ውክፔዲያ amwiki https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD MediaWiki 1.47.0-wmf.22 first-letter ፋይል ልዩ ውይይት አባል አባል ውይይት ውክፔዲያ ውክፔዲያ ውይይት ስዕል ስዕል ውይይት መልዕክት መልዕክት ውይይት መለጠፊያ መለጠፊያ ውይይት እርዳታ እርዳታ ውይይት መደብ መደብ ውይይት በር በር ውይይት TimedText TimedText talk ሞጁል ሞጁል ውይይት Event Event talk ጥንታዊ እንግሊዝኛ 0 4057 395193 392389 2026-10-07T01:04:01Z InternetArchiveBot 35471 Rescuing 1 sources and tagging 0 as dead.) #IABot (v2.0.9.6 395193 wikitext text/x-wiki [[ስዕል:Law_of_Æthelberht.jpg|300px|thumb|«'''''ጎደስ ፌውሕ ኦንድ ቺሪቼየን ትወልቨ ዪውልደ።'''''» («የአምላክ ነዋይና የቤተክርስቲያን፣ ፲፪ እጥፍ») በማለት ከሁሉ ጥንታዊ የታወቀው የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር፣ የ[[አሰልበርህት]] ህግጋት ([[594]] ዓም)፣ ይጀምራል። ይህ በ1100 ዓም ግድም የተሠራ ቅጂ ነው።]] '''ጥንታዊ እንግሊዝኛ''' ('''Englisc''' /ኧንግሊሽ/) በ[[እንግሊዝ አገር]] ከ440 ዓ.ም. ገደማ እስከ 1100 ዓ.ም. ያሕል የተናገረ ቋንቋ ነበር። ዛሬ [[ጀርመን]]ና [[ዴንማርክ]] ከተባሉት አገሮች ፈልሰው በእንግሊዝ በተስፈሩት ሕዝብ የተናገሩበት ሲሆን የዘመናዊ [[እንግሊዝኛ]] ቀድሞ አይነት ነው። ሆኖም በቃላትም ሆነ በስዋሰው ከዘመናዊ እንግሊዝኛ በጣም ይለያል። ቅርብ ዘመዶቹ [[ጥንታዊ ፍሪዝኛ]] እና [[ጥንታዊ ሴክስኛ]] ናቸው። ጥንታዊ እንግሊዝኛ በርካታ ተመሳሳይ ቀበሌኞች ነበሩት። በተለይ በስሜን እንግሊዝ የኖሩት የ[[አንገሎች]] መነጋገርያ በደቡብ ከኖሩት ከ[[ሴክሶች]] ትንሽ ተለያየ። ከ800 ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ስሜኑ በ[[ቫይኪንጎች]] ስለተወረረ በንጉስ [[አልፍሬድ]] ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ። ቢሆንም የቫይኪንጎች ቋንቋ [[ኖርስኛ]] ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ጋር ዝምድና ነበረውና ከኖርስኛ አያሌው ቃላት ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ለምሳሌ የእንግሊዝኛ ቃላት ''sky'' /ስካይ/ (ሰማይ) ''leg'' /ለግ/ (እግር) እና ''they'' /ዘይ/ (እነሱ) የደረሱ ከኖርስኛ ነበር። በእንግሊዝ ኗሪዎች ቋንቋ (በጥንታዊ እንግሊዝኛ) እነዚህ ቃላት 'ሄዮቮን'፣ 'ሽያንካ' እና 'ሂዬ' ሆነው ነበር። የተማሩ ሰዎች (መምህራን ወይም ቄሶች) በብዛት የ[[ሮማይስጥ]] ዕውቀት ስለነበራቸው ደግሞ ከሮማይስጥ ተጽእኖ አንዳንድ ቃላት የዛኔ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ንጉሥ አልፍሬድ እራሳቸው ብዙ መጻሕፍት ከሮማይስጥ አስተረጎሙ። [[ኖርማኖች]] እንግሊዝን በ[[1059]] ከወረሩ ጀምሮ እንግሊዝኛ ከትምህርት ቤት ስለ ተከለከለ በየጥቂቱ ባሕርዩ እጅግ ተለወጠ። በጥንታዊ እንግሊዝኛ እያንዳንዱ ስም የተወሰነ ጾታ (ወንድ፣ ሴት ወይም ግዑዝ) ነበረው። ለምሳሌ ''sēo sunne'' /ሴዮ ሱነ/ (ፀሐይቱ) አንስታይ፣ ''se mōna'' /ሴ ሞና/ (ጨረቃው) ተባዕታይ፣ ''þæt wæter'' /<u>ዛ</u>ት ዋተር/ (ውኃው) ግዑዝ ነበር። == ጽሕፈት == ቋንቋው መጀመርያ [[ፉሶርክ]] በተባለው የ[[ሩን]] ፊደል ሲጻፍ ክርስትና ከተቀበለ በኋላ ግን በ[[ላቲን አልፋቤት]] ሊጻፍ ጀመረ። አንዳንድ ተጨማሪ ፈደላት እንዲህ ነበሩ: * [[ȝ]] - ይህ ፊደል (ከ[[አይርላንድኛ]] ገብቶ) እንደ 'ይ' ወይም 'ግ' ወይም 