ውክፔዲያ
amwiki
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8C%88%E1%8C%BD
MediaWiki 1.47.0-wmf.24
first-letter
ፋይል
ልዩ
ውይይት
አባል
አባል ውይይት
ውክፔዲያ
ውክፔዲያ ውይይት
ስዕል
ስዕል ውይይት
መልዕክት
መልዕክት ውይይት
መለጠፊያ
መለጠፊያ ውይይት
እርዳታ
እርዳታ ውይይት
መደብ
መደብ ውይይት
በር
በር ውይይት
TimedText
TimedText talk
ሞጁል
ሞጁል ውይይት
Event
Event talk
ፍልስፍና
0
1820
395244
378593
2026-10-22T06:50:27Z
Vividvelma
61385
Fixed typo
395244
wikitext
text/x-wiki
'''ፍልስፍና''' የሚለው ቃል ከ[[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪኩ]] «''Philos''» /ፊሎስ/ ማለትም ፍቅር እና፣ «''sophos''» /ሶፎስ/ (ጥበብ) የተገኘ ውሁድ ነው። በቀጥታው የጥበብ ፍቅር ወይም ፍቅረ ጥበብ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በመሆኑም ፍልስፍና እውቀትን፣ እውነትን፣ ጥበብን መውደድ፣ መሻት፣ መመርመር ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ባንድ በኩል ወደ ጥበብ የተሳበ፣ ጥበብን የወደደ እንደዚሁም የጥበብ ባለሟልን የሚያመለክት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጥበብን ወዶ ሌላውም እንዲወድ ምክንያት የሚሆን ለማለት ይውላል። ይህ የጥናት ክፍል በዋናነት ነገሮችን በመላምታዊ መንገድ ለመመርመር ይሞክራል።
የፍልስፍናን ምንነት ለማወቅ የሚጠይቃቸውን ዋነኛ ጥያቄዎች እንመልከት።
== ፍልስፍናዊ ጥያቄዎች ==
ፍልስፍና የሚመረምራችው አምስት ዋነኛ ቁምነገሮች ህላዌ፣ ግብረገብ፣ ዕውቀት፣ እውነት፣ እና ውበት ናቸው። ፈላስፋዎችን ለብዙ ዘመናት ሲያስጨንቁ ከቆዩ ጥያቄዎች ውስጥ

* እውነት ምንድር ነው? አንድን አስተያየት ለምንና እንዴት እውነት ወይም ሃሰት መሆኑን እናውቃለን? ጥበብስ ምንድር ናት?
* አዋቂነት የሚቻል ነገር ነውን? ማወቃችንን እንዴት እናውቃለን? አዋቂነት የሚቻል ነገር ከሆነ የታወቀ እና ያልታወቀ ማለት ምንድር ነው? ከታወቀው ያልታወቀውን እንዴት መሻት እንችላለን?
* ግብረገብ በሆነው እና ባልሆነው መካከል ልዩነት አለን? ካለስ ልዩነቱ ምንድር ነው? የትኞቹ ድርጊቶቻችን ናቸው ልክ? ልክ ያልሆኑትስ የትኞቹ ናቸው? ሥነምግባራዊ መስፈርቶች ቋሚ ናቸው ወይስ ተነፃፃሪ? እንዴትስ መኖን አለብኝ?
* ገሃድ የሆነው ምንድር ነው? የገሃድ ነገሮች ተፈጥሮአቸው እንዴት ያለ ነው? እውን አንዳንድ ነገሮች ከኛ ግንዛቤ ውጭ መኖር ይቻላቸዋልን?
* ውበት ምንድር ነው? ውብ የሆኑ ነገሮች ከሌሎቹ በምን ይለያሉ? ሥነጥበብ ምንድር ነች? ሃቀኛ ውበት የገኛልን? የሚሉት ናቸው።

[[ስዕል:Plato-aristotle.jpg|thumb|120px|left|[[ፕሌቶ እና አሪስጣጣሊስ]]]]
እነዚህ ከላይ በደፈናው የተጠቀሱ ጥያቄዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው አመክንዮአዊ፣ ሥነ-እውቀታዊ፣ ሥነ-ምግባራዊ፣ ሥነ-ኃልዮአዊ፣ እና ሥነ-ውበትአዊ በመባል ይታወቃሉ። ምንም እንኳን እነዚህ ዋነኞቹ ጥያቄዎች ይሁኑ እንጂ ብቸኞቹ አይደሉም። በተጨማሪም በመካከላቸው አንዳንድ መደራረብ ይታያል። ታዋቂው የ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] ፈላስፋ [[አሪስጣጣሊስ]] [[ሥነ-መንግሥት]]፣ [[ሥነ ፍጥረት|ሥነ-ተፈጥሮ]]፣ [[ሥነ-ምድር]]፣ [[ሥነ፡ሕይወት (ባዮሎጂ)|ሥነ፡ሕይወት]]፣ [[ሥነ-አየር]] እና [[ሥነ ፈለክ]] የፍልስፍና ክፍሎች ናቸው ብሎ ያምን ነበር።

ሌሎች የፍልስፍና ባህሎች ከ[[ምዕራባውያን ፍልስፍና]] በተለየ በነዚህ ጉዳዮች ላይ በዙም አላተኮሩም። ምንም እንኳን የ[[ሂንዱ ፍልስፍና]] በዚህ አንፃር ከምዕራባውያኑ ቢመሳሰለም እስከ 19ኛው ምዕት-አመት ድረስ በ[[ኮሪይኛ]]፣ በ[[ጃፓንኛ]]፣ እና በ[[ቻይንኛ]] ውስጥ "ፍልስፍና" የሚል ቃል ይገኝ አልነበረም። በተለይ የ[[ቻይና]] ፈላስፎች ከግሪኮቹ ለየት ያለ የምደባ ስርዓት ይከተሉ ነበር።
== ፍልስፍናዊ ባህሎች ==
=== የምዕራቡ ዓለም ፍልስፍና ===
የምዕራቡ አለም ፍልስፍና የሚጀምረው ከግሪኮች ሲሆን የመጀመሪያው ፈላስፋ ተብሎ የሚታወቀው [[ታሊዝ]] ነው። ይህ ሰው የኖረበትን ጊዜ ለማወቅ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም። ይኸውም በ[[593 ዓክልበ.]] (ዓም) የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚኖር በመተንበዩ ከዚህ ጊዜ የተወሰነ አመት ቀደመ ብሎ ማይሌጠስ በተባለችው የትንሹ እስያ (የአሁኑ [[ቱርክ]]) ክፍል እንደተወለደ የታወቀ ነው። ታሊዝ ዓለም እና በውስጡ ያሉ ነገሮች ሁሉ ከ[[ውሃ]] እንደተፈጠሩ ያምን ነበረ። ከሱ በኋላ የተነሱ የግሪክ ፈላስፎች የሱኑ መንገድ በመከተል ዓለም ከአንድ ወይም ከሌላ ነገረ እንደተፈጠረች አስተምረዋል። ለምሳሌ [[አናክሲሜነስ]] የ[[ዓለም (ፍልስፍና)|ዓለም]] ጥንተመሰረቷ [[አየር]] ነው ሲል፣ [[ሄራቅሊጠስ]] [[እሳት]] ነው ብሏል። [[አናክሲማንደር]] ከነዚህ ሁሉ ለየት በማለት የዓለም መሰረቷ ይህ ነው የማይባል «''apeiron''» ወይም የትየለሌ የሆነ ነገር ነው ይላል።
የምእራቡን ዓለም ፍልስፍና እስክ 1900 ድረስ ቅርጽ እንዳስያዙ የሚነግርላቸው ፈላስፋዎች የሚከተሉት ናቸው፡
ሶቅራጥስ፣ አሪስጣጣሪስ፣ ፕላጦ፣ አክዊናስ፣ ኤራስመስ፣ ማኪአቬሌ፣ ቶማስ ሞር፣ ሞንታጝ፣ ግሮቲየስ፣ ዴካርት፣ ሆበስ፣ ስፒኖዛ፣ ሎክ፣ ሌብኒሽት፣ በርክሌ፣ ሑሜ፣ ቮልቴይ፣ ሩሶ፣ ካንት፣ ሺለር፣ ሄግል፣ ሾፐናዎር፣ ጆን ኦስቲን፣ ጄ.ኤስ. ሚል፣ ኮምቴ፣ ዳርዊን፣ ማርክስ፣ እንግልስ፣ ፍሬደሪሕ ኚሼ፣ ዱርካሂም
=== የምስራቁ ዓለም ፍልስፍና ===
የምስራቁ አለም ፍልስፍና መነሻ ኢትዮጲያ ናት፡፡እንደውም የመላው አለም፡፡
በተለይ ኮከባቸው gemini የሆኑት የሐበሻ ተወላጆች የኮከባቸውን ሀያልነት በመጠቀም ወደ አረቡ አለም በመገስገስ የምድራችንን የፍልስፍና መንገድ ቀይሠዋል፡፡{{citation needed}}
===ፍልስፍና በኢሥላም===
“ሐኪም” حَكِيم ማለት “ጥበበኛ” ማለት ሲሆን “ሓኪም” حَٰكِمِين ማለት ደግሞ “ፈራጅ” ማለት ነው፤ ሁለቱም “ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” “ተጠበበ” ከሚል ግስ የመጡ ናቸው፤ “ሒክማህ” حِكْمَة ማለት “ጥበብ” ማለት ሲሆን “ሑክም” حُكْم ደግሞ “ፍርድ” ማለት ነው፤ ጥበብ እና ፍርድ የጥበበኛው እና የፈራጁ [[አላህ]] ባህርያት ናቸው፤ አላህ እጅግ በጣም ጥበበኛ ነው፦
28፥9 «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው *ጥበበኛው* አላህ ነኝ፡፡ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّهُۥٓ أَنَا ٱللَّهُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
