል ሦስት አእዋፍን ወደ እርሱ ላከ እነሱም በግዕዝ፣ ዕዝል እናበአራራይ ዜማ እንደዚሁ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ሦስቱ አእዋፍ ቅዱስ ያሬድ በቆመበት ቦታ ፊት ለፊት በአየርላይ ቆመው [[File:Yared.jpg|thumb|265px|መንፈስ ቅዱስ በወፍ ተመስሎ ለቅዱስ ያሬድ ዜማ ሲገልጹለት]] “ብፁዕ ያሬድ ብፅዕት ከርሥ እንተ ጾረተከ ወብፁዕት አጥባት እለ ሐፀምህረቱ ቆሞ ድምጹን ከፍ አድርጎ “ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ ብሎ በልሳነ ግዕዝ አዜመ፡፡ ይህም ማለት ዓለም ሳይፈጠር ለነበረና ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም ለሚኖር ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው ማለት ነው፡፡” ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ “ሙራደ ቃል” (የቃል መውረጃ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ይኸውም ዜማው ከሰማይ የወረደ ለመሆኑ እውነተኛ ማስረጃ ነው፡፡ ይህችንም ዜማ “አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት ነው፡፡ ይህንንም ዜማ ከፍ አድርጎ በሚያሰማ/ በሚያዜም/ ጊዜ ሰው፣እንስሳና አዕዋፍ ሁሉ እርሱ ወዳለበት ቦታ ተሰብስበው ከጣዕሙ የተነሣ መንፈስን የሚያድሰውን ልቡናን የሚያስደስተውንና አጥንትን የሚያለመልመውን ሰማያዊን ዜማ ይሰማሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ በግእዝ፣ በዕዝልና በዓራራይ ዜማውን እያስማማ እግዚአብሔርን ማመስገኑን ቀጠለ፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል የዜማውን ጣዕም ከሰሙና ከተረዱ በኋላ [[እግዚአብሔር]] ለቤተ ክርስቲያን መገልገያና ለሕዝቡ መባረኪያ የሰጣቸው መሆኑን በመገንዘብ ሊቃውንቱንና ካህናቱን “ተቀበሉትና ለቤተ ክርስቲያን መገልገያ ይኹን” ብለው አዘዟቸው።[[ስዕል:Saint-yared-1.jpg|thumb|265px|ቅዱስ ያሬድ ለንጉሡ ለዐፄ ገብረ መስቀል ዜማውን ሲያሰማ]] ነገር ግን ካህናቱና ሊቃውንቱ ምን ምልክት ዐይተን እንቀበለው ብለው መለሱላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ይግለጽልን ብለው ከታኅሣሥ አንድ ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ሰባት ቀን ሱባዔ እንዲያዝ አወጁ፡፡ ታኅሣሥ አንድ ቀን ሰኞ ዕለት ውሎ ነበርና ከሰኞ እሰከ [[እሑድ]] አንድ ሱባዔ ይዘው በየቀኑ የአክሱም ጽዮን ማርያምን ቤተ ክርስቲያን እየዞሩ አራት መቶ እግዚኦታና አርባ አንድ በእንተ ማርያም እያደረሱ ምሕላውን አካሔዱ፡፡ በሰባተኛው ቀን እሑድ ዕለተ ምሕላውን ጨርሰው ሲያሳርጉ ጌታ በዕለተ ዐርብ እንደተሰቀለ ሆኖ በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ተገለጸ፡፡ ከዚህም አያይዞ ቅዱስ ያሬድ “ዘበመስቀሉ ተቀነወ ወበነቢያት ተሰብከ መላእክት ወሊቃነ መላእክት ሰብሕዎ ኪያሁ ንሰብክ መድኅነ” ብሎ ነገረ መስቀሉን በማውሳት የወልድ ምሳሌ በሆነው በዕዝል ዜማ ዘመረ፡፡ ትርጓሜውም “በነቢያት ትንቢት የተነገረለትና በመስቀሉ ላይ የተቸነከረው ጌታ መላእክትና የመላእክት አለቆች አመሰገኑት፤ እኛም እርሱ መድኃኒት እንደሆነ እንናገራለን” ማለት ነው፡፡ በዚህ በተገለጸው ምስክርነት መሠረት ዜማው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ መሆኑ ታምኖ ከዚያን ዕለት ጀምሮ የቅዱስ ያሬድ ዜማ [[የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን]] መደበኛ መገልገያ ሆነ፡፡[[ስዕል:Styared.jpg|thumb|265px|ቤተክርስቲያን በቅዱስ ያሬድ ዜማ ሲሸበሸብ]] ከዚህም በተጨማሪ ይህ ቀን ስብከት ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ስብከት መባሉም ቅዱስ ያሬድ ዜማ ማስተማር የጀመረበት ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ትንቢት ለመፈጸሙ መታሰቢያ ስለሆነ ነው ይህም ቀን አስከ ታኅሣሥ 17 ታስቦ ይውላል፡፡
==የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች==
[[ቅዱስ ያሬድ]]ን ብቸኛ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መስራች አድርጎ ለማየት በቂ ምክንያት አለን ፡፡ እንዲያዉም የግእዝ ስነ ጽሑፍ
መስራች ከማለት ይልቅ '''የ[[ኢትዮጵያ]]''' ስነ ጽሑፍ መሥራች ልንለዉ ይገባል ፡፡
"ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ኃይሌ የቅዱስ ያሬድ ታሪክና የግእዝ ስነ ጽሑፍ ፤ 1999 ፤ ገጽ 3" በዚሁ ጥናታቸዉ እንዳብራሩት የ'''[[ግእዝ]]''' ስነ ጽሑፍን ለሁለት ልንከፍለዉ እንችላለን
ይላሉ ፡፡ ምክንያቱን ሲያስረዱ ፦ አንዱ ክፍል ከባህር ማዶ ተጽፈዉ ወደ ግእዝ የተተረጎሙትን መጻሕፍት ይይዛል ፡፡
ሁለተኛዉ ክፍል በቀጥታ በግእዝ የተደረሱትን ድርሰቶች ያጠቃልላል ፡፡
እነዚህም ፡-የቅዱስ ያሬድ፣
'''[[አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ|የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ]]''' ፣ የርቱዐ ሃይማኖት ፣ '''[[አፄ ዘርአ ያዕቆብ|የአፄ ዘረአ ያዕቆብ]]''' ፣ የዐርከ ሥሉስ ፣ የአባ ባሕርይ ድርሰቶች የሚቀድም በግእዝ ቋንቋ የተደረሰ ድርሰት እስከ አሁን አለመገኝቱን ጥናቱ ያሳያል ፡፡
ቅዱስ ያሬድ ድርሰቶችን ሲያዘጋጅ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት
ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል ፡፡
ብሉያትን ከሐዲሳት፣ከሊቃዉንት እያጣቀሰ ያለምንም ችግር የድርሰት ሥራዉን ሊያከናዉን ችሏል ፡፡
የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች መንፈሳዊ ይዘት ያላቸዉ ናቸዉ ፡፡
በድርሰቶቹ የሚታዩት የቃላት አመራረጥ ፣
የዐረፍተ ነገር አወቃቀር ፣ የሚስጥር ፣
የዘይቤ አገላለጥ ቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ የስነ-ጽሑፍ ተሰጥኦ እንደነበረዉ ለመረዳት ይቻላል፡፡
በቅዱስ ያሬድ የተደረሱት የዜማ መጻሕፍት አምስት ናቸዉ እነርሱም :
*'''ድጓ'''
*'''ጾመድጓ'''
*'''ዝማሬ'''፣
*'''መዋሥዕት'''ና
*'''ምዕራፍ'''
ናቸዉ፡፡
[[መደብ:የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች]]
{{መደብ:ተዋህዶ}}
{{መደብ:ክርስትና}}
fnx6a9wmsu4mjycjypz37xgj357rbk0
ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት - Ethio Resins
0
55889
395133
395060
2026-09-26T04:02:55Z
~2026-51674-00
60859
/* ምርቶች */
395133
wikitext
text/x-wiki
'''ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር''' '''(Ethio Resins PLC)'''፡ ማእከሉ በአዲስ አበባ ያደረገ የተፈጥሮ ሙጫ በተለይም እጣንን (Frankincense) ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች እና ወረዳዎች በመሰብሰብ፤ እጣንን በጥራት በአይነትና በመጠን በመለየት፤ እንዲሁም በማቀነባበር በተገቢው የማሸግ ሂደት በማዘጋጀት ለውጭ ገበያ (Export) የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡<ref>[https://ethioresins.com/ Home -]</ref>
== '''ምርቶች''' ==
* '''ቦስዌሊያ ፓፒሪፌራ (Boswellia papyrifera )'''፡ ከዚህ የእጣን ዝርያ የሚገኘው የእጣን ምርት በኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት በአብዛኛው ወደ ውጭ የሚላክ ሲሆን፤ ካምፓኒው ምርቶቹን የሚሰበስበው ከትግራይ፣ ጎጃም እና አዊ ዞኖች ከሚገኙ የሕብረት ሥራ ማእከላት ነው፡፡ ይህ የምርት አይነት በአብዛኛው የኢትዮጵያ እጣን ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በሥፋት ገበያ ላይ የዋለ ምርት ነው፡፡<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-papyrifera/ Boswellia Papyrifera: Ethiopian Frankincense (Gum Olibanum), Composition, Properties and Uses - Ethio Resins]</ref>
* '''ቦስዌሊያ ኔግሌክታ (Boswellia neglecta'''<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-neglecta/ Boswellia Neglecta: Ethiopian Frankincense, Composition, Origin and Uses - Ethio Resins]</ref>''')'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይኸኛውን አይነት የምርት አይነት ከደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም ቦረና አካባቢ ካሉ ገበሬዎች በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡ የዚህ ምርት ሬዚን ጠቆር ያለ እና ብራውኒሽ ሲሆን እጅግ ልዩ የሆነ አሮማቲክ መአዛ ሽታ አለው፤ ምርቱ Borena-type frankincense በመባልም በስፋት በመላው ዓለም ይታወቃል፡፡