'ኅ' ሊጠቀም ይችል ነበር። * [[ð]] - ይህ ፊደል ከላቲን [[d]] ተቀይሮ እንደ '<u>ስ</u>' ወይም '<u>ዝ</u>' ሊጠቀም ይችል ነበር። * [[þ]] - ይህ ከቀድሞው ፉሶርክ ተገኝቶ ደግሞ እንደ '<u>ስ</u>' ወይም '<u>ዝ</u>' ጠቀመ። * [[ƿ]] - '[[W]]' የሚለው ፊደል ገና ስላልኖረ 'ው' ለመጻፍ በዚህ ፊደል (ከፉሶርክ ተገኝቶ) ነበር። በኋላ ዘመን ከ[[p]] (ፕ) ጋር ስላለው ተመሳሳይነት ይህ ፊደል ጠፋ። ስለዚህ የዛሬ ሊቃውንት ጥንታዊ እንግሊዝኛ የሚጽፉት በዘመናዊው 'w' ነው። == ምሳሌ == === የጌታ ጸሎት (አባታችን ሆይ) === : Fæder ure þu þe eart on heofonum, : Si þin nama gehalgod. : To becume þin rice, : gewurþe ðin willa, on eorðan swa swa on heofonum. : urne gedæghwamlican hlaf syle us todæg, : and forgyf us ure gyltas, swa swa we forgyfað urum gyltendum. : and ne gelæd þu us on costnunge, ac alys us of yfele. soþlice. : ፋደር፡ ኡረ፡ <u>ዙ</u>፡ <u>ዘ</u>፡ ኤየርት፡ ኦን፡ ሄዮቮነም፣ : ሲ፡ <u>ዚ</u>ን፡ ናማ፡ ይሃልጎድ። : ቶ፡ በኩመ፡ <u>ዚ</u>ን፡ ሪቸ፣ : ይዉር<u>ሰ</u>፡ <u>ዚ</u>ን፡ ውላ, ኦን፡ ኤዮር<u>ሳ</u>ን፡ ሷ፡ ሷ፡ ኦን፡ ሄዮቮነም። : ኡርነ፡ ይደይኋምሊቻን፡ ህላፍ፡ ሲውለ፡ ኡስ፡ ቶደይ፣ : አንድ፡ ፎርዪውፍ፡ ኡስ፡ ኡረ፡ ዪውልታስ, ሷ፡ ሷ፡ ዌ፡ ፎርዪውቫ<u>ስ</u>፡ ኡረም፡ ዪውልተንደም። : አንድ፡ ነ፡ ይለይድ፡ <u>ዙ</u>፡ ኡስ፡ ኦን፡ ኮስትኑንገ, አክ፡ አሊውስ፡ ኡስ፡ ኦፍ፡ ኢውቨለ። ሶ<u>ስ</u>ሊቸ። ==ደግሞ ይዩ== * [[:wikt:Wiktionary:የእንግሊዝኛ ቅድመ-ታሪካዊ አመጣጥ - ሷዴሽ ዝርዝር]] == የውጭ መያያዣዎች == {{interWiki|code=ang}} * [http://www.wmich.edu/medieval/research/rawl/IOE/index.html The Electronic Introduction to Old English] {{Wayback|url=http://www.wmich.edu/medieval/research/rawl/IOE/index.html |date=20060615201139 }} * [http://www.kami.demon.co.uk/gesithas/OEsteps/ First steps in Old English - a course for absolute beginners] * [http://www.omniglot.com/writing/oldenglish.htm Old English (Anglo-Saxon) alphabet] * [http://beowulf.engl.uky.edu/~kiernan/BT/Bosworth-Toller.htm Bosworth and Toller, ''An Anglo-Saxon dictionary''] {{Wayback|url=http://beowulf.engl.uky.edu/~kiernan/BT/Bosworth-Toller.htm |date=20080509165820 }} * [https://web.archive.org/web/20120515201049/http://home.comcast.net/~modean52/oeme_dictionaries.htm Old English - Modern English dictionary] * [http://lonestar.texas.net/~jebbo/learn-as/origins.htm The Origins of Old English] {{Wayback|url=http://lonestar.texas.net/~jebbo/learn-as/origins.htm |date=20070115120238 }} * [http://www.nosweatshakespeare.com/shakespeare_old_english.htm Shakespeare's English vs Old English] {{Wayback|url=http://www.nosweatshakespeare.com/shakespeare_old_english.htm |date=20061111173418 }} * [http://tlt.its.psu.edu/suggestions/international/bylanguage/oegermanic.html Guide to using Old English computer characters] {{Wayback|url=http://tlt.its.psu.edu/suggestions/international/bylanguage/oegermanic.html |date=20100615154106 }} (Unicode, HTML entities, etc.) * [https://web.archive.org/web/20190502000644/https://www.doe.utoronto.ca/ Dictionary of Old English Project at the University of Toronto] * [http://www.ling.upenn.edu/~kurisuto/germanic/language_resources.html The Germanic Lexicon Project] * [http://www.georgetown.edu/faculty/ballc/oe/oe-texts.html Text Collections - Texts and Translations] {{Wayback|url=http://www.georgetown.edu/faculty/ballc/oe/oe-texts.html |date=20070115042416 }} [[መደብ:እንግሊዝኛ]] [[መደብ:እንግሊዝ]] bijbzloku8782etkf3fdw5oc08my1ic የደቡብ-ምሥራቅ እስያ አገራት ማኅበር 0 49024 395194 388207 2026-10-07T07:12:05Z Ziv 51918 ([[c:GR|GR]]) [[c:COM:Duplicate|Duplicate]]: [[File:Map and flag of ASEAN countries 2025.png]] → [[File:Map and flag of ASEAN countries.png]] Exact or scaled-down duplicate: [[c::File:Map and flag of ASEAN countries.png]] 395194 wikitext text/x-wiki [[ስዕል:Map and flag of ASEAN countries.png|500px|thumb|የASEAN አባላት በአሁኑ ሰአት]] '''የደቡብ-ምሥራቅ እስያ አገራት ማኅበር''' ([[እንግሊዝኛ]]፦ ASEAN ወይም Association of Southeast Asian Nations) የ[[ደቡብ-ምሥራቅ እስያ]] አገራት ስምምነት ድርጅት ሲሆን 10 አባላት አገራት አሉት። በ[[1959]] ዓም የተመሠረተ የኢንተርናሽናል መንግሥታት ጸጥታና ምጣኔ ሀብት ስምምነት ውል ወይም ጓደኝነት ነው። {{መዋቅር-ድርጅት}} [[መደብ:ፖለቲካ]] [[መደብ:ድርጅቶች]] [[መደብ:እስያ]] pp46av2o0h1kyf89ok7tz0uh4gvbnzm ኣማን ዓንዶም 0 50822 395191 363060 2026-10-06T18:04:27Z Dagio lol 55597 395191 wikitext text/x-wiki [[ስዕል:Aman andom.png|thumb|ሚካኤል አንድዬም]] '''ኣማን ሚኻኤል ዓንዶም''' (n. [[ሃዚሲን]]፣ ጣልያን ኤርትራ ፣ [[ሰኔ 21]] ከ [[1924]] - ረ. [[አዲስ አበባ]] ፣ [[ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ምክር ቤት|ኢትዮጵያ]] ፣ እ.ኤ.አ. [[በር 23]] ከ [[1974 እ.ኤ.አ.]]) [[ወታደራዊ]] [[ኤርትራ]] - [[ኢትዮጵያ]] ፣ እና የመጀመሪያው ከ [[ደርግ|ንጉሠ ነገሥት]] [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]] ከወታደራዊ ወታደራዊ ኃይል ከወረዱ በኋላ በኋላ ከ [[ኢትዮጵያ]] [[በኋላ]] [[ኮሚኒስት]] የሚባሉት [[ደርግ|ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር የሶሻሊስት ኢትዮጵያ]] ወይም ‹ደርግ› ፡፡ {{ጅምር}} [[መደብ :ደርግ]] lfkf6jxnoztamyog2mvhgsn2lquw4ms