3፥6 እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው *ጥበበኛው* ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى يُصَوِّرُكُمْ فِى ٱلْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَآءُ ۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብን ከአላህ የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጦታል፦
2፥269 *ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብንም የሚሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ*፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡ يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
አላህ ጥበብን ለሰው ልጆች በዐቅል እና በነቅል ይሰጣል፤ እነዚህ ሁለት የጥበብ ጭብጦችን ነጥብ በነጥብ እንይ፦
ነጥብ አንድ
* “ዐቅል”
“ዐቅል” عقل ማለት “ግንዛቤ”Metacognition” ማለት ሲሆን አላህ በ[[ቁርአን]] “ለዐለኩም ተዕቂሉን” لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُون ይለናል፦
12:2 በእርግጥ እኛ *ትገነዘቡ ዘንድ* ዐረብኛ ቁርአን ሲሆን አወረድነው። إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
2:242 እንደዚሁ አላህ አንቀጾቹን *ትገነዘቡ ዘንድ* ለእናንተ ያብራራላችኋል፡፡ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
“ትገነዘቡ ዘንድ” የሚለው ቃላት በአጽንዖትና በእንክሮት ልናጤነው የሚገባ ሃይለ ቃል ነው፤ የሰው ልጅ “አዕምሮ” እራሱ “ዐቅል” ይባላል፤ ዐቅል የጥበብ ተውህቦ”faculty” ነው፤ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ጥበብን ይወዳል፤ “ፊሎሶፍይ” φιλοσοφία የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ፊሎስ” φίλος “ፍቅር” እና “ሶፎስ” σοφός “ጥበብ” ሲሆን “የጥበብ ፍቅር” ማለት ነው፤ ይህም [[ሥነ ጥበብ]] በውስጡ፦
*[[ሥነ-አመክንዮ]] ”logic”፣
*[[ሥነ-ኑባሬ]] ”Ontology”፣
*[[ሥነ-እውነት]] ”metaphysics”፣
*[[ሥነ-ዕውቀት]] ”epistemology”፣
*[[ሥነ-መለኮት]] ”theology”፣
*[[ሥነ-ምግባር]] ”ethics”፣
*[[ሥነ-ውበት]] ”aesthetics”፣
*[[ሥነ-መንግሥት]] ”politics”፣
*[[ሥነ-ቋንቋ]] ”Linguistics”
የመሳሰሉት እሳቦት ይዟል። ጥበብ”craft” እራሱ፦ ሥነ-ጥበብ፣ እደ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ እና አውደ-ጥበብ ለአሉታዊ ነገር ከተጠቀሙበት ምግባረ-እኩይ”witch-craft” ሲሆን በአውንታዊ ከተጠቀምንበት ምግባረ-ስናይ”art-craft” መማሪያም ነው፤ አላህ፦ “አፈላ ተዕቂሉን” أَفَلَا تَعْقِلُون ይለናል፦
21:10 *ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደ እናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አትገነዘቡምን*? لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَٰبًۭا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
“አትገነዘቡምን?” የሚለው ቃላት በአጽንዖትና በእንክሮት ልናጤነው የሚገባ ሃይለ ቃል ነው፤ ቁርአን ክብራችን በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ነው፤ አዎ የሰው ልጆች ሊከብሩበት የሚችሉበት ጥበብ ይዟል።
ነጥብ ሁለት
*“ነቅል” -
“ነቅል” نفل ማለት “አስተርዮ”epiphany” ማለት ሲሆን “ወሕይ” وَحْى ነው፤ አምላካችን አላህ ወደ ነብያችን””ﷺ”” ጥበብን አውርዷል፦
4፥113 አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና *ጥበብን* አወረደ፡፡ *የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا
ይህም ጥበብ ክብራችን በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ቁርአን ነው፤ ቁርአን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ ነው፦
10፥1 “አሊፍ ላም ራ” ይህቺ *ጥበብ* ከተመላው መጽሐፍ ከቁርኣን አንቀጾች ናት፡፡ الٓر ۚ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ
30፥2 ይህች *ጥበብ* ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ
36፥2 *ጥበብ* በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡ وَٱلْقُرْءَانِ ٱلْحَكِيمِ
ስለዚህ ክብራችን በውስጡ ያለበትን ይህንን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ መገንዘብ ግድ ይላል ማለት ነው፤ የእሳት ሰዎች “የምናገናዝብ” በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ብለው ይፀፀታሉ፦
67:10 የምንሰማ ወይንም *”የምናገናዝብ”* በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ይላሉ። وَقَالُوا۟ لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِىٓ أَصْحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ
(✍ከወንድም ወሒድ ዑመር)
== ተግባራዊ ፍልስፍና ==
{{መዋቅር-ትምህርት}}
[[መደብ:ፍልስፍና|*]]
7oixtu82l78pdku5ce07z1qkl2p4nmr
ቡርኪና ፋሶ
0
1865
395241
395051
2026-10-21T14:35:49Z
Ziv
51918
([[c:GR|GR]]) [[File:Coat of arms of Burkina Faso (1984-2025).svg]] → [[File:Coat of arms of Burkina Faso (1997–2025).svg]] → The file was renamed on Commons, but the filename in the language versions was not changed ([[c:c:GR]])
395241
wikitext
text/x-wiki
{{የሀገር መረጃ|
ስም = ቡርኪና ፋሶ|
ሙሉ_ስም = ቡርኪና ፋሶ
Burkina Faso|
ባንዲራ_ሥዕል = Flag_of_Burkina_Faso.svg|
ማኅተም_ሥዕል =Coat of arms of Burkina Faso (1997–2025).svg|
መዝሙር = ''Une Seule Nuit''

ካርታ_ሥዕል = Burkina Faso in its region.svg|
ካርታ_መግለጫ_ፅሁፍ = ቡርኪና ፋሶ በቀይ ቀለም|
ዋና_ከተማ = [[ዋጋዱጉ]]|
ብሔራዊ_ቋንቋ = [[ፈረንሳይኛ]]|
የመንግስት_አይነት = ፕሬዝዳንታዊ-ሪፐብሊክ|
የመሪዎች_ማዕረግ = [[ፕሬዚዳንት]]
[[ጠቅላይ ሚኒስትር]]|
የመሪዎች_ስም = [[ሮሽ ማርክ ክርስቲያን ካቦሬ]]
[[ፖል ካባ ጤጋ]]|
ታሪካዊ_ቀናት = [[ሐምሌ ፳፱]] ቀን [[1952|፲፱፻፶፪]] ዓ.ም.