* '''ቦስዌሊያ ሪቫ (Boswellia rivae'''<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-rivae/ Boswellia Rivae: Ethiopian Frankincense (Mirafur), Composition, Origin and Uses - Ethio Resins]</ref>''')'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይህንን ምርት ከደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በተለይም ኬንያ እና ሶማሊያ አዋሳኝ አካባቢዎች ካሉ ገበሬዎች በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ ያቀርባል::
* '''ቦስዌሊያ ኦጋዴኒሲስ (Boswellia ogadensis'''<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-ogadensis/ Boswellia Ogadensis: Ethiopian Frankincense, Composition, Origin and Uses - Ethio Resins]</ref>''')'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይሄኛውን ምርት በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ከሚገኙ የሕብረት ሥራ ማሕበራት በማስመጣት ለውጭ ገበያ ያቀርበዋል፡፡
* '''ከርቤ (Myrrh/ Commiphora myrrha)'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይህንን ምርት በኢትዮ ሶማሌ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡
* '''ኦፖፓናክስ (Scented Myrrh/ Commiphora guidottii)'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይህንን ምርት በኢትዮ ሶማሌ ክልል በተለይም አፍዴር ዞን ውስጥ ካሉ ገበሬዎች እና አቅራቢዎች በመግዛት ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡
== የቢዝነስ ሞዴል ==
ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ እጣን እና ከርቤ ምርት በሚገኝባቸው አካባቢዎች ትልልቅ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን ምርቶቹን ለሚፈልጉ የውጭ ሀገር ደንበኞች ኦርደር ሲደረግ በፍጥነት ያቀርባል፤ ምርቶቹን ገዢዎች ከድርጅቱ በዌብሳይታቸው አማካኝነት ማግኘት የሚቻል ሲሆን፣ ድርጅቱ በአሊባባ አንዲሁም በአማዞን ቢዝነስ ላይም የድርጅቱን ተወካዮች በደርጅቱ የየፕላትፎርሞቹ ኦፊሻል አካውንት ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ ገዢዎች አሊባባ ላይ በትሬድ አሹራንስ በኩል ስለሚገዙ እጅግ በጣም ሴፍ ነው፤ በኤል ሲ ደግሞ በባንክ ኦርደር ማድረግ ስለሚቻል፤ በኤፍኦቢ ጅቡቲ ማዘዝ ይቻላል እነዲሁም በኢትዮጵያ ኤርላይን ካርጎ መላክ ይችላሉ፡፡
== References ==
{{Reflist}}
kzsbug5a14p6qeozcdbbh0uu6h8x3j9
395134
395133
2026-09-26T05:25:47Z
~2026-51637-13
60860
395134
wikitext
text/x-wiki
'''ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር''' '''(Ethio Resins PLC)'''፡ ማእከሉ በአዲስ አበባ ያደረገ የተፈጥሮ ሙጫ በተለይም እጣንን (Frankincense) ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች እና ወረዳዎች በመሰብሰብ፤ እጣንን በጥራት በአይነትና በመጠን በመለየት፤ እንዲሁም በማቀነባበር በተገቢው የማሸግ ሂደት በማዘጋጀት ለውጭ ገበያ (Export) የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡<ref>[https://ethioresins.com/ Home -]</ref><ref>[https://medium.com/@roberthank/from-ethiopian-drylands-to-global-markets-the-story-behind-ethio-resins-export-d32c18b3cfe1 From Ethiopian Drylands to Global Markets: The Story Behind Ethio Resins Export | by Robert Hank | Sep, 2026 | Medium]</ref>
== '''ምርቶች''' ==
