ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.47.0-wmf.21
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
ሞጁል
ሞጁል ውይይት
Event
Event talk
ጮቄ
0
50267
395146
387291
2026-09-28T17:18:53Z
~2026-52118-57
60923
/* */
395146
wikitext
text/x-wiki
አስደሳቹ ስፊውና ማራኪው '''ጮቄ''' በምስራቅ ጎጃም ውስጥ ከሚገኙ የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ዞኑ በስፋት የሚታወቅበት አስደናቂና ከፍተኛ የሆነ ተራራማ ቦታ ነው። ጮቄ በእፅዋት ብዝሀነት የታደለና ከ85 በላይ አገር በቀል እፅዋት የሚበቅልበት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ፡- [[ጅባራ]]፣ [[ጓሳ]]፣ [[አስታ]]፣ [[ቅርቅሃ]]፣ [[አምጃ]]፣ [[አሸንግድየ]]፣ [[ዝግባ]]/[[ግምይ]]/ ተጠቃሽ ናቸው። አባይን ያረገዘ ጮቄ አካባቢው የ[[አባይ ወንዝ]] የውሃ ምንጭ ሲሆን የአባይ ተፋሰስ የውሃ ማማ እንደሆናና ከአባይ 9.5% ተፋሰስ ድርሻ ያለው ተራራማ የውሃ ስፍራ ነው። እንደ አጠቃላይ ሲታይ የ[[ምስራቅ አፍሪካ]] የውሃ ማማ (East Africa water Tower) የሆነው ጮቄ የአባይ ገባር የሆኑ 273 ትናንሽ የውሃ ጅረትና ከ23 በላይ የሚሆኑ ታላላቅ ወንዞች መፍለቂያ ነው። ከታላላቅ ወንዞች መካከል [[እናት ሙጋ]]፣ [[ግልገል ሙጋ]]፣ [[ተምጫ]]፣ [[ዝምብል]]፣ [[ትልቁ አብያ]]፣ [[ትንሹ አብያ]]፣ [[ጨሞጋ]]፣ [[ጌደብ]]፣ [[ጥጃን]]፣ [[ጠፍ]]፣ [[ጦመ]]፣[[አዝዋሪ]]፣ ተጠቃሽ ሲሆኑ ከነዚህም ቢቡኝ ወረዳ ውስጥ የሚገኙት፡- ዝምብል፣ ትልቁ አብያና ትንሹ አብያ ናቸው። የጮቄ ተራራ ከባህር ወለል በላይ 4088 ሜትር አካባቢ ከፍታ ያለው በመሆኑ የ[[ጎጃም]] ጣራ ( The roof of Gojjam) በመባል ይታወቃል። የጮቄ ተራሮች በ[[ምስራቅ ጎጃም]]ና በ[[ምዕራብ ጎጃም]] ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎች ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ጠቅላላ ስፋቱም 53558 [[ሄክታር]] በላይ እንደሚደርስ ጥናቶች ያመለክታሉ። ጮቄ በጣም ሰፊ ከመሆኑም የተነሳ ገና ብዙ ያልታወቁ ዋሻዎች፣ ጥንታዊ መኖሪያዎችና ያልተዳሰሱ አስደሳች የተፈጥሮ መስህቦች አሉት ፡፡ የጮቄ አካባቢ፡- በስተ ምስራቅ [[እነማይና እናርጅ እናውጋ]]፣ በስተ ሰሜን ምስራቅ [[2 እጁ እነሴ]] በስተ ሰሜን ቢቡኝ በምዕራብ [[ማቻከል]]፣ በስተ ደቡብ [[ስናን]] እንዲሁም በስተ ደቡብ ምስራቅ [[ደባይ ጥላት ግን]] ወረዳዎች ያዋስናል። ይህ ተራራ በዋናነት በቢቡኝ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አምስት ቀበሌዎችን ያቀፈ ነው፡፡ እነሱም፡- አሩሲ መሰሳቢያ ደድ ደብረ ፅዮን ደብረ ጊዮርጊስና ወንበር ቅዱስ ዮሐንስ ቀበሌዎች በዋናነት ይገኛሉ፡፡
===የአየር ንብረት ሁኔታ===
የጮቄ አካባቢ የዝናብ መጠን ከ900- 1400 ሚ/ሜ የሚደርስ ሲሆን የአካባቢው የሙቀት መጠንም 00c አካባቢ እንደሚደርስና በተለይም በክረምት ወቅት ከሳምንት በላይ በበረዶ ይሸፈናል፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን የበረዶ ግግር እየቀነሰ የመጣበት ሁኔታ ይታያል፡፡
===የመሬት አቀማመጥ===
የጮቄ አካባቢ የመሬት አቀማመጥ 86 ከመቶ ተራራማ 1.5 ከመቶ ሸለቋማ ና 12.5 ከመቶ ሜዳማ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የጮቄ የተፋሰሱ የታችኛው ክፍል ማለትም የአብያ ወንዝ መሰል አካባቢዎችን ተከትሎ ሸላቋሚ ሲሆን በዚህ አካባቢ እንደ [[ሾላ]]፣ [[ሉል]]፣ [[ክትክታ]]፣ [[ግራር]]፣ [[ቅላባ]]ና [[አምቡስ]] በመሳሰሉ እፅዋቶች የተሸፈነ ነው፡፡ የመካከለኛው ክፍል ተራራማና ተዳፋታማ ሲሆን ይህ አካባቢ በዋናነት በአስታ የተሸፈነና አልፎ አልፎ የአዕምጃና በሌሎች የተሸፈነ ነው፡፡ የጮቄ የላይኛው አካል በአብዛኛው ሜዳማ ሲሆን ይህም በጅባራ፣ ግምይና አሸንግድየ ተክሎች የተሸፈነና አካባቢው ከፍተኛ የሆነ የግጦሽ ጫና ያለበት ነው፡፡ ከጠጠር ወደ ድጓ ፅዮን ሲጓዙ ግምይና ጅባራ የበዛበትን ድልዳላማ መሬት አልፈን የምናገኘው የፍልፈል ሜዳ ከፍተኛ ቦታን እናገኛለን፡፡ ይህ ቦታ ለቱሪስት ማረፊያነት ማገልገል የሚችል ሲሆን የአካባቢውን ገፅታ ለመመልከት የሚያስችል ከፍተኛ ቦታ ነው፡፡ የጮቄ ተራራ ልዩ ውበትና ተፈጥሮአዊ ፀጋ መላበሱ እንደተጠበቀ ሆኖ የአፍሪካ የውሃ ማማነቱን ሊቀንስ የሚያስችሉ ድርጊቶች ሲፈፀሙበት ይታያል፡፡ ለምሳሌ፡- ስድ ግጦሽ፣ የደን መጨፍጨፍና ብርቅየ የዱር እንስሳት መምናመን በአካባቢው ባሉ አርሶ አደሮች በእርሻና በመኖሪያ ቤት መወረር ይታያል፡፡ ስለሆነም ቀጣይ ይህንን ቦታ ከነውበቱ ለማስቀጠልና ለማልማት ከመንግስትም ሆነ በየደረጃው ካለው ማህበረሰብ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠውና የልማት ፕሮጀክት ሊነደፍለት ይገባል እንላለን፡፡
[[መደብ:ጎጃም]]
9nsnqzlvs08pk3trrsvur4w6009u97z