(August 5, 1960 እ.ኤ.አ.)|
ታሪካዊ_ክስተቶች = ነፃነት ከ[[ፈረንሳይ]]|
የመሬት_ስፋት = 274,200|
የመሬት_ስፋት_ከዓለም = 74|
ውሀ_ከመቶ =
0.1|
የሕዝብ_ብዛት_ግምት_ዓመት = 2017 እ.ኤ.አ.|
የሕዝብ_ብዛት_ቆጠራ_ዓመት = 2006 እ.ኤ.አ.|
የሕዝብ_ብዛት_ግምት = 19,632,147<ref>http://www.insd.bf/n/contenu/autres_publications/Projections_demographiques_sous_nationales_2007-2020.pdf</ref>|
የሕዝብ_ብዛት_ቆጠራ =
14,017,262|
የሕዝብ_ብዛት_ከዓለም = 60|
የገንዘብ_ስም = ምዕራብ አፍሪካዊ CFA ፍራንክ|
ሰዓት_ክልል = +0|
የስልክ_መግቢያ = +226|
ከፍተኛ_ደረጃ_ከባቢ = .bf|
የግርጌ_ማስታወሻ =}}
'''ቡርኪና ፋሶ''' በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት።
== ማጣቀሻ ==
{{Reflist}}
{{commons|ቡርኪና ፋሶ}}
{{በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች}}
{{መዋቅር-መልክዐምድር}}
[[መደብ:ቡርኪና ፋሶ]]
p5dnms3k70w9g54plm98rjvdh79602v
መንግስቱ ኃይለ ማርያም
0
2482
395245
388264
2026-10-22T10:46:42Z
Joseph mathewos
61403
/* growthexperiments-addlink-summary-summary:3|0|0 */
395245
wikitext
text/x-wiki
{{የፖለቲካ ሰው መረጃ
| ስም = መንግሥቱ ኀይለማሪያም
| ስዕል =
| የተወለዱት = በግንቦት 27 በ1929 እ.ኤ.አ.
[[አዲስ አበባ]]፣ [[መንግሥተ ኢትዮጵያ]]
| ቢሮ2 = የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት
| ቀናት2 = ከግንቦት ፳ ቀን [[1966]] ዓ.ም. እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን [[1983]] ዓ.ም.
| ጠቅላይ_ሚኒስትር2 = [[ተስፋዬ ዲንቃ]]
[[ታምራት ላይኔ]]
| ቀዳሚ2 =
| ተከታይ2 = [[ተስፋዬ ገብረ ኪዳን]] ''(ተግባራዊ)''
| ሌላ_ስም =
| ዜግነት =
| ፓርቲ = [[የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ]]
| ልጆች =
| ሃይማኖት = የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና
| ፊርማ =

ይህን ታሪክ የጸፍው ግለሰብ የመንግስት ሀይለማሪያ ቀንደኛ ደጋፊ እንደሆነ ከፁሁፉ አንጸር መርዳት አያዳግትም ትክክለኛውን ታሪክ ከምንጭ ጋር እንደሚያስተካክልው ተስፍ አደርጋለሁ።
'''መንግሥቱ ኀይለማሪያም''' በ[[ግንቦት 27]] በ[[1929 እ.ኤ.አ.]] በ[[አዲስ አበባ]] ተወለዱ። አባታቸው ሃምሳዓለቃ ሃይለማሪአም ወልዴ፣ እናታቸው ብዙነሽ ተሰማ ነበሩ የአሁኑ መንግስት እና ብዙ የምእራባውያን መንግስታት እሱን እንደ ኮሚኒስት ተኮር አምባገነን አድርገው የሚቆጥሩት ሲሆን የቀድሞው አምባገነን [[ሮበርት ሙጋቤ]] የጥገኝነት ጥያቄውን ከተቀበሉ ወዲህ ወደዚምባብዌ ተሰዷል ፡፡
መንጌ በሀይማኖት በኩል ብዙ አጥፍቷል ኦርቶዶክስን ማዳከም የጀመረዉ በሱ የሰልጣን ግዜ ነወ የማይካድ ግን አገርወዳድ መሪ ነበር ማንም ባለሰልጣን ሰራገበተዉ ላይ የሚገኝ በዩኒፎርም ልብሰ ነበር ሌባ የለም ብቻ አገርወዳድ መሪ ነበር
ምንም እንኳን መንግስት እንደዚህ ያሉ ክሶችን በተደጋጋሚ ቢክድም በ 2006 (2008) በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ፍ / ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሷል ፡፡ ሆኖም በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል እንዲከሰስ [[በሄግ]] አልተከሰሰም ፡፡{{ዋቢ}}
[[ስዕል:Mengistu Bundesarchiv 183-1986-0417-012.JPG|thumb|160px|መንግስቱ ኃይለ ማርያም 1978|left]]
ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም' ከ[[1966]] እስከ [[1983]] ዓ.ም. (1974 እስከ 1991 እ.ኤ.አ.) ለ17 ዓመታት የ[[ኢትዮጵያ]] መሪ ነበሩ። ወደ ስልጣን የወጡት በ[[ደርግ]] ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ንጉሠ ነገሥቱን [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]]ን በመገልበጥ ሲሆን የአብዮቱ መሪ ሆነው ከቆዩ በኋላ በ[[መለስ ዜናዊ]] በሚመራው በኢሓዴግ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን እና በአሜሪካው የቀድሞው የሲአይኤ ዳሪክተር ሃርማንኮህ እርዳታ በ1983ዓ.ም ከስልጣን ተወገዱ። በአሁኑ የሀገሩ መንግስት እና በአብዛኞቹ የምዕራባውያን አገራት የኮሚኒስት አምባገነን ተደርጎ ፣
ይህ መፈንቅለመንግስት በሲአይኤ ስውር ዘዴ የተከናወነ ሲሆን የህወሓትና የሻእብያው መሪ ከሱዳን በቦይን 777 ከቀድሞው ከሲአይኤ ዳሪክተር ከ ሃርማንኮህ ጋር ታጅበው አዲስ አበባ ገብተዋል። ይህነው የኮሎኔል መንግሰቱ ኃይለማርያም የመንግሰቱ ግልበጣ ሳቦታጅ!! መንግስቱ ኃይለማርያም ያላሰበው ግልበጣ ተቀናብሮበት ያለአማራጭ በአየርላይ ቀረ እንጂ በራሱ ፍላጎት ሸሽቶ ዚምቡዋቤ ተሸሸገ የሚለው አባባል ከእውነት የራቀነው። ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በቃላቸው የሚገኙ አገር ወዳድ ጀግና ሰው እንደነበሩ እናውቃለን።
መንግሥቱ ኃይለማሪያም ወደ ርዕሰ ብሄርነት ሥልጣን ብቅ ሲሉ ገና የ፫፯ ዓመት ወጣት የነበሩ ሲሆኑ በሀረር የ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ ይሰሩ ነበር። በወቅቱ በክፍለ ጦሩ አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሓይሌ ባይከዳኝ የሚባሉ ኮ/ መንግስቱን በባህሪያቸው በመጠርጠራቸው ከአጠገባቸው ዞር ለማድረግ ወደ ኦጋዲን አዛውረዋቸው እንደ ነበር ይነገራል። በእዚያም ጥቂት ጊዜ በኋላ ለትምህርት ወደ [[አሚሪካ]] [[ሜሪላንድ]] ለወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት ተላኩ።