* '''ቦስዌሊያ ፓፒሪፌራ (Boswellia papyrifera )'''፡ ከዚህ የእጣን ዝርያ የሚገኘው የእጣን ምርት በኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት በአብዛኛው ወደ ውጭ የሚላክ ሲሆን፤ ካምፓኒው ምርቶቹን የሚሰበስበው ከትግራይ፣ ጎጃም እና አዊ ዞኖች ከሚገኙ የሕብረት ሥራ ማእከላት ነው፡፡ ይህ የምርት አይነት በአብዛኛው የኢትዮጵያ እጣን ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በሥፋት ገበያ ላይ የዋለ ምርት ነው፡፡<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-papyrifera/ Boswellia Papyrifera: Ethiopian Frankincense (Gum Olibanum), Composition, Properties and Uses - Ethio Resins]</ref>
* '''ቦስዌሊያ ኔግሌክታ (Boswellia neglecta'''<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-neglecta/ Boswellia Neglecta: Ethiopian Frankincense, Composition, Origin and Uses - Ethio Resins]</ref>''')'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይኸኛውን አይነት የምርት አይነት ከደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም ቦረና አካባቢ ካሉ ገበሬዎች በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡ የዚህ ምርት ሬዚን ጠቆር ያለ እና ብራውኒሽ ሲሆን እጅግ ልዩ የሆነ አሮማቲክ መአዛ ሽታ አለው፤ ምርቱ Borena-type frankincense በመባልም በስፋት በመላው ዓለም ይታወቃል፡፡
* '''ቦስዌሊያ ሪቫ (Boswellia rivae'''<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-rivae/ Boswellia Rivae: Ethiopian Frankincense (Mirafur), Composition, Origin and Uses - Ethio Resins]</ref>''')'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይህንን ምርት ከደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በተለይም ኬንያ እና ሶማሊያ አዋሳኝ አካባቢዎች ካሉ ገበሬዎች በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ ያቀርባል::
* '''ቦስዌሊያ ኦጋዴኒሲስ (Boswellia ogadensis'''<ref>[https://ethioresins.com/article/boswellia-ogadensis/ Boswellia Ogadensis: Ethiopian Frankincense, Composition, Origin and Uses - Ethio Resins]</ref>''')'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይሄኛውን ምርት በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ከሚገኙ የሕብረት ሥራ ማሕበራት በማስመጣት ለውጭ ገበያ ያቀርበዋል፡፡
* '''ከርቤ (Myrrh/ Commiphora myrrha)'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይህንን ምርት በኢትዮ ሶማሌ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡
* '''ኦፖፓናክስ (Scented Myrrh/ Commiphora guidottii)'''፡ ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት ይህንን ምርት በኢትዮ ሶማሌ ክልል በተለይም አፍዴር ዞን ውስጥ ካሉ ገበሬዎች እና አቅራቢዎች በመግዛት ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡
== የቢዝነስ ሞዴል ==
ኢትዮ ሬዚንስ ኤክስፖርት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ እጣን እና ከርቤ ምርት በሚገኝባቸው አካባቢዎች ትልልቅ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን ምርቶቹን ለሚፈልጉ የውጭ ሀገር ደንበኞች ኦርደር ሲደረግ በፍጥነት ያቀርባል፤ ምርቶቹን ገዢዎች ከድርጅቱ በዌብሳይታቸው አማካኝነት ማግኘት የሚቻል ሲሆን፣ ድርጅቱ በአሊባባ አንዲሁም በአማዞን ቢዝነስ ላይም የድርጅቱን ተወካዮች በደርጅቱ የየፕላትፎርሞቹ ኦፊሻል አካውንት ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ ገዢዎች አሊባባ ላይ በትሬድ አሹራንስ በኩል ስለሚገዙ እጅግ በጣም ሴፍ ነው፤ በኤል ሲ ደግሞ በባንክ ኦርደር ማድረግ ስለሚቻል፤ በኤፍኦቢ ጅቡቲ ማዘዝ ይቻላል እነዲሁም በኢትዮጵያ ኤርላይን ካርጎ መላክ ይችላሉ፡፡
== References ==
{{Reflist}}
rpzceozvej5men5vpaddlvvfan7ro6o