Wikipedia:ቀላል መማርያ/ገጽ 2

From Wikipedia

አሁን ማወቅ የሚፈለገው ገጽ በትክክል እንዴት እንደሚዘጋጅ ነው።

ብዙ የሚጠቅሙ መሣሪያዎች ጨለማ ጽሕፈት እና Italic (ኢታሊክ) ጽሕፈት ናቸው። ይህ የሚደረግ ቃልን ወይም ቃላትን በብዙ ' (ነጠላ ጥቅስ) በመክበብ ብቻ ነው፦




  • ሁለት ' ምልክቶች በየጎኑ ''እንዲህ'' ሲጨመሩ እንዲህ italic ጽሕፈት ይሰጣል።
  • ሦስት ' ምልክቶች በየጎኑ '''እንዲህ''' ሲጨመሩ እንዲህ ጨለማ ጽሕፈት ይሰጣል።
  • አምስት ' ምልክቶች በየበኩሉ '''''እንዲህ''''' ሲጨመሩ እንዲህ ጨለማ እና italic ጽሕፈት አንድላይ ይሰጣል።


በዊኪፔድያ የመጣጥፉ አርእስት ወይም ስሞች ለመጀመርያ ግዜ ሲጠቀሱ በጨለማ ጽሕፈት እንጽፋቸዋለን። እንዲሁም የመጽሐፍ ስም ወይም የውጭ አገር ቃላት ወዘተ. በitalic መጻፍ ይገባል። የውጭ አገር ቃል እና የአርእስቱ ስም በአንድ ጊዜ ሲሆን ለምሳሌ በጨለማ italic ልንጻፍ እንችላለን።

[ለማስተካከል] ንዑስ ክፍል እና ንዑስ-ንዑስ ክፍል

ንዑስ ክፍሎች የጽሑፉን አደረጃጀት ለማሻሻል ቀላል ዘዴ ናቸው። እነዚህ መጣጥፉን በክፍሎች ያካፍላሉ።

ክፍሎች እንዲህ ይፈጠራሉ፦

  • ==ላይኛ ክፍል== (በ2 የእኩሌታ ምልክቶች)
  • ===ንዑስ ክፍል=== (በ3 የእኩሌታ ምልክቶች)
  • ====ንዑስ-ንዑስ ክፍል==== (በ4 የእኩሌታ ምልክቶች)

ገጽ ቢያንስ 4 ክፍሎች ቢኖሩት፣ የገጽ ማውጫ በቀጥታ ይፈጠራል። ከዚያ በኋላ አዲስ ክፍሎች ደግሞ ለዚህ ገጹ ማውጫ በቀጥታ ይጨመራሉ።