ከትምህርት ሲመለሱም በ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።
ከዛም በደረጃ እድገት ካገኙ በሁዋላ የአፄ ኃይለስላሴን ጨቋኝ አገዛዝ ለመገርሰስ የደርግ ኩዴታን መሰረቱ በመኮንኖች ህብረት የተመሰረተው ደርግ በአብዛኛው ተደማጭነትና የፓለቲካ ብስለት በነበራቸው በቆራጥነታቸው ታዋቂ በሆኑት በመንግስቱ ኃይለማርያም ስልታዊ አደረጃጀት ተቀናብሮ የንጉሱን ወንበር ገለበጡት ይህ በሆነ ወቅት በነበረው አለመረጋጋት በከተማው የተኩስ ልውውጥ ተደረጎነበር።
የመጀመርያውን ስልጣን በመያዝ የደርግ ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙት ጀኔራል አማን አምዶም ነበሩ።
በተለያየ አመታት በተለያየ ክህደትና አሻጥር የተገኙ አመራሮች ከስልጣን ሲወገዱ ቆይተው በአራ0ተኛው ዙር ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ የመጀመርያው [[ፕሬዝዳንት|ፕሬዚዳንት]] ለመሆን በቅተዋል።
[[ስዕል:ET-Red Terror Martyr Memorial Museum, Addis Abeba (1).JPG|thumb|የመንግስቱ ተቃዋሚዎች]]
ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት [[ሶማሊያ]]የዚያድባሬ መንግስት በሶቭየቶች ተደግፋ ሀገራችንን ድንገት ወረረች። በወቅቱ [[የአሜሪካ ፕሬዚዳንት]] ነበሩትን ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተርን ፈጣን ወታደራዊ እርዳታ ጠይቀው እሳቸውም የንጉሱ የቅርብ ወዳጅ ስለነበሩ በስዊስ ባንክ ያለውን የኢትዮጵያ ሃብት ለመንግስቱ ኃይለማርያም ከሰለመስጠት በተደረገው ውይይት የአሜሪካ እጅ ስለነበረበት መንግስቱ ነጮችን በ73 ሰአት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ አድርጎ ስለነበር በዚህ ቂም ጥያቄውን ሳይቀበሉ ቀሩ። በእዚህም ምክንያት አማራጭ ያጣው ደርግና መንግሥቱ ሀገሪቱ በከፍተኛ ስጋት ላይ በመውደቋ የግድ ወደ ሞስኮ መሳሪያ ልመና ልኡካን ላኩ። በሌላ በኩል ሞስኮ ከሶማሊያ ጋር ጥቅምዋን በማወዳደር ለመንግስቱ መሳሪያ መስጠት ካስፈለገ በፊርማ ሶሻሊስት ካምፐ መግባቱን እንዲያረጋግጡ ስለ ጠየቀች ኮ/መንግሥቱ ይህን በማድረጋቸው በይፋ የሚመሩት አብዩት የሌኒኒስት ማርክሲስት መሆኑን በአዋጅ አሳወቁ። ኮ/መንግሥቱ የቼጉቬራና የሶቬቱን ማርክሲዝም አሜሪካ ለወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት በተላኩበት ዘመን ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ሃር ሳይመለሱ ወደ ሞስኮ በማምራት የራሻን ሶሻሊዝም በግላቸው ተምረው ነበር፣ወደ አገር ሲመለሱም ንጉሱ በዚህ ድርጊታቸው ለሁለት አመት በኦጋዴን በረሃ በቅጣት እንዲቆዩ ተደርጎነበር። የመንግስቱ ስለሶቪየት ሶሸሰሊዝም ፖለቲካ እውቀት የሚያውቁት የቅርብ መኮንኖች በደርግ ኩዴታው የነቃውንና ብስለት ያለውን ደፋሩን መንግስቱ ኃይለማረወያምን ነበር በአደራጅነት የመደቡት።
ከስምምነቱም በሁዋላ በ፪ ወር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሚሊዮን ዶላር ታንክና የጦር መሣሪያ እርዳታ ማግኘት ብቻ ሳይሆን በሞስኮ በኩል የኩባን የጦር አማካሪዎች በማግኘታቸው የወራሪውን የሶማሊያን ኃይል መመከት ችለዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ የጭንቅ ጊዜ ጥያቄ መላሽ ሆና ባለመገኘትዋና በንጉሱ ስም በስዊስ ባንክ የተቀመጠውን በትሪሊዮን የሚቆጠር ዶላርና ወርቅ የስዊስ ባንክ ለኢትዮጵያ መንግስት እንድትመልስ መንግስቱ ኃይለማረወያም ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረጓ የአሜሪካ ትብብር በመኖሩ ምክንያት መንግስቱ ኃይለማርያም በስልጣን እስከቆዩበት ዘመን ሁሉ በዋና ጠላትነት ተፈርጀዋል። አንዳንድ ሚሲዮናዊያንንም ከአገር አባረሩ። በንጉስ ኃይለስላሴ ፊርማ በስዊስባንክ የነበረው የኢትዮጵያ ሃብት እስካሁን አልተመለሰም። [[ዐቢይ አህመድ|አብይ አህመድ]] ይህን የመጠየቅ ወኔ የለውም፣ምፅዋእት ከመለመን በቀር።
በወቅቱ በአገር ውስጥ ግንባር ቀደም ተቃናቃኝና ተቃዋሚ ከነበረው ከኢህአፓ ጋር የከተማ ለከተማ ውጊያና መገዳደል ተጀመረ። ሁለቱም ወገኖች ቀን በቀን ግድያም ለብዙ ወጣትና አዋቂ እልቂት ምክንያት ሆኑ።
መንግሥቱ ኃ/ማሪያም በወታደራዊ አመራር ውስጥ የተከስተው የስልጣን ዝቀጠትና ምግባረ ብልሹነት፤ የደህንነቱ ክፍል በሁለት ቢላዋ መብላት፣ ተደማምሮ ውድቀታቸውን እንዳፋጠነው የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።
የመንግስቱን አስተዳደር ለውድቀት ያበቃው የኮሎኔሉ አምባገነን አመራር ነው የሚሉት ተቀናቃኞቻቸውና በሁለት ቢለዋ እየበሉ አገርን ለመሸጥ ያስማሙ የነበሩ በወቅቱ (በመኢሶን) ውስጥ ተሰግስገው የነበሩ የኦነግ ስውር ባንዳ መኮንኖችና የ(TPLF) እና የ (EPLF) ሰላዮችና አገር በሆድና በስልጣን የሸጡ የመንግስቱ ተቀናቃኞች መረጃን አሾልኮ ለተቃዋሚ ኃይሎች አሳክፎ በመስጠት እንደሆነ ይታወቃል።
በመንግስቱ ኃይለማርያምላይ የተቀነባበረ የ 16 ግዜ የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸው አምልጠዋል።
ጠላቶቻቸው ከውስጥና ከውጭ ብዙ ስለነበሩ ለ17 አመታት ቀንና ሌሊት ሲዋጉ አገርን በልማት በምርት ዘመቻ፣በትምህርትዘመቻ፣እንዲሁም ስራአጥነትንና ሴተኛ አዳሪነትን ለማስወገድ የኢንዱስትሪ ስራዎችን በመክፈትና በማስፋፋት መሬትን ለአራሹ በመሰከፋፈል፣ ለደሃው ህዝብ ርካሽ የቤትክራይን በመደንገግ፣ለአገራቸው ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከቱ ታላቅ መሪናቸው። ይህን በጎ ተግባራቸውን ለመናገር የሚያንቃቸው የግል ጥቅማቸውን ከአገር ጥቅም ይልቅ አብልጠው የሚወዱ ተቀናቃኝ ሰዎች ብቻ ናቸው።
መንግሥቱ (የቀድሞው) ርዕሰ ብሔር ማንኛውም መሪ ላይ ሊከሰት የሚችል ስህተት ነው የፈፀሙት...ስለ ሐገር ስለ ብሔራዊ ክብር እና ኩራት ግን እርሳቸው ! ከፊት ቢሠለፉ የሚገባቸውና የሚያምርባቸው ናቸው።
የኮሎኔል መንግስቱን ህይወት ተቀጥፋ ለማየት የጓጉና የፎከሩ ሁሉ ቀድመዋቸው ሞተዋል!!
የእድሜ በለፀጋው ጓድ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሦስት ልጆች አባት ሲሆኑ 3ስቱም ልጆቻቸው ዶክተሮች ናቸው። ዛሬ የ 83 አመት አዛውንት ሆነው በሃራሬ በህይወት ይገኛሉ።
<ref>http://www.madote.com/2018/08/why-photo-of-mengistu-haile-mariam-has.html</ref><ref>https://borkena.com/2018/08/01/hailemariam-desalenge-met-colonel-mengistu-hailemariam-in-zimbabwe/</ref>
በብዙ መልኩ ይህ አምባገነን በ[[ስታሊኒዝም]] ተመስጦ ነበር።
==ማህበራዊ አውታረ መረቦች==
*[https://www.facebook.com/guadmengistu መንግስቱ በፌስቡክ]
==ማጣቀሻዎች==
57gu456hiau3swroszbrfbqrlekishl
የዊኪፔዲያዎች ዝርዝር
0
50963
395243
369213
2026-10-21T16:45:55Z
~2026-56352-62
61389
/* የዊኪፔዲያ እትም ኮዶች */ Added links
395243
wikitext
text/x-wiki
[[ስዕል:Wikipedia Portal Screenshot (2022).svg|thumb|በጽሑፍ ቆጠራ የተደረደሩ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚያሳይ የዊኪፔዲያ መተላለፊያ ገጽ ቅጽበታዊ ገጽ እይታ]]
== የዊኪፔዲያ እትም ኮዶች ==
[[:en:List of Wikipedias]]
4wgsx7aiowjdnpwpi6ffctwrzgmclrw
AK-47
0
54907
395242
385248
2026-10-21T15:27:21Z
Ziv
51918
([[c:GR|GR]]) [[File:Coat of arms of Burkina Faso 1984-1991.svg]] → [[File:Coat of arms of Burkina Faso (1984–1997).svg]] → The file was renamed on Commons, but the filename in the language versions was not changed ([[c:c:GR]])
395242
wikitext
text/x-wiki
[[ስዕል:AKM automatkarbin - 7,62x39mm.jpg|alt=ኤ.ኬ.ኤም ክላሽ|thumb|492x492px|'''ኤ.ኬ.ኤም ክላሽ''' ፤ በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ የክላሽንኮቭ ቤተሰብ ]]
'''AK-47''' በይፋዊ አጠራሩ '''አቭቶማት ካላሽኒኮቫ 1947''' ('''ክላሽንኮቭ ፤ ክላሽኒኮቭ''' ወይም '''ክላሽ''' ብቻ በመባልም ይታወቃል) 7.62×39 ሚሜ ጥይት የሚጠቀም ጠመንጃ ነው። ይህ መሣሪያ በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት በሩሲያዊው ታዋቂ የጦር መሣሪያ ዲዛይነር ሚካሂል ካላሽኒኮቭ የተሠራ ሲሆን የካላሽኒኮቭ የጠመንጃ ቤተሰብ መሠረት ነው። ይህ ኤኬ-47 የተሰኘው ሞዴልና መሰል የጦር መሳሪያዎቹ ከተሠሩ ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ ቢቆጠሩም፣ ዛሬም ድረስ በዓለም ላይ በስፋት ከሚታወቁና በብዛት ጥቅም ላይ ከዋሉ የጦር መሣሪያዎች ተርታ ይመደባሉ።
== ታሪክ ==
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመን ኃይሎች ጥቅም ላይ የዋለው ስተርምገዌር 44 (Sturmgewehr 44) የተባለው ጠመንጃ በሶቪየት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። የጀርመኑ ጠመንጃ አዲስ የሆነ መካከለኛ መጠን (ካሊበር) ያለው ጥይት እንዲሁም እንደ መትረየስ እሩምታ ተኩስ የመተኮስ ችሎታን ያጣመረ ነበር። ሶቪየቶች በመሳሪያው ተደንቀው የራሳቸውን መካከለኛ ካሊበር ያለው አውቶማቲክ ጠመንጃ ለመሥራት አነሳሽነት ሆነ።
ውጤቱም ኤስ ኬ ኤስ በመባል የሚታወቀው ግማሽ አውቶማቲክ ጠመንጃ ነበር። SKS 7.62x39ሚሜ ጥይት ይጠቀማል።[2] ሆኖም ኤስ ኬ ኤስ በቂ አውቶማቲክ ስላልነበረ ብዙም ሳይቆይ ሶቪየቶች ይበልጥ ዘመናዊ የሆነውን ኤኬ-47 የተባለውን ጠመንጃ ሠሩ። ኤኬ-47 በፍጥነት ኤስ ኬ ኤስን በመተካት በሶቪየት ወታደሮች ዘንድ ተወዳጅነትን አገኘ። በኋላም በ1959 እ.ኤ.አ. AKM የተባለ ቀለል ያለ፣ በአረብ ብረት የታተመ የኤኬ-47 ሞዴል ተሰራ። ኤኬኤም ከኤኬ-47 ተከታታይ የጦር መሳሪያ ዘሮች በስፋት የሚገኘው ነው። በ1960ዎቹ ደግሞ አር ፒ ኬ (RPK) የተባለ ቀላል መትረየስ ተሰራ፤ ይኸውም የኤኬ-47 አይነት ሆኖ ይበልጥ ጠንካራ አፈሙዝ እና መቆሚያ ያለው ነበር።
=== ጽንሰ-ሐሳብ ===
ሚካሂል ካላሽኒኮቭ የጦር መሣሪያ ዲዛይነር በመሆን ሥራውን የጀመረው እ.ኤ.አ በ1941 ሲሆን፣ በዚያን ወቅት በብራያንስክ ጦርነት ወቅት ከደረሰበት የትከሻ ቁስል በማገገም ላይ ነበር። ራሱ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር እንዲህ ብሏል... "ሆስፒታል ውስጥ ነበርኩ፣ ከጎኔ ካለው አልጋ ላይ አንድ ወታደር 'ጀርመኖች አውቶማቲክ መሣሪያ ሲኖራቸው ወታደሮቻችን ሁለት እና ሦስት ሆነው አንድ ጠመንጃ ብቻ የሚይዙት ለምንድን ነው?' አለኝ። በዚህ ምክንያት እኔም እንደ አንድ ወታደር ለወታደሮች የሚሆን ማሽን ለመሥራት ተነሳሁ፤ ያም የካላሽኒኮቭ አውቶማቲክ መሣሪያ ሆነ። መሣሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው በ1947 እ.ኤ.አ ነው።" <ref>{{Cite news|url=http://www.worldpress.org/cover5.htm|title=For Patriotism and Profit: An interview with Mikhail Kalashnikov|first=Robert|last=Fisk|author-link=Robert Fisk|newspaper=[[The Independent]]|location=London, England|date=22 April 2001}}</ref>
ኤኬ-47 (AK-47) ቀደም ሲል የነበሩ የጠመንጃ ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ድብልቅ ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል። "ካላሽኒኮቭ የአሜሪካን ኤም 1 ጋራንድን (M1 Garand) እና የጀርመኑን ኤስ ቲ ጂ 44ን (StG 44) ምርጥ ባህሪያትን በማጣመር አውቶማቲክ ጠመንጃ ለመንደፍ ወስኗል።"[1] የካላሽኒኮቭ ቡድን እነዚህን የጦር መሣሪያዎች የማግኘት ዕድል ነበራቸው፤ ስለዚህም ከዜሮ መጀመር አላስፈለጋቸውም። ካላሽኒኮቭ ራሱ እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ "ብዙ የሩሲያ ጦር ወታደሮች አንድ ሰው እንዴት የጦር መሣሪያ ዲዛይነር መሆን እንደሚችል፣ እንዲሁም አዲስ የጦር መሣሪያ እንዴት እንደሚነደፍ ይጠይቁኛል። እነዚህ በጣም አስቸጋሪ ጥያቄዎች ናቸው። እያንዳንዱ ዲዛይነር የራሱ መንገድ፣ የራሱ ስኬቶችና ውድቀቶች ያሉት ይመስላል። ነገር ግን አንድ ነገር ግልጽ ነው፤ አዲስ ነገር ለመፍጠር ከመሞከርዎ በፊት በዚህ መስክ ውስጥ ያሉትን ነገሮች በሙሉ በጥሩ ሁኔታ መገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ነው። እኔ ራሴ ይህ እውነት መሆኑን የሚያረጋግጡ ብዙ ተሞክሮዎች አሉኝ።"
አንዳንዶች ካላሽኒኮቭ እንደ ቡልኪን ቲኬቢ-415ን (TKB-415) ወይም እንደ ሲሞኖቭኤቪኤስ-31ን (AVS-31) ያሉ ንድፎችን ኮርጆ ነው ሲሉ ይከራከራሉ።
== ንድፍ ==
[[ስዕል:Deconstructed rifle.jpg|thumb|503x503px|ክላሽ ሲበተን]]
ኤኬ-47 (AK-47) በ1940ዎቹ መገባደጃ ላይ በሶቭየት ኅብረት በወቅቱ በነበረው እጅግ የላቀ የጅምላ አመራረት ዘዴ በመጠቀም በፍጥነትና በርካሽ ሊመረት የሚችል ቀላል፣ አስተማማኝና ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ ጠመንጃ ተደርጎ የተነደፈ ነው። ኤኬ-47 (AK-47) በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ከፍተኛ አስተማማኝነትን የሚያረጋግጥ ረጅም-ምት (long-stroke) ጋዝ ሲስተም ይጠቀማል። ትልቁ የጋዝ ፒስተን፣ በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ ክፍሎች መካከል ያለው ሰፊ ክፍተት እና ሾጣጣ ቅርጽ ያለው የካርትሪጅ ዲዛይን መሳሪያው ሳይተኮስ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ቆሻሻዎች እንዲቋቋም ያስችለዋል።
=== ጥይት ===
ኤኬ (AK) ክላሽ 7.62×39ሚሜ ጥይትን በ715 ሜትር በሰከንድ ፍጥነት ይተኮሳል።
=== የአሠራር ዘዴ ===
[[ስዕል:Chinese_type_56_AK47.jpg|thumb| የክላሽ አሰራር|438x438px]]ለመተኮስ ተኳሹ ሙሉ መጋዘን ያስገባል፣ ከዚያም ማቀባበያውን ወደ ኋላ ጎትቶ ይለቀዋል፣ ቀጥሎም አነጣጥሮ ቃታውን ይጫናል። በከፊል-አውቶማቲክ ሁኔታ መሳሪያው አንድ ጊዜ ብቻ ይተኩሳል፤ ለቀጣዩ ጥይት ቃታው ተለቅቆ እንደገና መጫን ያስፈልጋል። ሙሉ-አውቶማቲክ (fully automatic) ሁኔታ ላይ መጋዘኑ እስኪያልቅ ወይም ከቃታው እስኪለቀቅ ድረስ ጠመንጃው አዲስ ጥይቶችን ወደ ክፍሉ እያስገባ በእሩምታ መተኮሱን ይቀጥላል።
ኤኬ-47 (AK-47) የሚሠራው በጥይት ቃጠሎ አማካኝነት በሚፈጠር ጋዝ ግፊት ነው። ቃታው ሲጫን፡-
# መዶሻው ወደ ፊት ይፈናጠራል፤ የመተኮሻውን መርፌም ይመታል።
# ይህም መተኮሻውን መርፌም የጥይቱን ፕሪመር ይመታል, ይህም ጥይቱ እንዲተኮስ ያደርገዋል። ጥይቱ ከተተኮሰ በኋላ ከፍተኛ መጠን ያለው ጋዝ ይፈጠራል።
# ይህ ጋዝ በአፈሙዙ አናት ላይ ወዳለው የጋዝ ሲሊንደር ይጓዛል።
# በጋዝ ሲሊንደሩ ውስጥ ጋዙ ፒስተን የሚባለውን ክፍል ወደ ኋላ ይገፋል። ፒስተኑ ከቦልት ተሸካሚው ጋር የተያያዘ ነው፤ ስለዚህ ፒስተኑ ወደ ኋላ ሲገፋ ቦልት ተሸካሚውንም አብሮ ይገፋዋል። ቦልት ተሸካሚው ወደ ኋላ ሲንቀሳቀስ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፤
#* የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሰውን ቀለሃ ያስወጣል።
#* በተመሳሳይ ጊዜ, የመመለሻ ስፕሪንግ በመባል የሚታወቀው ክፍል ተጨምቆ ለቀጣዩ ተግባር ኃይል ያከማቻል።
#* መዶሻውን ወደ ኋላ በመሳብ ለቀጣዩ ተኩስ ያዘጋጃል።
# ቦልት ተሸካሚው የመመለሻ ስፕሪንግ በመጠቀም ወደ ፊት ሲመለስ አዲስ ጥይት ከመጋዘኑ ወደ ክፍሉ እንዲገባ ያደርጋል፣ መቀርቀሪያውን ይቆልፋል። አሁን መሳሪያው ለመተኮስ ዝግጁ ነው።
=== የተኩስ መምረጫ ===
[[ስዕል:Viet_Cong_soldier_DD-ST-99-04298.jpg|left|thumb| Việt Cộng ወታደር ኤኬ-47 ታጥቆ። መሳሪያው ቁልፍ ላይ ነው|287x287px]][[ስዕል:Ak-47-iraqis.jpg|thumb| AK-47 አፈሙዝ እና ልዩ የጋዝ ማስተላለፊያው|216x216px]]ኤኬ-47ን (AK-47) ለመተኮስ የሚውለው መቆጣጠሪያ በቀኝ በኩል የሚገኝ ትልቅ ዘንግ ሲሆን፣ ይህም ጠመንጃው አቧራ እንዳይገባበት የሚከላከል ከመሆኑም በላይ "ቁልፍ" (Safe) ላይ ሲሆን መሳሪያውን ለመጫን የሚያገለግለውን እጀታ (ማቀባበያውን) ሙሉ በሙሉ ወደ ኋላ እንዳንጎትተው ይከለክለናል። ይህ መቆጣጠሪያ በቀኝ እጃችን አመልካች ጣት የምንገለገልበት ሲሆን በሦስት ዓይነት ቦታዎች ላይ ይቆማል፤ እነዚህም "ቁልፍ" (ወደ ላይ)፣ "እሩምታ" (መሃል) እና "አንድ በአንድ/ ከፊል-አውቶ" (ወደ ታች) ናቸው። እንዲህ የተደረገበት ምክንያት ወታደሮች በተደናገጡ ጊዜ መቆጣጠሪያውን ወደ ታች አጥብቀው ስለሚገፉት "እሩምታ" የሚለውን አማራጭ ትተው በቀጥታ ወደ "አንድ በአንድ" በመቀየር ጥይት እንዳይባክንባቸው ነው። ጠመንጃውን ሆን ብለን "እሩምታ" ላይ ለማድረግ፤ አስበንበት መቆጣጠሪያውን በትክክል ወደ መሃል ማምጣት ያስፈልጋል። ይህንን መቆጣጠሪያ በቀኝ እጃቸው የሚጠቀሙ ሰዎች እጃቸውን ከመያዣው ላይ ለትንሽ ጊዜ ማንሳት ስለሚጠበቅባቸው በጣም ምቹ አይደለም። ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመስጠት አንዳንድ የኤኬ (AK) አይነት ጠመንጃዎች ከጎን በኩል ሌላ መቆጣጠሪያ የተገጠመላቸው ሲሆን ይህም በተኳሹ ቀኝ አውራ ጣት የሚሠራ ነው። ይህ አዲሱ መቆጣጠሪያ ሦስት ቦታዎች ያሉት ሲሆን እነርሱም፡- "ቁልፍ" (ወደ ፊት)፣ "እሩምታ" (መሃል) እና "አንድ በአንድ" (ወደ ኋላ) ናቸው።
=== ማነጣጠሪያ ===
[[ስዕል:AK47-rear-sight.jpg|thumb| 100 ሜትር - 800 ሜትር ማነጣጠሪያ ያለው የቻይና ክላሽ|336x336px]]
ኤኬ-47 (AK-47) ላይ የተገጠመው የብረት ማነጣጠሪያ ከ100 ሜትር ጀምሮ እስከ 800 ሜትር ርቀት ድረስ በ100 ሜትር ልዩነት የሚስተካከል ነው። ይህ ማነጣጠሪያ በ100 ሜትር ልዩነት ምልክት የተደረገበት ሲሆን ርቀቱን ለመለካት ያስችላል። የፊት ማነጣጠሪያው ከፍታውን ለማስተካከል የሚያስችል ሲሆን ይህ ማስተካከያ በውጊያ ላይም ቢሆን ሊከናወን ይችላል። ነገር ግን ጎንዮሹንለማስተካከል ልዩ መሣሪያ ያስፈልጋል፤ ይህ ማስተካከያ የሚደረገውም የጦር መሣሪያ ባለሙያዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው። የማነጣጠሪያው መስመር ከአፈሙዙ በግምት 4.85 ሴንቲሜትር ከፍ ብሎ የሚገኝ ሲሆን "П" ተብሎ የተጻፈበት ቦታ ለ300 ሜትር ርቀት የተስተካከለ ነው። ይህ ማለት አንድ ወታደር 300 ሜትር ርቀት ላይ ላለ ጠላት ኢላማውን ሲያነጣጥር በቀላሉ የጠመንጃውን ማነጣጠሪያ በጠላት ሰውነት መሃል ላይ (በቀበቶው አካባቢ) ማድረግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። በዚህ ርቀት ውስጥ የጠላት ርቀት ቢሳሳትም እንኳ በተነጣጠረው የሰውነት ክፍል ላይ ጥይቱ ስለሚመታ ስህተቱ ብዙም ጉዳት አያመጣም። አንዳንድ የኤኬ (AK) ዓይነት ጠመንጃዎች በጨለማ ውስጥ ለመዋጋት እንዲያግዝ የፊት ማነጣጠሪያው ላይ የሚገለባበጥና በ50 ሜትር ርቀት ላይ የተስተካከለ ብርሃን ያለው ምልክት ይኖራቸዋል።
=== ተገጣጣሚ ክፍሎች ===
ኤኬ-47 (AK-47) መጀመሪያ ላይ በጠጣ እንጨት በተሠሩ ሰደፍ የእጅ መያዣ እና የላይኛው ሙቀት መከላከያ ክፍሎች ነበር የሚመጣው። ዓይነት 3 ተቀባይ ከተዋወቀ በኋላ ሰደፉ፣ የታችኛው የእጅ መያዣ እና የላይኛው ሙቀት መከላከያው ከበርች እንጨት ጣውላዎች ተሠሩ። እነዚህ እንጨቶች ከአንድ ቁራጭ እንጨት ይልቅ ጠንካራ ከመሆናቸውም በላይ ቅርጻቸውን የመጠበቅ አቅማቸው የላቀ ነው፣ ብዙ ጊዜ መቆየትም አያስፈልጋቸውም፣ እንዲሁም ዋጋቸውም ያነሰ ነው። ኤኬኤስ (AKS) እና ኤኬኤምኤስ (AKMS) ሞዴሎች እንደ ጀርመናዊው ኤም ፒ 40 (MP40) ንዑስ ማሽን-ጠመንጃ ወደ ታች የሚታጠፍ የብረት ሰደፍ ነበራቸው ።
=== መጋዘን ===
[[ስዕል:Bakelite_AK_magazines.jpg|thumb| 30 ፍሬ የፕላስቲክ መጋዘን ]]
መደበኛ የመጋዘን አቅም 30 ጥይት ነው። ባለ 10፣ 20 እና 40 ሳጥን መጋዘን እንዲሁም ባለ 75-ዙር ጥምዝ መጋዘኖች አሉ።
የኤኬ-47 (AK-47) መደበኛ ባለ30 መጋዘኖች ጥይቶችን ወደ ክፍሉ በቀላሉ ለማስገባት የሚያስችል ጎልቶ የወጣ ኩርባ አላቸው። ከብረት የተሠሩት እነዚህ መጋዘኖች ከ"የጥይት መግቢያ ከንፈሮች" ጋር በአንድ ላይ (የጥይት መግቢያ ከንፈሮች ማለት ጥይቱ ወደ ክፍሉ የሚገባበትን አቅጣጫ የሚቆጣጠሩት የመጋዘኑ የላይኛው ክፍል ናቸው) እጅግ በጣም ጠንካራ ከመሆናቸው የተነሳ ጉዳት ለማድረስ እጅግ አስቸጋሪ ያደርጋቸዋል። እነዚህ መጋዘኖች በጣም ጠንካራ ከመሆናቸው የተነሳ "ወታደሮች መዶሻ በማድረግ አልፎ ተርፎም የጠርሙስ መክፈቻ በመጠቀምባቸው ይታወቃሉ።"[1][2] ይህ የኤኬ-47 (AK-47) መጋዘኖችን ይበልጥ አስተማማኝ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ ከአሜሪካ እና ከኔቶ መጋዘኖች የበለጠ ክብደት እንዲኖራቸው አድርጓል።
=== መለዋወጫዎች ===
[[ስዕል:AK-47_bayonet_and_scabbard.jpg|left|thumb| AK-47 6H2 ጩቤ]]
[[ስዕል:AK47Figure54.jpg|left|thumb| AK-47 የእጅ ቦምብ ማስተኮሻ አፈሙዙ ላይ ]]
ከጠመንጃው ጋር ከሚቀርቡት ተጨማሪ መሣሪያዎች መካከል 387 ሚሊ ሜትር (15.2 ኢንች) ርዝመት ያለው 6H3 ጩቤ (bayonet) ይገኝበታል፤ ይህ ጩቤ 200 ሚሊ ሜትር (7.9 ኢንች) ርዝመት ያለው ጦር የሚመስል ጫፍ ያለው ስለት (blade) አለው። ኤኬ-47 (AK-47) ጩቤን ለመግጠም የ17.7 ሚሊ ሜትር (0.70 ኢንች) የሆነውን የአፈሙዝ ቀለበትበአፈሙዙ ዙሪያ በማንሸራተት እጀታውን ከፊት ማነጣጠሪያው በታች ባለው ጩቤ ማያያዣ ላይ መቆለፍ ያስፈልጋል።
== ባህሪያት ==
=== የአገልግሎት ዘመን ===
ኤኬ-47 (AK-47) እና ተያያዥ የጦር መሳሪያዎቹ በበርካታ አገራት ውስጥ የተመረቱ ሲሆን ጥራታቸውም እጅግ በጣም ጥሩ ከሚባሉት ጀምሮ እስከ አጠራጣሪ ጥራት ያላቸው ይገኙበታል። በዚህ ምክንያት ኤኬ-47 በአማካይ ከ6,000 እስከ 15,000 ጥይት እድሜ አለው። ኤኬ-47 ርካሽ፣ ቀላል እና ለማምረት ምቹ የሆነ ጠመንጃ እንዲሆን ተደርጎ የተሠራ ሲሆን ይህም የሶቪየት ኅብረት የጦር ኃይል መሣሪያዎችንና ቁሳቁሶችን እንደ ጊዜያዊ አድርጎ ከሚመለከትበት አስተምህሮ ጋር የሚስማማ ነው። የጦር ኃይሎቹ ብዙውን ጊዜ በቂ ድጋፍ ሳይደረግላቸው ስለሚሰማሩ እና ከአውድማ በሚያገኙት አቅርቦት ላይ ጥገኛ ስለሆኑ የጦር መሣሪያዎችን ከመጠገን ይልቅ መተካት የበለጠ ወጪ ቆጣቢ ይሆናል።
== አይነቶች ==
[[ስዕል:AK-47_bullets_from_China,_Pakistan_and_Russia.jpg|thumb| 7.62×39 ሚሜ ካርትሬጅ ከሩሲያ፣ ቻይና እና ፓኪስታን|367x367px]]
; ቀደምት አይነቶች (7.62×39 ሚሜ)
የ1948/49 እትም፡ ዓይነት 1፡ እጅግ በጣም ቀደምት ሞዴሎች ሲሆኑ የታተመ የብረት ሽፋን ተቀባይ- ያላቸው ናቸው፤ በአሁኑ ጊዜ እጅግ ብርቅ ናቸው። የ1951 እትም፡ ዓይነት 2፡ የተቀረጸ ተቀባይ አለው። በርሜሉና ክፍሉ ዝገትን ለመቋቋም በክሮሚየም ተለብጠዋል። የ1954/55 እትም፡ ዓይነት 3፡ የቀለለ፣ የተቀረጸ ተቀባይ ያለው ሞዴል ነው። የጠመንጃው ክብደት 3.47 ኪሎ ግራም (7.7 ፓውንድ) ነው።[7] ኤኬኤስ (AKS) (ኤኬኤስ-47)፡ ዓይነት 1፣ 2 ወይም 3 ተቀባዮች ያሉት ወደ ታች የሚታጠፍ የብረት ሰደፍ ነበረው።
; ዘመናዊ (7.62×39 ሚሜ)
* AKM : ቀላል፣ ቀላል የ AK-47 ስሪት; ዓይነት 4 ተቀባይ የሚሠራው ከተጨፈለቀ ብረት ነው።
* RPK : በእጅ የሚያዝ መትረየስ ስሪት ከረጅም አፈሙዝ እና እግር ጋር።
; የውጭ ስሪት (7.62×39 ሚሜ)
* ዓይነት 56 ፡ በ {{Nowrap|AK-47 Type 3}} ላይ የተመሰረተ [[ቻይና|የቻይና]] ክላሽ። <ref name="miller2001">{{Cite book|date=2001|title=The Illustrated Directory of 20th Century Guns}}</ref> አሁንም በዋነኛነት ለውጭ ገበያዎች በመመረት ላይ ነው።
== ምርት ==
ኤኬ-47 (AK-47) እና ኤኬ-103 (AK-103) በተለይም ኤኬ-103 በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት በሚተዳደረው የጋፋት የጦር መሳሪያ ምህንድስና ኮምፕሌክስ "ኢቲ-97/1" (Et-97/1) በሚል ስያሜ በአገር ውስጥ ይመረታል።
=== ሕገወጥ ንግድ ===
[[ስዕል:Somalimerirosvojen_rynnäkkökiväärejä_Maneesi.JPG|thumb| AK-47 ቅጂዎች ከሶማሊያ የባህር ወንበዴዎች በፊንላንድ ፈንጂ-ንብርብር Pohjanmaa ኦፕሬሽን አታላንታ ተይዘዋል፣ በማኔጌ ወታደራዊ ሙዚየም ውስጥ ፎቶግራፍ ተነስቷል። አክሲዮኖቹ በከፍተኛዎቹ ሶስት ኤኬዎች ላይ ጠፍተዋል።|380x380px]]
በዓለም ዙሪያ ኤኬ (AK) እና ተያያዥ የጦር መሣሪያዎቹ በመንግሥታት፣ በአብዮተኞች፣ በአሸባሪዎች፣ በወንጀለኞች እንዲሁም በሲቪሎች ዘንድ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። በአንዳንድ አገሮች ለምሳሌ ሶማሊያ፣ ሩዋንዳ፣ ሞዛምቢክ፣ ኮንጎ እና ታንዛኒያ የኤኬ (AK) የጦር መሣሪያዎች በጥቁር ገበያ ከ30 እስከ 125 ዶላር ይሸጣሉ፤ በጅምላ ከሚጭበረበሩት ምርቶች የተነሳ ዋጋቸው ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ቀንሷል። [1] በኬንያ "አንድ ኤኬ-47 (AK-47) በገንዘብ ሲገዛ ከሚገኘው ዋጋ በግማሽ ያህል ያነሰ ዋጋ አምስት ራሶች ከብቶች (ወደ 10,000 ኬንያ ሺሊንግ ወይም 100 የአሜሪካ ዶላር ገደማ) ያስወጣል"። [2] በዓለም ዙሪያ የኤኬ (AK) ዓይነት የጦር መሣሪያዎችን "በ6 ዶላር ወይም በዶሮ ወይም በአንድ ከረጢት እህል መለወጥ የሚቻልባቸው ቦታዎች አሉ።" [3][4][5]
== የባህል ተጽዕኖ ==
[[ስዕል:Flag_of_Mozambique.svg|thumb| AK-47 [[የሞዛምቢክ ሰንደቅ ዓላማ|በሞዛምቢክ ባንዲራ]] ላይ]]
[[ስዕል:Coat of arms of Burkina Faso (1984–1997).svg|thumb| በቡርኪናፋሶ የቀድሞ የጦር ካፖርት ላይ ያለው AK-47]]
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሶቭየት ኅብረትና ቻይና እንዲሁም አሜሪካና ሌሎች የኔቶ አገሮች በዓለም ዙሪያ ላሉ በርካታ አገሮችና አማፂ ኃይሎች የጦር መሳሪያና የቴክኒክ እውቀት ይሰጡ ነበር። በዚሁ ጊዜ ምዕራባውያን አገሮች እንደ ኤፍ ኤን ፋል (FN FAL)፣ ኤች ኬ ጂ 3 (HK G3)፣ ኤም 14 (M14) እና ኤም 16 (M16) ያሉ በአንጻራዊነት ውድ የሆኑ አውቶማቲክ ጠመንጃዎችን ይጠቀሙ ነበር። በሌላ በኩል ሩሲያውያንና ቻይናውያን ኤኬ-47ን (AK-47) ይጠቀሙ ነበር፤ አነስተኛ የምርት ወጪውና በቀላሉ የመሥራት ችሎታቸው ኤኬዎችን በብዛት እንዲያመርቱ አስችሏቸዋል።
በቀድሞው የኮሚኒስት መንግስታትን ይደግፉ በነበሩ አገሮች ኤኬ-47 (AK-47) የሶስተኛው ዓለም አብዮት መገለጫ ሆኖ ነበር የሚታየው። በካምቦዲያ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲሁም በካምቦዲያና ቬትናም መካከል በተደረገው ጦርነት በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል። በ1980ዎቹ ሶቭየት ኅብረት ምዕራባውያን ማዕቀብ በጣሉባቸው እንደ ሊቢያና ሶሪያ ላሉ አገሮች የጦር መሣሪያ ዋና አቅራቢ ነበረች፤ እነዚህ አገሮችም ከእስራኤል ጋር በሚያደርጉት ጦርነት የሶቭየት ኅብረትን ድጋፍ በደስታ ይቀበሉ ነበር። ሶቭየት ኅብረት ከፈረሰች በኋላ ግን ኤኬ-47 (AK-47) የጦር መሣሪያዎቹ በገንዘብ ለሚገዙ ሁሉ በጥቁር ገበያም ሆነ በግልጽ መሸጥ ጀመሩ፤ በዚህም የተነሳ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችን፣ የአምባገነን መሪዎችን እንዲሁም እንደ አልቃይዳ፣ አይሲስና ታሊባን ያሉ አክራሪ እስላማዊ ቡድኖች፣ በኮሎምቢያ የሚገኙትን ፋርክንና ኤጀርሲቶ ደ ሊበራሲዮን ናሲዮናልን የመሳሰሉ የሽምቅ ተዋጊዎችን እጅ ውስጥ ለመግባት በቅተዋል። ዛሬ በአፍጋኒስታንና ኢራቅ ብቻ ሳይሆን በየቦታው ይገኛል።
በሩሲያ ውስጥ ክላሽ የብሔራዊ ኩራት ምንጭ ነው።
1okmmv7sw7mkujsicqqk756isvvwacl